icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ሞነስተር ሃንተር ዋይልድስ ውስጥ ድራጎናይትን እንዴት ማግኘት ይቻላል? 

ድራጎናይቶች ሞነስተር ሃንተር ዋይልድስ ውስጥ የጦር መሳሪያዎችን ለማሻሻል እና ልዩ ትጥቆችን ለመሥራት የሚያገለግሉ አስፈላጊ ግብዓቶች ናቸው። ድራጎናይትን ለመሰብሰብ የሚረዳዎት ቀላል መመሪያ ቀጥለን አዘጋጅተናል። 

ድራጎናይት የት ነው የሚገኘው? 

ድራጎናይትን ማግኛ ሁለት ዋና ዋና መንገዶች ያሉ ሲሆን፡- 

1. የማዕድን ክምችቶች፡- ሹል ሰማያዊ ክሪስታሎች ያላቸው ጂኦድ የሚመስሉ መዋቅሮችን ይፈልጉ እና አንድ ሲያገኙ እቃዎችን ለመሰብሰብ B (Xbox)፣ Circle (PlayStation) ወይም F (PC) ይጫኑ። የማዕድን ክምችቶች እስከ ሶስት የሚደርሱ ግብዓቶችን ሊያስገኝ ይችላል፣ በተጨማሪም ጓደኞችዎ ጋር በመሆን ተጨማሪ መሰብሰብ ይችላሉ። 

  • ኦይል ቤዚን፡- ዞን 13 ካምፑ አቅራቢያ ሶስት ክምችቶች ያሉ ሲሆን ዞን 14 እና 16 አቅራቢያ ደግሞ ሶስት ተጨማሪ ክምችቶች አላቸው። 

  • ዋይቬሪያ ሪውንስ፡- ዞን 9 ካምፕ አጠገብ ክምችቶች ያሉ ሲሆን ይበልጥ ደግሞ ዞን 8፣ 9 እና 10 ላይ በብዛት ይገኛሉ። 

  • አይስ ክሊፍስ፡- ዞን 8 በላይኛው ክፍል ላይ እርስ በርስ የሚቀራረቡ ሶስት ክምችቶች አሉ። 

2. የተልዕኮ ሽልማቶች፡- የዋናው ታሪክ ተልዕኮዎች እና የጎን ተልዕኮዎችን በማጠናቀቅ ድራጎናይትን ማግኘት ያስችላል። 

በርካታ ድራጎናይንትን መሰብሰብ የሚያስችሉ ጠቃሚ ነጥቦች 

  • የማዕድን ክምችቶችን በቀላሉ ለማግኘት ካርታው ላይ የሚገኘውን የ"resources" ማጣሪያ ይጠቀሙ። 

  • ቦታውን ካገኙ በኋላ ቶሎ ለመድረስ የሴክሬት ታክሲን ይጠቀሙ። 

  • የክምችት ቦታዎች በየ15 ደቂቃው ስለሚፈጠሩ ዞኖችን ይቀያይሩ። 

  • ምንም እንኳን ባስቸኳይ ድራጎናይት ባያስፈልገዎትም ጉዞ በሚያደርጉበት ወቅት በመደበኛነት ይሰብስቡ። 

ተጨማሪ ዘዴዎች 

ኦይል ቤዚን ውስጥ ክራዶናቶችን በማደን ድራጎናይቶችን ማግኘት የሚቻል ሲሆን፥ እነዚህ ትናንሽ ጭራቆች ሲሸነፉ ድራጎናይት ይጥላሉ። 

የድራጎናይቶች ጥቅም 

ድራጎናይቶች በዋናነት ጥቅም ላይ የሚውሉት፡- 

  • የማዕድን ዓይነት የጦር መሣሪያዎችን ለማሻሻል። 

  • ልዩ የትጥቅ ስብስቦችን ለማዘጋጀት። 

  • ልዩ ታሊዝማኖችን ለመፍጠር።. 

ኤክስፐርት ደረጃ ላይ ከሆኑ ክራዶናቶችን ማደን በፍጥነት ድራጎናይቶችን መሰብሰብ የሚያስችል የመጠባበቂያ አማራጭ እና ቀላሉ ዘዴ ነው። 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !