icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

አስደሳች ዜና! አዲሱ የGTA 5 የፒሲ ዝማኔ ተለቋል! 

ግራንድ ቴፍት አውቶ 5 እ.ኤ.አ 2013 ከተለቀቀ ጀምሮ፣ የተለያዩ የኮንሶል ማሻሻያዎች የተደረጉለት ሲሆን፣ እ.ኤ.አ በ2022 ለPS5 እና Xbox Series X|S ኮንሶሎች የተሻሻለ እትም ተዘጋጅተውለት ነበር። አሁን ደግሞ፣ ከሶስት ዓመታት ጥበቃ በኋላ፣ የፒሲ ተጫዋቾች ይህንኑ ማሻሻያ "Enhanced Edition" በነጻ ሊያገኙ ነው!  

ቀደም ሲል ፒሲዎ ላይ GTA 5 ከነበረዎት፣ ይህን የተሻሻለ እትም ያለ ምንም ክፍያ ማውረድ ይችላሉ። ነገር ግን፣ አሮጌ ኮምፒውተር ያላቸው ተጫዋቾች "GTA V Legacy" ተብሎ ወደተሰየመው የመጀመሪያው ስሪት መመለስ ይችላሉ። ሆኖም ግን፤ በእነዚህ ሁለት ስሪቶች መካከል መጫወት የሚያስችል የክሮስ-ፕለይ አማራጭ አልተዘጋጀም። 

ይህ ማሻሻያ ከዚህ ቀደም ለኔክስት-ጂን ኮንሶሎች የተዘጋጁ አስደናቂ የጥራት እና የአፈጻጸም ቴክኒካል ማሻሻያዎችን ይዞ ይመጣል፡- 

  • Ray Tracing፦ አስደናቂ እና ተፈጥሯዊ ይዘት ያላቸው ብርሃኖች፣ ጥላዎች እና ነጸብራቆች። 

  • የአፈጻጸም ማሻሻያዎች፦ የተሻለ የጨዋታ ተሞክሮ የሚሰጡ AMD FSR (1 & 3) እና NVIDIA DLSS 3ን ይደግፋል። 

  • ፈጣን የመክፈቻ ቆይታ፦ SSD እና DirectStorage የሚያካተት በመሆኑ ጌሙ እስከሚከፍት ረጅም ጊዜ መጠበቅ አክትሞለታል። 

  • አስደናቂ ድምፅ፦ በአካል ከሚሰሟቸው ድምፆች ያልተናነስ ጥራት የሚያቀርብ Dolby Atmos። 

  • ከፍተኛ ጥራት እና ፍሬም ሬት፦ እጅግ ሰፋፊ የሆኑ ስክሪኖች ላይ በከፍተኛ ጥራት እና ፍሬም ሬት መጫወት የሚያስችል እንዲሆን ተደርጎ ቀርቧል። 

  • DualSense መቆጣጠሪያ፦ ተጫዋቾች ባለተጣጣሚ መቀስቀሻ DualSense መቆጣጠሪያን እና ባለሃፕቲክ ምላሽ ሰጪ እማራጮችን መጠቀም ይችላሉ። 

GTA ኦንላይን ላይ ምን አዲስ ነገር አለ? 

የባለ-ብዙ ተጫዋችቾች ሞድ አድናቂዎች አዳዲስ አስደሳች ማሻሻያዎችን ያገኛሉ፣ ከእነዚህም መካከል፡- 

  • Hao's Special Works (HSW)፦ ለአምስት አዳዲስ መኪኖች እና 20 ነባር ሞዴሎች ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው ተሽከርካሪዎችን ማሻሻያ አዲስ ጋራዥ። 

  • ልዩ ውድድሮች እና ዝግጅቶች፦ አዲስ የHSW ውድድሮች፣ ጊዜያዊ ሙከራዎች እና ፕሪሚየም ሙከራዎች። 

  • የGTA+ ምዝገባ፦ ፒሲ ላይ የሚገኝ አገልግሎት ሲሆን፣ በየወሩ ልዩ ሽልማቶችን እና ጥቅማጥቅሞችን ያገኛሉ። 

የፒሲ ተጫዋቾች GTA 6 እስከሚለቀቅ ድረስ በእነዚህ ማሻሻያዎች GTA 5ን ከመቼውም ጊዜ በላይ ማጣጠም ይችላሉ!  

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !