
ካርሚን ኮርፖሬሽን የሊግ ኦፍ ሌጀንድስ የአውሮፓ ሻምፒዮን በመሆን ታሪክ ሰርቷል! እ.ኤ.አ. በ2020 የቀጥታ ስርጭት አዘጋጅ በሆኑት ካሜል «ካሜቶ» ከቢር እና ዙሄር «ኮቴይ» ዳርጂ የተመሰረተው ይህ ቡድን የኢ-ስፖርት ማህበረሰቡ ልብ ውስጥ መግባት እና በፍጥነት አንጋፋ መሆን የቻለ ሲሆን፣ በተጨማሪም በሺዎች ለሚቆጠሩ አድናቂዎቹ ትልቅ ተምሳሌት መሆን ችሏል።.
ከዚህ ቀደም ቡድኑ ካሜቶ ኮርፖሬሽን ተብሎ የሚጠራ የነበረ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በኖቬምበር 2020 ስሙን ወደ ካርሚን ኮርፖሬሽን ሊቀይር ችሏል። ብዙም ሳይቆይ እንደ ራፐር አሚነ «ፕራይም» መክሪ ያሉ ታዋቂ የጥበብ ሰዎች ላይ ኢንቨስት በማድረግ ተደራሽነቱን እና የጥበበኞች ስብስቡን በማስፋት ኢ-ስፖርት ላይ መንገስ ችሏል። ዛሬ ላይ፣ ካርሚን ኮርፖሬሽን የሊግ ኦፍ ሌጀንድስ ቡድን ብቻ ሳይሆን እንደ ሮኬት ሊግ፣ ቫሎራንት እና ስትሪት ፋይተር 6 ያሉ ጌሞች ላይ ድሎችን መቀዳጀት የቻለ ታዋቂ ስምም ነው።
ካርሚን ኮርፖሬሽን የሊግ ኦፍ ሌጀንድስ የEMEA ማስተርስ ላይ የበላይነትን በመቆናጠጥ እ.ኤ.አ.2021 በታሪክ የመጀመሪያው የፀደይ እና የበጋ ውድድሮች አሸናፊ መሆን ችሏል። በመቀጠል እ.ኤ.አ.በ2023 እንደገና በማሸነፍ የበላይነቱን በድጋሚ ማረጋጥ የቻለ ሲሆን፥ በያዝነው ዓመት እ.ኤ.አ. 2025 ደግሞ መች ተነካና በሚል በLEC ዊንተር ስፕሊት ላይ ከአውሮፓ ምርጥ ቡድኖች ተርታ ራሱን ማስቀመጥ ችሏል።
ከእነዚህ ድሎች በስተጀርባ መስራቾቹ ለተሰጥዖ ማሳደግ እና ለጥራት ማሻሻያዎች ያደረጉት ትልቅ ኢንቨስትመንት እና የሰነቁት ትልቅ ራዕይ ትልቅ ሚናን የተጫወተ ሲሆን፣ በተጨማሪም ቡድኑ በፍጥነት በማደግ ላይ ከሚገኘው የውድድር ዘመን ጋር በቀላሉ መላመድ መቻላቸው እና የተጫዋቾቹ የማይናወጥ ቁርጠኝነት ለካርሚን ኮርፖሬሽን የስኬት ምስጢር መልስ ሆኖ መቀመጥ ይችላል።
ዛሬ ላይ ቡድኑ ትልልቅ ህልሞችን ይዞ በመንቀሳቅስ ላይ ሲሆን ከቅርብ ጊዜው የLEC ድሉ በኋላም የዓለም ሻምፒዮና ለመሆን በመስራት ላይ ይገኛል። ብዙ ጌሞች ውስጥ ተገኝ መሆኑ እና የማያቋርጥ ቁርጠኝነቱ እድገቱን ምንም እንደማያስቆመው ማሳያ ነው። ካርሚን ኮርፖሬሽን ጥንካሬ እና ትጋትን በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ የኢ-ስፖርት ተጫዋቾች እና አድናቂዎች ያሳየ ትልቅ ተምሳሌት ነው።