
ሞነስተር ሃንተር ዋይልድስ ውስጥ የሚገኘው “The Catch of a Lifetime” ተልዕኮ እንደ ውፐር ያሉ ግዙፍ ዓሣሳ እንዲይዙ ተልዕኮ ላይ ይሰጥዎታል። ትዕግስት፣ ብልሀት፣ እና እድል የሚጠይቅ አስቸጋሪ ተልዕኮ ሊሆን ይችላል፥ ምንም አያስቡ! ይህን ተልዕኮ እንዴት በስኬት መወጣት እንደሚችሉ ቀጥለን እናሳይዎታለን።
ዓሣ ለማጥመድ ምቹ የሆነው የስካርሌት ጫካ ውስጥ እንደ ውፐር ያሉ ግዙፍ ዓሣዎች በብዛት ይገኛሉ። በተለይ ደግሞ፦
ዞን 17፡- ይህ አካባቢ ለትልልቅ ዓሳዎች ተስማሚ ሲሆን፣ በተለይም ደግሞ መኸር ላይ ሐይቁ ስለሚሞላ በርካታ ትልልቅ ዓሳዎችን ለማግኘት ተመራጭ ቦታ ነው።
ዞን 12፡- እንደ ዞን 17 የተትረፈረፈ ባይሆንም፣ ትልልቅ ዓሳዎችን አልፎ አልፎ ማግኘት ይችላሉ።
የማግኘት እድልዎን ከፍ ለማድረግ ተገቢ የአየር ሁኔታ እና ሰዓት መምረጥ እንዳለብዎ ያስታውሱ። ለምሳሌ እንደ ታይታን ስኩዊድ ያሉ ዓሣዎች ብዙውን ጊዜ ምሽት ላይ ነው የሚገኙት።
ይህን ተልዕኮ ለመወጣት ተገቢ መሳሪያዎችን መጠቀም ወሳኝነት አለው፣ ከእነሱም መካከል፦
አርቲኩሌትድ ቤይት፡- እንደ ጋጃው፣ ግሬት ፐርች እና ግሉቶነስ ያሉ ዓሣዎች ለማጥመድ።
ስቴላርዲን ሉር፡- ግሉቶነስ ቱናን ወደ ወጥመድዎ ለመሳብ።
ቴንታክል ቤይት፡- እንደ ታይታን ስኩዊድ ያሉ የምሽት ዓሳዎች ለማጥመድ።
ስካርሌት ጫካ ውስጥ ከምትገኘው አሳ አጥማጇ ካንያ የምትሰጥዎትን ተልዕኮዎች በማጠናቀቅ እነዚህን የማጥመጃ መሳሪያዎች ማግኘት ይችላሉ።
ማጥመጃ ዘንግዎን እና ተገቢውን ማታለያ ምግብ ያዘጋጁ።
ውሃው ውስጥ ትልቅ ጥላ የሚታይበት ቦታ ላይ ማጥመጃዎን ይጣሉ።
ዓሣው የማጥመጃዎን መንጠንቆ ሲነክስ፣ በግራ በኩል የሚገኘውን ጆይስቲክ በማንቀሳቀስ የዓሣውን እንቅስቃሴ ይቆጣጠሩ፣ እንዲሁም ገመድዎ እንዳይወጠር ጥንቃቄ ያድርጉ።
ዓሣውን ለማዳከም ገመድዎን ቀስ ብለው በጥንቃቄ ይጎትቱት።
ዓሣው ድንገት ከውሃው ከዘለለ፣ እንዳያመልጥ ጆይስቲክዎን ዓሣው ወደ ሚገኝበት አቅጣጫ ያዙሩ።
ዓሣው እስኪጠጋዎ እና ከውሃው ማውጣት እስኪችሉ ድረስ፣ ከላይ ያሉትን ሂደቶች መደጋገምዎን ይቀጥሉ።
ግዙፍ ዓሣዎች ማግኘት ካልቻሉ አካባቢውን ለቀው ይሂዱ እና ቆይተው ይመለሱ ወይም ድንኳንዎ ውስጥ አረፍ ብለው የአየር ሁኔታውን ይቀይሩ።
ጊዜዎን ለመቆጠብ ዞን 17 አካባቢ ጊዜያዊ ካምፕ ያዘጋጁ።
ያስታውሱ! ትላልቅ ዓሣዎች ብርቅዬ እና እምብዛም የሚገኙ አይደሉም፣ ስለዚህ ሳይሰላቹ መሞከርዎን ይቀጥሉ።
መልካም ዕድል!