
በሲፉ እና አብዞልቨር ታላቅ ዝናን የተቀዳጀው የፈረንሳይ ስቱዲዮ ስሎክላፕ የእግር ኳስ ጌም አፍቃሪያንን ልብ የሚያርስ ሪማች የተሰኘውን የእግር ኳስ ጌም እ.ኤ.አ. ጁን 19 2025 በፒሲ፣ ፒኤስ5 እና ኤክስቦክስ ሲሪየስ ላይ ለመልቀቅ ቀጠሮ ይዟል። በስታቲስቲክስ እና በሜኑዎች የተጨናነቁ ኋላቀር ጌሞች ተማረው ከነበረ፣ ይህ ፈጣን እና በፉክክር የተሞላ ጌም ተወዳጅ ምርጫዎ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም።
5v5 ግጥሚያዎች፦ አንድ ቡድን ውስጥ 5 ተጫዋቾች ያሉ ሲሆን እርስዎ የሚቆጣጠሩት አንድ ተጫዋች ብቻ ነው። ይህም እያንዳንዱን የኳስ ቅብብል፣ ምት እና ነጠቃ ተሞክሮ ተለዋዋጭ እና እውነታኛ ስሜት እንዲኖረው ያደርገዋል።
ሙሉ በሙሉ ማንዋል፦ ምንም አቅም መጨመሪያ፣ ምንም ራስ-ሰር እንቅስቃሴዎች የሉም። ሁሉም ነገር ባለዎት ችሎታ፣ ብቃት እና ከቡድን አጋሮችዎ ጋር ባለዎት ቅንጅት ላይ የተመሰረተ ነው።
የሶስተኛ ሰው እይታን (third-person view)፦ የሚጠቀም ሲሆን፣ እያንዳንዱ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ጊዜን እና ስልትን ያማከሉ መሆን አለባቸው።
ምንም ባህላዊ የእግር ኳስ ህጎች የሉም፦ ምንም ጥፋት፣ ምንም Off-side፣ ምንም VAR ነገር የለም! ያለማቋረጥ የሚደረጉ ጥረቶች ብቻ።
ጨዋታውን በተመለከተ፣ የአርኬድ ይዘት ያለው ሲሆን፣ የምት ሲስተሙ የኳስ ኃይልን፣ ሽክርክሪትን እና አቅጣጫን ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠሩ ያስችልዎታል። ቀስ አድርገው መምታት፣ በረዥሙ ማቀበል ወይም ጠመዝማዛ ምት ማድረግ ይችላሉ። ፊዚክስ፣ አስደናቂ አኒሜሽኖች እና የቡድን መስተጋብሮች ላይ ትኩረት በመስጠት አዝናኝ እና ቴክኒካል ጥልቀትን በሚያስደንቅ ሁኔታ ያቀርባል።
ሪማች ተራ መዝናኛ ጌም ብቻ አይደለም፣ ውድድርሮች እና በፉክክር የተሞላ ጌም ነው። በደረጃ ሠንጠረዦች፣ መደበኛ ውድድሮች እና አዳዲስ ይዘቶችን የሚያቀርብ ሲዝናን ሲስተሞችን ያካተታል። እንዲሁም ለማሸነፍ የሚደረጉ ክፍያዎች፣ ኢ-ፍትሃዊ ጥቃቅን ግብይቶች የሉም። በችሎታ እና ብቃት ላይ የተመሰረቱ ፍትሐዊ ጌም ነው። ስለዚህ፣ ለማሸነፍ የሚደረጉ ክፍያዎች የሰለቻቸው የኢ-ስፖርትስ አድናቂዎች እና ተጫዋቾች ምርጫቸው እደሚያደርጉት ምንም ጥርጥር የለውም።