
ካንዲ ክራሽ ሳጋን ኮምፒውተርዎ ላይ ጭነው ትልቅ ስክሪን ላይ በነፃ መኮምኮም ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ የምስራች፣ የሚጠቀሙት ዊንዶውስ 10 ይሁን ወይም 11 ካንዲ ክራሽን ኮምፒውተርዎ ላይ መጫንና መጫወት የሚችሉበት በርካታ መንገዶች አሉ። ካንዲ ክራሽን እንዴት ኮምፒውተርዎ ላይ መጫን እና መጫወት የሚችሉባቸውን መንገዶች ቀጥሎ በዝርዝር ያገኛሉ።
ካንዲ ክራሽ በዋናነት ለሞባይል የተዘጋጀ ጌም ቢሆንም፣ ኮምፒውተር ላይ መጫወት ልዩ ጥቅሞችን ይሰጣል፡-
ትልቅ ስክሪን፡- ያማሩ ግራፊክሶቹ እና አኒሜሽኖቹ ሰፊ ስክሪኖች ላይ ሲታዩ እጅግ ማራኪ ናቸው።
የበለጠ ምቹ፡- ከተች ስክሪን ይልቅ፣ ማውዝ ወይም ኪቦርድን በመጠቀም መጫወት ይበልጥ ምቾትን ይሰጣል።
ተመሳሳይ ሂደት፡- ወደ ፌስቡክ ወይም ኪንግስ አካውንትዎ በመግባት፣ ጌሙን ድጋሚ ማስጀመር ያይጠበቅብዎ የተለያዩ መሳሪያዎች ላይ ሂደትዎን መልሰው ማግኘት እና መጫወት ይችላሉ።
በኮምፒውተር የመጫወት ጥቅሙን ካወቁ፣ አሁን ደግሞ በቀላሉ እንዴት መጫን እንደሚችሉ እንመልከት።
የሚጠቀሙት ዊንዶውስ 10 ወይም 11 ከሆነ ቀላሉ ማውረጃ ዘዴ ማይክሮሶፍት ስቶር ነው።
ኮምፒውተርዎ ላይ የማይክሮሶፍት ስቶር መተግበሪያን ይክፈቱ (taskbarን ወይም Start menuን በመጠቀም)።
የፍለጋ ሣጥኑ ውስጥ ካንዲ ክራሽ ሳጋ በማለት ይፈልጉ።
"Get" ወይም "Install" የሚለውን ይጫኑ።
ጭነው ከጨረሱ በኋላ ጌሙን Start menu ውስጥ በመግባት ይክፈቱ።
የጌሙን የሞባይል ስሪት በመጠቀም ቀጥታ ኮምፒውተርዎ ላይ መጫወት ከፈለጉ፣ አንድሮይድ ኢሙሌተሮች ጥሩ አማራጭ ናቸው። በጣም ታዋቂ ከሆኑት አማራጮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-
Bluestacks፦ ለሞባይል ጌሞች ተብሎ የተዘጋጀ ታዋቂ ኢሙሌተር ነው።
MEmu፦ ለመጠቀም እና ለማዘጋጀት እጅግ ቀላል ነው።
LDPlayer፦ ትልቅ አቅም ለሚጠይቁ ጌሞች የሚሆን ቀልጣፋ እና ተስማሚ ኢሙሌተር ነው።
ኢሙሌተርን በመጠቀም ካንዲ ክራሽን መጫኛ ሂደቶች፡-
Bluestacksን (ወይም ሌላ ኢሙሌተር) ድረ-ገጽ ውስጥ በመግባት ያውርዱና ይጫኑ።
ኢሙሌተሩን ይክፈቱና የጎግል አካውንትዎን በመጠቀም ወደ ጎግል ፕለይ ስቶር ይግቡ።
ካንዲ ክራሽ ሳጋን ያውርዱ እና ይጫኑት።
ጌሙን ያስጀምሩና ማውዝዎን እና ኪቦርድዎን በመጠቀም ጨዋታዎን ይጀምሩ።
ጌም-ሉፕ በTencent የተዘጋጀ ሲሆን፣ የሞባይል ጌምችን ፒሲዎ ላይ መጫወት የሚያስችልዎ ኢሙሌተር ነው። ካንዲ ክራሽ ሳጋን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ጌሞችን ያቀርባል።
በGameLoop በኩል መጫኛ ሂደቶች፡-
ወደ ድረ-ገጹ በመግባት GameLoopን ያውርዱ።
መተግበሪያውን ይጫኑና ይክፈቱ።
የፍለጋ ሣጥኑ ውስጥ ካንዲ ክራሽ ሳጋ ብለው በመፈለግ፣ ያውርዱት።
ተጭኖ ካለቀ በኋላ ጌሙን ከፍተው መጫወት መጀመር ይችላሉ።