
ሬማች የእርስዎን ስራ እንዲሰራልዎ AIን የሚወክሉበት ጌም አይደለም። እያንዳንዱ የሚያደርጉት ቅብብል፣ የመከላከል ሙከራ በእርስዎ ብቃት ላይ ብቻ የተመሰረተ እና ምንም ዓይነት እርዳታ የማያገኙበት፣ በጊዜ አጠቃቀምዎ እና ስልትዎ ላይ የተመሠረተ ጌም ነው። አነጣጥረው ለመምታት ካሜራዎን በትክክል ማስቀመጥ እና ርቀቱን ግመት ውስጥ በማስገባት ኃይሉን ማስተካከል ይኖርብዎታል፣ ለአጭር ኳስ ቆልፉን በሰሱ መጫን፣ ለአብዛኛዎቹ ቅብብሎች ጫን አድርገው መልቀቅ እና ኃይለኛ ምቶችን ለማድረግ ወይም ለማሻማት በረጅሙ መጫን ያስፈልጋል። መጀመሪያ ላይ ቀላል የሆኑ ነገሮችን ሊሳሳቱ ይችላሉ፣ ሆኖም ግን አይጨነቁ፣ ሁሉንም በልምምድ ያመጡታል።
በመከላከል ረገድ ትልቁ ሊያስታውሱት የሚገባ ነገር በግዴለሽነት መንቀሳቀስ ማቆምን ነው። በተቃራኒ ቡድን የተመቱ ኳሶችን ለመከላከል እና የመቀባበያ መንገዶችን ለመዝጋት ጥሩ የተከላካይ አሰላለፍ መመደብ እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው። ሌላው መንሸራተት (Tackle) ሲሆን፣ ይህም በፍጥነት የሚሮጡ የተቃራኒ ቡድን ተጫዋቾችን ለመጥለፍ ይጠቅምዎታል፣ የቁም ሸርታቴ ደግሞ ደህንነቱ የተጠበቀ ቢሆንም ቶሎ አቅምዎን ያሟጥጣል። ትክክለኛው ስልት የተቃራኒ ቡድን ተጫዋቾችን ሳይጠልፉ ጫና ለመፍጠር የመከላከያ አቋም ቁልፍን (defensive stance button) ይጠቀሙ።
ኳሱ በቁጥጥርዎ ስር ሲሆን ዓይኖች ሁሉ እርስዎ ላይ መሆኑን ያስታውሱ። ስለዚህ ለብቻዎ መጫወትን ያቁሙ እና ከቡድን አጋሮችዎ ጋር በመቀናጀት ይጫወቱ። ኳሰን ማጣጠፍን ጠንካራ የሆኑ ተከላካዮች ላይ ብቻ ይጠቀሙ፣ እና ከሸርታቴ ሙከራዎች ራስዎን ለማዳን ደግሞ የrainbow flick ዘዴን ይጠቀሙ። ከኳስ ውጪ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች፣ እርዳታዎች እና የማይገመቱ መሆን አለባቸው። ከሁሉም በላይ ደግሞ ኳሱን ያቀብሉ! ከቡድን አጋሮችዎ ጋር ኳስን መቀባበል እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው። ስለ offside ሳይጨነቁ ኳሶችን በመሬት ማቀበል፣ ማሻማት እና አንድ-ሁለት ቅብብሎችን መጠቀም ይችላሉ። ቀለል አድርገው እና በቅልጥፍና ከተጫወቱ ድልን መቀዳጀት ይችላሉ።
ሁሌ ሊያታውሱት የሚገባ ነገር ቢኖር ሪማች የግል ጨዋታ አይደለም። የፈለገ ብቃት ቢኖርዎ፣ ቡድንዎ ጋር በቅንጅት ካልተጫወቱ ድል ከጎንዎ አትሆንም። ስለዚህ ከጓደኞችዎ ጋር በመሆን ስለተቃራኒው ቡድን ድክመቶች እና ስልቶች ይነጋገሩ። ሁልጊዜ ተመሳሳይ ስልት የሚጠቀም ወይም ብቻውን የሚጫወት ሰው በደንብ በተደራጀ ቡድን ጫና ይደርስበታል። ድል በቅንጅት ከሚጫወቱ ቡድኖች ጋር ብቻ ናት።
እንዲሁም ጉልበትዎን እንዴት መቆጠብ እንደሚችሉ ማጥናት ይኖርብዎታል። ያለማቋረጥ የሚሮጡ ከሆነ ቶሎ ይደክሙ፣ እና ወሳኝ ሰዓት ላይ መበላሸት የሌለበት እድል ሊያባክኑ ይችላሉ። ጉልበትዎን ቁልፍ ለሆኑ ሁኔታዎ በመቆጠብ፣ ትክክለኛው ጊዜ ላይ ይጠቀሙበት። ሰዓትንም በተመለከተ ቀድመው እድሎችዎን ለመጠቀም ይሞክሩ፣ ነገር ግን አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ በተለይ ደግሞ በመጨረሻዎቹ ሰከንዶች እንዴት መቀዝቀዝ እና መፍጠን እንዳለብዎት ይወቁ።
በመጨረሻም የግብ ጠባቂ ጉዳይ ሲሆን፣ ግብ ጠባቂውን የሚቆጣጠረው AI ሳይሆን፣ እውነተኛ ተጫዋች ነው። ስለዚህ እያንዳንዱ ሙከራ በውጥረት የተሞላ ነው። ግብ ጠባቂው ከሳጥኑ ውጭ ያልተገደበ ጉልበት ስላለው፣ የማጽዳት ሚናን እንዲጫወቱ እና ልዩ የመልሶ ጥቃት እንዲያደርጉ ያስችልዎታል። ጨዋታውን በደንብ ከተረዱት፣ ጊዜዎን በትክክል ከተጠቀሙ እና አደረጃጀቱ ላይ በአግባቡ ከተሳተፉ ግጥሚያው ላይ ትልቅ ተጽዕኖ መፍጠር ይችላሉ።