icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ነፃ የማይንክራፍት ሰርቨር እንዴት መፍጠር ይቻላል? 

ነፃ የማይንክራፍት ሰርቨር መፍጠር ከሚያስቡት በላይ በጣም ቀላል ነው! የሚፈልጉትን ዓለም ለመገንባት ይሁን፣ ከጓደኞችዎ ጋር ለመጫወት፣ ቀላል ሂደቶችን በመከተል የራስዎን ሰርቨር መፍጠር ይችላሉ። 

1. ሆንስቲንግ ፕላትፎርም ይምረጡ 

የመጀመሪያው ሂደት ሆንስቲንግ ፕላትፎርም መምረጥ ሲሆን፥ እ.ኤ.አ በ2025 ታዋቂ ከሆኑ የሆንስቲንግ ፕላትፎርም አማራጮች መካከል፡- 

  • አትሮነስ (Aternos)፡- ቀላል እና ለአጠቃቀም ቀላል በመሆኑ፣ ለጀማሪዎች ጥሩ አማራጭ ነው። 

  • ማይን-ኸት (Minehut)፡- አብሮ የተሰራ ገበያ ያለው ሲሆን የማያቋርጥ አገልግሎት ይሰጣል። 

  • ስካላ-ኪውብ (ScalaCube)፡- ላቅ ያሉ ማስተካከያዎችን ማድረግ ለሚፈልጉ ተመራጪ ነው። 

ጀማሪ ከሆኑ እና አስቸጋሪ ግራ የሚያጋቡ ማስተካካዮችን ስለሚያስወግድ አትሮነስን (Aternos) ቢጠቀሙ ይመከራል። 

2. ሰርቨርዎን ያዘጋጁ 

2.1. የመረጡት ፕላትፎርም ላይ አካውንት ይክፈቱ። 

2.2. ሰርቨርዎን ያዘጋጁ፡- 

  • የማይንክራፍት ስሪትን ይምረጡ። 

  • የጌም ሞዱን እና ደረጃውን ይምረጡ። 

  • ስንት ተጫዋቾች መቀላቀል እንደሚችሉ ያስቀምጡ። 

3. ሰርቨርዎን ያሻሽሉ 

  • ያለምንም መቆራረጥ መጫወት እንዲችሉ የሬንደር መጠኑን ከ8–12 ያድርጉ። 

  • ሰርቨርን የበለጠ አስተማማኝ ለማድረግ እንደ ፔፐር (Paper) ወይም ስፒጎት (Spigot) ያሉ ፕለጊኖችን ይጫኑ። 

4. ደህንነቱ ያስጠብቁ 

  • አንላይን ሞድን ያብሩ፡- ይህም የተጫዋቾች አካውንት እውነተኛ መሆኑንን ያረጋግጥልዎታል። 

  • ነጭ መዝገብ ይጠቀሙ፡- ይህም የተፈቀደላቸው ተጫዋቾች ብቻ ሰርቨርዎን እንዲቀላቀሉ ያስችላል። 

  • አንቲ-ግሪፍ ፕለጊኖች፡- ግንባታዎችዎን በሌሎች ተጫዋቾች ጉዳት እንዳይደርስበት ይጠብቅልዎታል። 

 

 

5. ሰርቭርዎን እንደልብዎ ያስተካክሉ 

ሰርቨርዎን ልዩ ለማድረግ ሞዶችን ማከል፣ ፕለጊኖችን ማገናኘት ወይም አዲስ የጌም ሞዶችን መሞከር ይችላሉ። ቢፈልጉ ክላሲክ ሰርቫይቫል ዎርልድ ወይም ሙሉ በሙሉ የተስተካከለ ሰርቨር፣ የሚፈልጉትን ሁሉ እንዲያደርጉ ያስችልዎታል። 

6. ጓደኞችን ይጋብዙ 

  • የሰርቭርዎን የአይ.ፒ አድራሻ ከሆስቲንግ ፕላትፎርሙ ድህረ-ገጽ በመሄድ ያግኙ። 

  • ጓደኞችዎ ሰርቭርዎን እንዲቀላቀሉ የአይ.ፒ አድራሻውን ይላኩላቸው። 

  • የእድገት ሂደትዎ እንዳይጠፋ፣ አለምዎን በየጊዜው ባከአፕ ማድረግዎን ያስታውሱ። 

ነፃ የሆነ ፕላትፎርም እየተጠቀሙ ከሆነ፣ የሰርቨር ቦታዎች እስኪከፈቱ ድረስ ከመጠበቅ ለመዳን ቀድመው የጨዋታ ጊዜዎን ያቅዱ። 

ነፃ የማይንክራፍት ሰርቨር ማስጀመር ማንኛውም ሰው ሊያደርገው የሚቻል ቀላል ሂደት ነው። ከጓደኛዎችዎ ጋር በጋራ በመሆን የራሳችሁ ልዩ ዓለም እንዲፈጥሩ ያስችልዎታል። መልካም ጨዋታ! 

 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !