
InZOI ላይ ድመት ማሳደግ ይፈልጋሉ? ለጊዜው ይህ አማራጭ ያልተጀመረ ቢሆንም፣ የዚህ እድል ተጠቃሚ የሚሆኑበት ቀን ግን እጅግ ቅርብ ነው! ምንም እንኳን የድመት ዛፎች፣ ሳህኖች፣ አሻንጉሊቶች… እና ሌሎች ከድመት ጋር የተያያዙ ነገሮች (Build Mode) ውስጥ ቢኖሩም አሁን ላይ ያለው እትም ላይ ድመቶችን ማሳደግ የሚችሉበት አማራጭ አልተካተተም።
ግን አያስቡ! የKrafton አዘጋጆች ድመቶች እና ውሾች በቅርቡ እንደሚካተቱ አረጋግጠዋል። ይህ በተጫዋች ማህበረሰቡ በተደጋጋሚ ከሚጠየቁ ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ በመሆኑ፣ ይሆናል አይሆንም ሳይሆን ጥያቄው፣ መቼ ነው የሚለው ነው።
ተጫዋቾች ድመቶች በጉጉት በመጠበቅ ላይ የሚገኙት ጌሙን የበለጠ ነብስ ስለሚዘሩበት ነው። ድመትዎን መመገብ፣ መጫወት፣ መንከባከብ አልፎ ተርፎም እንደፍላጎትዎ ማስጌጥ፣ ያስቡት ምን ያህል አስደሳች እንደሚሆን! እንደ Krafton ገለጻ ከሆነ፣ ከተማው ውስጥ የሚገኙ አሳዳጊ የሌላቸው የጠፉ ድመቶችን ማግኘት እና ማሳደግ ይችላሉ፣ ይህም በInZOI ዓለም ላይ የሚኖርዎትን ቆይታ ይበልጥ አስደሳች ያደርገዋል።
ቤትዎ ውስጥ ምቹ ቦታ ፣ የምግብ ሳህኖች፣ መፀዳጃ ሣጥኖች፣ መጫወቻዎች… ሁሉም (Build Mode) ውስጥ የሚገኙ “የቤት እንስሳት” ክፍል ውስጥ የሚገኙ ነገሮችን በማዘጋጀት ይህ ትልቅ ዜና እውን እስከሚሆን ድረስ፣ ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረጉ መጠበቅ ይችላሉ።
ቅድመ-ዝግጅቱ ጋር ኣብረው ሊተገበሯቸው የሚገቡ ተጫማሪ ጉዳዮች፡-
መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርስዎት፣ ድረ-ገጹን፣ የዲስኮርድ ገጽን፣ እና ማህበራዊ ሚዲያዎችን ይከታተሉ።
አዘጋጆች የማህበረሰቡን አስተያየቶች ስለሚቀበሉ፣ የማህበረሰብ ውይይቶችን ይቀላቀሉ።
ለወደፊት ድመትዎ ምቹ የሆነ ትንሽየ ቦታ ያዘጋጁ።
ስለ መጪው ሲስተም አስቀድመን የምናውቀው፡-
በከተማው ውስጥ የሚያገኟቸውን የጠፉ እና አሳዳጊ የሊላቸው ድመቶችን ማሳደግ ይችላሉ።
እያንዳንዱን የቤት እንስሳት እንደፍላቶትዎ ሊያስተካክሏቸው ወይም ሊያስጌጧቸው ይችላሉ።
ሰፊ የመጫወቻ፣ የእንክብካቤ፣ የመተቃቀፊያ ጊዜ …
የቤት እንስሳቱ በስሜቶቻቸው እና ፍላጎቶቻቸው አማካኝነት ስለ Zoi ህይወትዎ ምላሽ ይሰጣሉ።