
ሰላም ቤተሰቦች! InZOI ላይ Error 62003 ራስ ምታት ሆኖብዎታል? አይጨነቁ!፣ ይሄ ችግር በተደጋጋሚ የሚከሰት ሲሆን በተለይ ደግሞ Steam አካውንታችሁን ከKRAFTON ID ጋር ለማገናኘት ወይም ሽልማቶችን ከTwitch ወይም CHZZK ለመቀበል ስትሞክሩ የሚከሰት ሲሆን፣ ይህም ከጌሙ እንዲታገዱ ይዳርግዎታል። እንደ እድል ሆኖ፣ በፍጥነት ችግሩን በመቅረፍ በሰላም ጨዋታወን መቀጠል የሚችሉባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ።
ብዙውን ጊዜ፣ ይሄ ብልሽት በአካውንቶች መካከል በሚፈጠሩ የግንኙነት ወይም ያለመመሳሰል (synchronization) ችግሮች የሚከሰት ነው። ይህም የሚሆነው ወይ የSteam አካውንትዎ በአግባቡ አልተገናኘም፣ ወይም የማረጋገጫ ቶክኑ (authentication token) ጊዜው አልፎበታል፣ ወይም ደግሞ እንደ Twitch ያሉ ፕላትፎርሞች እንደገና መገናኘት ሲኖርባቸው ነው። ከዚህ በፊት ብልሽቱ ዴኑቮ (Denuvo) በተባለ የጸረ-ቫይረስ ሲስተም (anti-piracy system) ምክንያት ይከሰት የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን ከአዲሱ ቅዲ ሙሉ በሙሉ እንዲወገድ ተደርጓል።
በቅድሚያ ወደ InZOI አካውንት አስተዳደር ገጽ ወይም በቀጥታ ወደ Drops event page ይሂዱ። በመቀጠል የSteam አካውንትዎ ከKRAFTON ID ጋር በትክክል መገናኘቱን ያረጋግጡ፣ እንዲሁም Twitch ወይም CHZZK በአግባቡ እየሰሩ መሆናቸውን ያረጋግጡ። ከሁለት አንደኛቸው ወይም ሁለቱም በአግባቡ እየሰሩ ካልሆነ፣ ያቋርጧቸው እና በድጋሚ አካውንትዎ ጋር ያገናኟቸው።
ችግሩ ጊዜ ባለፈበት ቶከን ምክንያት ከሆነ የተከሰተው፣ ወደ KRAFTON ID ገጽዎ በመሄድ ሁሉንም እንደገና ያገናኙ። ከፒሲ ይልቅ የሞባይል መተግበሪያው ላይ የተሻለ ስለሚሰራ፣ ስልክዎን በመጠቀም ሽልማቶችዎን ለመውሰድ ይሞክሩ።
ሌላው ጉዳይ፣ ግራፊክስ ድራይቨሮችን (graphics drivers) ማዘመንዎን ያረጋግጡ። ጊዜ ያለፈባቸው ድራይቨሮች የግንኙነት መቋረጥ ወይም ግራ የሚያጋቡ ብልሽቶችን ሊያስከትሉ ይችላሉ። እንዲሁም ኮምፒውተርዎ የጌሙን መስፈርቶች (VRAM፣ specs፣ ወዘተ) የሚያሟላ መሆኑን ለማረጋገጥ Can You Run It እና መሰል ድረ-ገፆችን በመጠቀም ማረጋገጥ ይችላሉ።
አሁንም ብልሽቱ እንዳለ ነው? Steam ሊረዳችሁ ይችላል። ላይብረሪያችሁ ውስጥ InZOI ላይ Right-click ያድርጉ፣ Properties > Installed Files የሚለውን ይምረጡ፣ እና Verify integrity of game files የሚለውን ይጫኑ። አንዳንድ ጊዜ አንድ የተበላሸ ፋይል ካለ ሁሉንም ሊያበላሽ ይችላል።
ከላይ የዘረዘርናቸው ዘዴዎች መፍትሄ ካላመጡ የመጨረሻው አማራጭ፤ የጌሙን የሙከራ ቅጂ (demo) ያጥፉት (uninstall) እና በድጋሚ ይጫኑት። ይህ ከባድ ውሳኔ ቢሆንም፣ ሁሉንም ነገር ወደ ነበረበት አቋም በመመለስ ችግሩን ይፈታልዎታል።
መልካም የጨዋታ ጊዜ!