icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ፎርትናይት በቤዝቦል ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የራሱ ገፀ-ባህሪ ያለውን ሾሄይ ኦታኒን አካቷል 

ፎርትናይት ግዛቱን ማስፋቱን የቀጠለ ሲሆን አሁን ደግሞ ጃፓናዊው የMLB ኮከብ ተጫዋች የሆነውን ሾሄይ ኦንታኒ እ.ኤ.አ ማርች 17፣ 2025 ጀምሮ ጌሙ ላይ አካቷል። የሎስ አንጀለስ ዶጀርስ ተጫዋች የሆነው ሾሄይ ኦታኒ ፎርትናይት ላይ መካተት የቻለ የመጀመሪያው የቤዝቦል ተጫዋችም ነው። 

የሾሄይ ኦታኒ ገፀ-ባህሪዎች 

1. የዶጀርስ ዩኒፎርም 

  • ባለነጭ እና ግራጫ የዶጀርስ ዩኒፎርም እና ውሻው ዲኮይን በቦብልሄድ ምስል ከሚወክል ቦርሳ ጋር በማጥመር የተዘጋጀ ሲሆን ልዩ የሌጎ ይዘትም ይኖረዋል። 

2. ሳሙራይ ሾሂ፡ 

  • ይህ አልባስ ሾሂን ወደ ጥቁር እና ወርቃማ ቀለም ያለው ዘመናዊ ሳሞራይ የሚቀይረው ሲሆን፣ ግራ ክንዱም ወደ ነበልባል እሳትነት ይቀየራል። 

  • በተጨማሪም የሚንበለበል ቤዝቦል እና ሄልሜት የያዘ "Samurai Screamer" የሚባል ቦርሳንም ያካትታል። 

ሌሎች ሽልማቶች 

  • "Trusty Two-Way" መፍለጫን እና "Baseball Batana,"። 

  • ልዩ ኢሞቶች፡-ኦታኒ ውሻው ዲኮይ ጋር ኳስ ሲመታ እና ልዩ መለያውን መሰረት ያደረገ ኢሞት። 

ልዩ ዝግጅቶች 

  • የሾሄይ ኦህታኒ ዋንጫ (ማርች 15)፡- በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ላይ የሚገኙ ተጨዋቾች የሳሞራ ሾሄን ገፀ-ባህሪ ቀድመው ማስከፈት የሚችሉበት ውድድር። 

  • የኦታኒ ጭብጥ ያላቸው ተልዕኮዎች (ከማርች 18 ጀምሮ)፡- እስከ ምዕራፍ 6 ክፍል 2 መጨረሻ ድረስ የሚቆይ እና የXP ሽልማቶችን ማግኘት የሚችሉበት ዝግጅት። 

ይህ ሽርክና እ.ኤ.አ የ2025 MLB ውድድር መጀመሩን እና እ.ኤ.አ ማርች 18-19 MLB ቶኪዮ ላይ ዶጀርስ ከ ከብስ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታን ትልቅ ድምቀትን የሚሰጥ ሲሆን፣ በተጨማሪም ፎርትናይት ስፖርት፣ ባህን፣ እና ቪዲዮ ጌምን በማዋሃድ አዲስ ተከታዮችን ማፍራት የቻለበት ልዩ ሽርክና ነው። 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !