icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ማክዶናልድስ እና ማይንክራፍት የአጋርነት ስምምነት ፈፀሙ! 

የማይንክራፍት እና የማክዶናልድስ አድናቂዎች በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው አስደሳች አጋርነት ተጀምሯል! እ.ኤ.አ ኤፕሪል 2፣ 2025 ላይ "Minecraft: The Movie" የተሰኘው ፊልም መለቀቅን ምክንያት በማድረግ፣ ሁለቱ ትላልቅ ኩባንያዎች ለልጆችም ሆነ ጎልማሶች የሚመጥን ልዩ የማስተዋወቂያ ዘመቻ ይዘውላችሁ ቀርበዋል። እ.ኤ.አ ከማርች 25፣  2025 ጀምሮ ማክዶናልድስ ልዩ ጭብጥ ያላቸው ምግቦችን፣ ልዩ አሻንጉሊቶችን እና አዳዲስ ዲጂታል ይዘቶችን ያቀርባል። እነዚህ ልዩ እድሎች እንዳያመልጥዎ ማድረግ ያለብዎትን ነገር በዚህ መመሪያ እናሳውቅዎታለል! 

ይህ የማስተዋወቂያ ዘመቻ እ.ኤ.አ ማርች 25፣ 2025 የሚጀምር ሲሆን ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ በትክክል ባይታወቅም ለተወሰነ ጊዜ ብቻ እንደሚቆይ ተረጋግጧል። ስለዚህ ይህ ልዩ እድል እንዳያመልጥዎ መፍጠን ይኖርብዎታል! 

የሁሉንም ሰው የምግብ ፍላጎት ለማሟላት፣ ማክዶናልድስ ሁለት የተለያዩ ምግቦችን አዘጋጅቷል። የመጀመሪያው "Minecraft Movie Meal" ለአዋቂዎች ተብሎ የተዘጋጀ ሲሆን 9 የዶሮ ማክ-ነጌትስ (በመደበኛ ወይም በአትክልት አማራጭ)፣ ትልቅ ችፕስ፣ ትልቅ መጠጥ እንዲሁም አሻንጉሊትን ያካትታል። ዋጋቸው ገና ይፋ ባይገለጽም፣ ለህፃናት ተብሎ የተዘጋጀው ሁለተኛው አማራጭ "Minecraft Movie Happy Meal" በመደበኛው የHappy Meal ዋጋ ለሽያጭ የሚቀርብ ይሆናል። ይህ ምግብ ልዩ የሆነ የማይንክራፍት አሻንጉሊትን የሚያካተት በመሆኑ፣ ለወጣት አድናቂዎች እንደ ስጦታ፣ ለአዋቂዎች ደግሞ እንደ ተሰብሳቢ መሆን ይችላል። 

የማይንክራፍት አድናቂዎች እነዚህ ምግቦች አሻንጉሊቶችን እንደሚያካትቱ ሲያውቁ ደስተኛ እንደሚሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ለአዋቂዎች የተዘጋጁ እና ጌሙን መሰረት በማድረግ የተሰሩ እንደ የግሪሜስ እንቁላል (የማይንክራፍት ድራጎን እንቁላል)፣ ዞምቢ ሀምበርግላር እና ቢግ ማክ ክሪስታል ያሉ ስድስት አሻንጉሊቶች ይገኛሉ። ልጆችም አልተረሱም! ፊልሙም ሆነ ጌሙ ላይ የሚገኙ የብሎክ ዓለም እና የብሎክሄድ ገጸ-ባሕሪያትን የሚወክሉ 12 የተለያዩ አሻንጉሊቶች ተዘጋጅተውላቸዋል። እነዚህ አሻንጉሊቶች ስብስብዎን ለማስፋት ወይም ማይንክራፍትን በዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ላይ ለማካተት ተመራጭ ናቸው። 

ይሄ ብቻ አይደለም! ይህን ተሞክሮ የበለጠ አስደሳች ለማድረግ፣ ማክዶናልድስ አዳዲስ የምግብ አቅርቦቶችን ይጀምራል። ማይንክራፍት ውስጥ የሚገኘውው የኔዘር ዓለምን መሰረት በማድረግ የተዘጋጀው Nether Flame sauce የሚገኝ ሲሆን፣ ይህ ቅመም ከካየን በርበሬ፣ ቀይ በርበሬ እና ጣፋጭ የአፕሪኮት ጣዕም ጋር ተቀላቅሎ የተሰራ በመሆኑ የሚያቃጥሉ ምግቦችን ለሚወዱ ሰዎች አስደሳች እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። በተጨማሪም፣ የጌሙን ኩኪዎች መሰረት ተደርጎ የተሰራው ማክፍለሪ ኩኪስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀርቧል። ይህ ጣፋጭ ምግብ ከምግብ አማራጮቹ ውጭ የሚገኝ ሲሆን በማይንክራፍት እየተዝናኑ አፍዎ ላይ ጣል እያደረጉ ለመደሰት ተመራጭ ነው። 

ማክዶናልድስ እና ማይንክራፍት በዚሁ አላበቁም! እያንዳንዱ የአዋቂዎች ምግብ ላይ የሚገኙ አሻንጉሊቶች ስካን ሊደረጉ የሚችሉ ልዩ ኮድን የያዙ ካርዶችን ያካተታሉ። ተጫዋቾች ይህን ኮድ በመጠቀም በማይንክራፍት (ቤድሮክ እትም) መደብር ውስጥ ልዩ ገጸ-ባህሪዎችን እንዲሁም ልዩ የማክዶናልድ ተጨማሪ ጥቅሎችን ማግኘት ይችላሉ። የHappy Meal አሻንጉሊቶችን በተመለከተ፣ ማክዶናልድን መሰረት በማድረግ የተሰራ ማይንክራፍት ውስጥ የሚገኝ ዲጂታል ጌም ተልዕኮን ማጠናቀቅ ያስችሉዎታል። ይህም ይበልጥ ተሞክሮውን የበለጠ አስደሳች እና መሳጭ ያደርገዋል! 

 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !