
በጄራርድ ፒኬ የተፈጠረው፣ የመጀመሪያው የኪንግስ ሊግ ፈረንሳይ ውድድር እ.ኤ.አ አፕሪል 6 2025 ተጀምሮ እስከ ሜይ 25 2025 ድረስ ይቆያል። ይህ አዝናኝ የ7ለ7 የእግር ኳስ ውድድር ስምንት ቡድኖችን ያቀፈ ሲሆን እያንዳንዱም ቡድን በስፖርት ወይም በቀጥታ ስርጭት ዘርፍ ላይ የሚገኙ ዝነኛ ሰዎች መሪነት ልዩ እና ሳምንታዊ ውድድሮችን ያቀርባል።
መደበኛ የውድድር ዘመን፡- ጨዋታዎች እ.ኤ.አ ከኣፕሪል 6 እስከ ሜይ 5 ድረስ እሁድ እሁድ ይካሄዳሉ።
የማጣሪያ ጨዋታዎች፡- እ.ኤ.አ ከሜይ 25 እስከ ሜይ 8 ድርስ የመጀመሪያው ሻምፒዮን ይሸለማል።
የኪንግስ የዓለም ዋንጫ፡- ከፍተኛዎቹ 4 ቡድኖች በወርሃ ጁን ፈረንሳይ ላይ የሚካሄደው የኪንግስ የዓለም ዋንጫ ውድድር ላይ ይሳተፋሉ።
በቀጥታ ስርጭት አቅራቢዎች፣ በቡድን ፕሬዚዳንቶች እና በተመልካቾች በመታጀብ፣ ሁሉም ጨዋታዎች ትዊች እና M6+ ላይ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል።
የውድድሩ መጀመሪያ ቀን - እሑድ አፕሪል 6
16:00 – ዎልፍ ፓክ ኤፍ.ሲ vs ፓናማ ኦል ስታርዝ
17:00 – F2R vs ካራሱ
18:00 – ዩናይት3ድ vs ጄኔሬሽን ሰቨን
19:00 – ኤፍ.ሲ ሲልሚ vs 360 ኔሽን
በቀን 2-5 ባሉ ቀናት የሚደረጉ ተጨማሪ ጨዋታዎች በየሳምንቱ ይገለፃሉ፡-
ቀን 2 - እሁድ፣ አፕሪል 13
ቀን 3 - እሁድ፣ አፕሪል 20
ቀን 4 - እሁድ፣ አፕሪል 27
ቀን 5 - እሁድ፣ አፕሪል 4
ቡድኖች እና መሪዎቻቸው
እያንዳንዱ ቡድን ስፖርት ወይም መዝናኛ ኢንዱስትሪ ውስጥ በሚገኙ ታዋቂ ሰዎች ይመራሉ፡
360 ኔሽን፡- ቹአሜኒ፣ ኩንዴ፣ ማይኛን፣ ኮኔ፣ እምቤሞ፣ ማዩሉ
F2R፦ አሜንማቱ፣ ናስሪ፣ ሜኔዝ
ኤፍ.ሲ ሲልሚ፡- ዶሚንጎ
ጄኔሬሽን ሰቨን፡- ሚቹ
ካራሱ፡- ካሜቶ
ፓናም ኦል ስታርዝ፡- ፉት
ዩናይት3ድ፡- ስኩዚ፣ ጂልሲ፣ ማክስሚ ባያጂ
ዎልፍ ፓክ ኤፍ.ሲ፡- አዲል ራሚ
ቡድኖቹ የተቋቋሙት እ.ኤ.አ ማርች 24 በተካሄደው የምልመላ ስነ-ስርዓት ሲሆን፣ ከ80 በላይ ተጫዋቾችም ተሳትፈው ነበር። በውድድሩ ወቅት እያንዳንዱ ቡድኖች 3 የዋይልድካርድ ተጫዋቾችን መጨመር ይችላሉ።
የኪንግስ ሊግ ልዩ ሕግጋቶች
ጨዋታዎች ሁለት የ20 ደቂቃ ክፍለ-ጊዜዎች አሏቸው።
በሁለተኛው አጋማሽ፣ ሁሉም አሰልጣኞች ምስጢራዊ ካርዶችን (እንደ፦ ድርብ ጎል ወይም ነፃ የቅጣት ምት) መጫወት ይችላሉ። ይህም እያንዳንዱን ጨዋታ ያልተጠበቀ እና አስደሳች ያደርገዋል!
1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ቡድኖች በቀጥታ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ያልፋሉ።
ከ3ኛ–5ኛ ደረጃ የሚገኙ ቡድኖች ለሩብ ፍጻሜ ይወዳደራሉ።
6ኛ እና 7ኛ ደረጃ የሚገኙ ቡድኖች የመጨረሻውን የማጣሪያ ጨዋታ ያደርጋሉ።
ታላቁ የፍጻሜ ውድድር እ.ኤ.አ እሁድ ሜይ 25 ይካሄዳል።
ኪንግስ ሊግ ሳምንታዊ መዝናኛን፣ በአይነታቸው ልዩ እና እልህ አስጨራሽ ውድድሮችን እነሆ ሊል በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ብቻ ነው የሚቀሩት። ድጋፍዎ ለ#TeamMichou ይሁን ለ#TeamAmine፣ ወይም ቀንደኛ የእግር ኳስ ደጋፊ ይሁኑ፤ እስከ ሜይ ማገባደጃ ድረስ የሚቆዩት ውድድሮች አንጀትዎን እንደሚያርስዎት ምንም ጥርጥር የለውም!