
ሞነስተር ሃንተር ዋይልድስ ውስጥ ጭራቆችን በብቃት ለመቋቋም ትክክለኛውን የጦር መሳሪያ መጠቀም ቁልፍ ጉዳይ ሲሆን፣ ሁለተኛ ደረጃ የጦር መሳሪያዎች በቅርቡ የተካተቱ በመሆኑም ጌሙ ይበልጥ ተጨማሪ የስልት አካሄዶችን መከተልን ያስችላል። ምርጥ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ የጦር መሳሪያዎች ዝርዝሮችን እና አደንዎን በድል ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ ምርጥ ጥምሮችን ቀጥለን አዘጋጅተናል።
ደረጃ ኤስ የጦር መሳሪያዎች በጣም ኃይለኛ እና ሁለገብ በመሆናቸው፣ ለሁሉም የአጨዋወት ዘይቤዎች ተስማሚ ናቸው።
ቀስት (Bow)፦ በፈጣን እና የማይዛነፍ ዒላማ ያለው በመሆኑ ከሩቅ ለሚደረጉ ውጊያዎች ተመራጪ ነው። ተከታታይ ጥቃቶችን እያደረሱ እንደልብዎ እንዲንቀሳቀሱ ያስችልዎታል። ከሁለት ጩቤዎች ጋር በማጣመር፣ ጭራቆችን ከሩቅ በቀስት በማዳከም፣ ቀረብ ብለው በጩቤዎቹ መግደል ይችላሉ።
ታላቁ ሰይፍ (Great Sword)፦ ከፍተኛ ጥቃቶችን ማድረስ ለሚፈልጉ እና ታጋሽ አዳኞች ተስማሚ የሆነ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ የሚችል መሳሪያ ነው። ከባድ ጥቃቶችን በሚጥሉበት ወቅት ማበረታቻዎችን ለማግኘት ከአደን ቀንድ (Hunting Horns) ጋር አጣምረው ይጠቀሙት።
ረጅም ሰይፍ (Katana)፦ በቀላሉ ራስዎን እየተከላከሉ ኃይለኛ እና ተለዋዋጭ ጥቃቶችን እንዲጥሉ ያስችላል። ረጂም ሰይፍን ከመዶሻ ጋር በማጣመር የጭራቆችን ወሳኝ ክፍሎችን በሰይፉ በመቆራረጥ በመዶሻ ደግሞ መግደል ይችላሉ።
ደረጃ-ኤ የጦር መሳሪያዎች የተመጣጠነ ኃይል እና ስልቶችን ይሰጣሉ።
ኢንሴክት ግላይቭ (Insect Glaive)፦ ለአየር ላይ ውጊያዎች በጣም ጥሩ ሲሆን፣ ፈጣን ጉዳቶችን እያደረሱ በጭራቆች ዙሪያ እንዲያንዣብቡ ያስችልዎታል። ቡድንዎን ለማበርታት እና ቀልጣፋ ለማድረግ ከአደን ቀንድ (Hunting Horn) ጋር በማጣመር ይጠቀሙት።
መዶሻ (Hammer):- ጭራቆችን ለማስበርገግ እና ለቡድንዎ ክፍተቶችን ለመፍጠር የሚያገለግል ወሳኝ መሳሪያ ነው። ኃይልን እና ፍጥነትን አጣምሮ ለመጠቀም ከሁለት ጎራዴዎች ጋር አብረው ይጠቀሙት።
ሄቪ ቀስት (Heavy Crossbow)፦ ከጠላት ጥቃቶች በመራቅ ከፍተኛ ጉዳቶችን ማድረስ የሚያስችል ልዩ የረጅም ርቀት የጦር መሳሪያ።
ደረጃ-ቢ የጦር መሳሪያዎች ልዩ ለሆኑ አገልግሎቶኦች የሚውሉ የጦር መሳሪያዎች ናቸው።
ላንስ ካነን (Lance Cannon)፦ ጠንካራ የመከላከያ እና የፈንጂ ጥቃቶችን አጣምሮ የያዘ መሳሪያ ሲሆን፡ ግዙፍ ወይም የሚያዘግሙ ጭራቆችን ለማጥቃት ተመራጪ ነው።
ስዊች አክስ (Morpho Axe)፦ ሁለገብ ግን ቴክኒካል ሲሆን፣ መጥረቢያ እና ሰይፍን መቀያየር የሚያስችል ልዩ የውጊያ ስልቶች ይሰጣል።
ውጤታማነትን የሚጨምሩ የጦር መሳሪያ ጥምሮች ዝርዝር፡-
ቀስት + ሁለት ጩቤዎች፡- ጠላትን ከሩቅ በቀስት በማዳከም፣ ቀረብ ብለው በጩቤ መግደል ይችላሉ።
ረጅም ሰይፍ + መዶሻ፡- ረጂም ሰይፍን ከመዶሻ ጋር በማጣመር የጭራቁን ወሳኝ ክፍሎችን ለመቆራረጥ ሰይፉን ይጠቀሙ እና በመዶሻ መጨረስ ይችላሉ።
ታላቁ ሰይፍ + የአደን ቀንድ፡- ከፍተኛ ጥቃቶችን እያደረሱ ማበረታቻዎችን ያግኙ።
እነዚህ የጦር መሳሪያዎች የደረጃ ዝርዝር በፈለጉት የአጨዋወት ዘይቤ ላይ በመመስረት የትኞቹ የጦር መሳሪያዎች ላይ ማተኮር እንዳለቦት እገዛ ይሰጥዎታል!