icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ኪንግስ ሊግ ፈረንሳይ 2025፡ ቲኬቶች፣ የውድድር ቀናት እና ማወቅ ያለብዎ ጉዳዮች! 

በጄራርድ ፒኬ የሚዘጋጀው፣ 7ለ7 የሚደረገው የእግር ኳስ ውድድር ኪንግስ ሊግ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሀገረ ፈረንሳይ መቷል! ይህ አስደሳች ውድድር እንደ አሚን፣ አዲል ራሚ እና ስኩዊዚ ያሉ ዝነኛ የቡድን መሪዎችን እና ልዩ ህጎችን እና አፍ የሚያስከፍቱ ውድድሮችን ያቀርባል። 

ቀናት እና ቦታዎች 

  • ጨዋታዎች ከፓሪስ አቅራቢ የሚገኘው ቪልፒንቴ ፓርክ ዴ ኤክስፖዚሽን አዳራሽ 8 ውስጥ፣ እ.ኤ.አ ከኣፕሪል 6 እስከ ሜይ 5 ድረስ እሁድ እሁድ ይካሄዳሉ። ይህ ሰፊ ስቴዲዬም በሺዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾችን ለማስተናገድ ምቹ ነው። 

  • በየሳምንቱ ስምንት ቡድኖች የሚጋጠሙ ሲሆን፣ የመደበኛ የውድድር ዘመኑ ላይ እስከ ደረጃ አራት ያሉ ምርጥ ቡድኖች የማጣሪያ ጨዋታዎችን ሜይ 8 ላይ የሚያደርጉ ሲሆን ፣ ታላቁ የፍጻሜ ውድድር ደግሞ ሜይ 25 ይካሄዳል። 

ትኬቶችን እንዴት ማግኘት ይቻላል? 

  • ትኬቶችን kingsleague.pro ድረ-ገጽ ላይ ቀጥታ መግዛት ይችላሉ። 

  • ቅናሾችን እና ፓኬጆችን ለማግኘት እንደ Ticketmaster እና Fnac Spectacles ያሉ ሌሎች ፕላትፎርሞችን ይጎብኙ። 

  • የጨዋታው ቀን ላይ box office ቪልፒንቴ ላይ ማግኘት ይችላሉ፣ ነገር ግን ትኬቶች በፍጥነት ስለሚያልቁ፣ አስቀድመው ቦታ ያስይዙ። 

የቲኬቶች መሸጫ ዋጋ 

የትኬቶች ዋጋ እንደሚፈልጉት መቀመጫ እና ሁኔታ ይለያያል፣ ካሉት አማራጮች ውስጥ፦ 

  • መደበኛ፡- ከ €15 ጅምሮ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፣ ከጓደኞችዎ ወይም ቤተሰብዎችዎ ጋር ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ ጥሩ አማራጭ ነው። 

  • ፕሪሚዪም፡- ከ30–50 ዩሮ ድረስ የሚሸጥ ሲሆን፣ ለእይታ የሚያመች የተሻለ ቦታ ለማግኘት እና አንዳንድ ጥቅማጥቅሞች ያካተታል።። 

  • ቪ.አይ.ፒ፡- ከ100 ዩሮ ጅምሮ የሚሸጥ ሲሆን፣ ከመድረክ በስተጀርባ መዳረሻን፣ ዝነኛ የቡድን መሪዎች ጋር መገናኘትን እና ከሜዳው አጠገብ መቀመጫዎችን ያካትታል። 

  • የውድድር ዘመን ምዝገባ፡- እያንዳንዱን ግጥሚያ መከታተል የሚያስችልዎ የላቀ አማራጭ። 

ሊያመልጥዎ አይገባም! 

ኪንግስ ሊግ ከእግር ኳስ በላይ ነው! የሚከተሉትን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት አስደሳች ተሞክሮ ነው፡- 

  • የተለመዱ ህጎችን ወደ ኋላ በመተው እንደ፣ ድንገተኛ ካርዶች እና በጨዋታ መኃል የሚደረጉ ስልታዊ ለውጦች ያሉ ልዩ ልዩ ህጎች። 

  • እንደ አሚን፣ ስኩዊዚ እና አዲል ራሚ ያሉ ኮከብ ተጫዋቾች እና የቡድን ፕሬዝዳንቶች። 

  • ትርኢቶች፣ ተገባዥ ዝነኛ እንግዶች፣ የምግብ መሸጫዎች እና የሚጋባ አስደናቂ ድባብ። 

ይህ አስደናቂ ዝግጅት ሊያመልጥዎ አይገባም! ቢያሻዎት ኦንላይን ወይም በአካል በመገኘት የዚህ አስደናቂ ክስተት ተካፋይ ይሁኑ። 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !