icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ኮል ኦፍ ዲውቲ ብላክ ኦፕስ 6፣ መቃብር ውስጥ የሚገኙ ድብቅ ተልዕኮዎችን እንዴት ማጠናቀቅ ይቻላል? 

ከጅምሩ፣ “The Tomb” የተሰኘው ዋና ተልዕኮ በርካታ አስቸጋሪ ተግዳሮቶችን የሚያካትት ሲሆን፣ “Pack-a-Punch” የሚባለውን ነገር በማንቃት ይጀምራል፤ ይህም የሙታን ከተማ የሆነውን “Citadel of the Dead” ክታብ ከመሬት በታች የሚገኘው ቤተ-መቅደስ ውስጥ ያለው አምድ ላይ ማስቀመጥን ይጠይቃል። ይህን ካጠናቀቁ በኋላ በአራቱም አቅጣጫዎች የተበተኑ አራት የተደበቁ ቅርሶችን (artifacts) ለመሰብሰብ ካርታውን ማሰስ ይጠበቅብዎታል። ማግኘት አስቸጋሪ ከሆነብዎ፣ “Death Perception” የሚባለውን ልዩ ችሎታ (perk) ለመጠቀም አያመንቱ፥ ነገሮችን በቀላሉ መለየት እንዲችሉ ይረዳዎታል። 

ሁሉንም ቅርሶች ሰብስበው ከጨረሱ በኋላ ዋናው ፈታኝ ጉዳይ አሁን ይጀምራል። ለቁጥር አስችጋሪ የሆኑ የዞምቢ መንጋዎችን (possessed zombies) መጋፈጥ ይኖርብዎታል። የመጀመሪያው ማዕበል ላይ “Mimic” ጋር የሚፋለሙ ሲሆን፣ ሁለተኛው ማዕበል ላይ ደግሞ “Doppelghast” ጋር ይፋለማሉ፣ ይህም ሊፈትንዎ ይችላል። በመጨረሻም፣ ሶስተኛው እና የመጨረሻው ማዕበል ላይ “Amalgamation” ጋር የሚያጋጭ ሲሆን ይሄ ከሁሉም የከፋ እና እጅግ አስቸጋሪው ነው። እነዚህን ፈተናዎች በብርታት እና በድል ከተወጡ በኋላ ሁለተኛው ፎቅ ላይ የሚገኘውን “Sentinel Artifact” በቅርሶቹ የሚለቀቁ ጨረሮችን በመጠቀም ማጥፋት ይጠበቅብዎታል። 

ይህን ፈተና መጨረስ ከቻሉ እንደ “The Tomb Calling Card”፣ ያሉ ለ“Ice Staff” የሚሆን ልዩ አልባስን (skin) እና ጌሙን መጫወትዎን ከቀጠሉ ማስከፈት የሚችሏቸው ጥቅማጥቅሞች ይኖራሉ። 

በረዶ ወርዋሪ ዘንግ (The Ice Staff) 

በዚህ ካርታ ላይ ካሉት በጣም ኃይለኛ መሳሪያዎች አንዱ የበረዶ ዘንግ ቢሆንም፣ ሆኖም ግን በቀላሉ የሚገኝ አይደለም። መሳሪያውን ራስዎ ለመስራት በቅድሚያ ካርታው ላይ ተበታትነው የሚገኙ ክፍሎችን በሙሉ ማግኘት ያኖርብዎታል። ሁሉንም ክፍሎች ሰብሰበው ከጨረሱ በኋላ ወደ ትጥቅ ማስቀመጫው (Arsenal) በመሄድ መገጣጠም ይችላሉ። ግን ይሄ ብቻ በቂ አይደለም፣ መሳሪያዎን የበለጠ ኃይለኛ ለማድረግ ማሻሻያ ማድረጊያዎችን ሊከፍቱልዎ የሚችሉ የተወሰኑ ተልዕኮዎችን መወጣት ይኖርብዎታል። 

ወርቃማው መከላከያ ትጥቅ (The Golden Armor) 

ወርቃማው መከላከያ ትጥቅ ሌላኛው ወሳኝ ኢስተር ኤግ (Easter egg) ነው። ካርታው ውስጥ ተበታትነው የሚገኙ የተደበቁ የኤተር ክሪስታሎችን (Aether Crystals) በመሰብሰብ ሊያገኙት የሚችሉ ሲሆን፣ ክሪስታሎቹን በተወሰነ በቅደም ተከተል በመሰባበር፥ የመከላከያ ትጥቁን ማግኘት ይችላሉ፣ ይህም ከፍተኛ ጥቅም ይሰጥዎታል። 

ድብቁ ሙዚቃ (Musical Easter Eggs) 

ልክ እንደ ብዙዎቹ የዞምቢ ካርታዎች፣ መቃብሩ "The Tomb" ውስጥ የተደበቁ ምስጢራዊ ዘፈኖች አሉ። እነዚህን ዘፈኖች ለመክፈት ካርታው ላይ ተበታትነው የሚገኙ ሶስት የዞምቢ ፕሉሺዎችን (zombie plushies) ማግኘት ያስፈልግዎታል። ዘፈኑ ለማጫወትም፣ የዞምቢ ፕሉሺዎቹን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ማንቃት ይጠበቅብዎታል። 

ድግምታዊው ሣጥን (The Cursed Chest) 

በመጨረሻም፣ ሊያስከፍቱት የሚገባ ልዩ ድግምታዊው ሣጥን አለ። ይህንን ለማድረግ ካርታው ላይ የሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ተበታትነው የሚገኙ ሩንሶችን (runes) መሰብሰብ አለብዎ። ሁሉንም ሩንሶች ከሰበሰቡ በኋላ ከመሬት በታች የሚገኘው ቤተ-መቅደስ ውስጥ የሚገኘው መሠዊያ ላይ ያስቀምጧቸው። ከዚያ ሆነው አንድ እንቆቅልሽ ይመጣል፣ እንቆቅልሹን መፍታት ከቻሉ ሣጥኑ ይከፈታል፣ ይህም አስደሳች ሽልማቶችን ያስገኝልዎታል። 

 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !