icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

የGTA 6 መውጫ ቀን ወደ 2026 ተራዘመ 

Grand Theft Auto VI እ.ኤ.አ በ2025 አይለቀቅም። Rockstar Games እ.ኤ.አ ሜይ 2 ላይ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን የGTA 6 መውጫ ቀን እ.ኤ.አ ወደ ሜይ 26፣ 2026 እንዳዘዋወረ በይፋ አሳውቋል። ለአንድ ዓመት መራዘሙ የቪዲዮ ጌም ማህበረሰቡን እና ኢንዱስትሪውን አስደንግጧል፣ ሆኖም ግን ስቱዲዮው በተጨዋቾች ዘንድ ያለውን ጉጉት የሚመጥን ነገር ይዘው መምጣት ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ ባለመሆኑ፣ በቂ ዝግጅት ለማድረግ በማሰብ ውሳኔውን እንደወሰኑ አሳውቀዋል። 

እ.ኤ.አ ዲሴምበር 2023 ላይ የመጀመሪያው ማስታወቂያ ቪዲዮ ከተለቀቀ በኋላ የተለያዩ ግምታዊ አስተያየቶች ተሰጥተው ነበር። እንዲሁም Take-Two Interactive እ.ኤ.አ. በ2025 መገባደጃ ላይ እንደሚለቀቅ በተደጋጋሚ ያረጋገጠ ቢሆንም፣ ባለፉት ሳምንታት በተጫዋቾች ዘንድ ከፍተኛ ጥርጣሬዎች ተጭረው ነበር። ይህንንም አስመልክቶ Rockstar የመራዘሙን ጉዳይ ግልጽ በሆነ መንገድ ይፋ አድርጓል። 

ይህን አስመልክቶ Rockstar ምን አለ? 

ስቱዲዮው GTA VI የቪዲዮ ጌም ደረጃን ከፍ ማድረግ ትልቁ ግቡ መሆኑን በአፅንዖት የገለጸ ሲሆን፣ ከዚህ በፊት የለቀቃቸው ክፍሎች ሁልጊዜ መመዘኛ እና መስፈርቶችን ከፍ ማድረግ የቻሉ በመሆናቸው፣ የገነቡትን መልካም ስም ለፍጥነት በለው ጥራትን መስዋዕት እንደማያደርጉ ገንፀዋል፣ ይህም ጊዜን እንደሚወስድ እና በችኮላ ያልተጠናቀቀን ጌም ከመልቀቅ መዘግየቱን በግልጽ መናገር እንደሚመርጡ ስቱዲዮው ተናግሯል። መልዕክቱ ግልጽ ነው፡- ስቱዲዮው ለስህተት፣ ለችኮላ ወይም ለፈጠራን መስዕዋትነት ምንም ዓይነት ቦታ የለውም። 

የመዘግየቱ ጉዳይ ለመላ ኢንዱስትሪው አስደንጋጭ ማዕበል ነበር፣ ይህም የTake-Two Interactiveን ፋይናንስ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ አሳድሯል። ይሁን እንጂ የአሳታሚ ድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ስትራውስ ዜልኒክ ሙሉ በሙሉ ያለቀ ጌም በችኮላ ከተወታተፈ ጌም የተሻለ እንደሆነ በመገንዘብ እርምጃውን ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፉ ገልጸዋል። 

ለጊዜው፣ Rockstar ስለቀጣይ እቅዶቹ፣ ስለ ሁለተኛው ማስታወቂያ፣ ስለ ጌሙ አዳዲስ ባህሪያት እና ስለ ጌሙ አጠቃላይ ዝርዝሮች ከመግለጽ ተቆጥቧል። በቀጣዮቹ ወራት ተጨማሪ ዜናዎች እንደሚኖሩ ብቻ ቃል ገብቷል። ነገር ግን ትዕግስት ቁልፍ ነው። የመዘግየቱ ነገር ቅር የሚያሰኝ ቢሆንም፣ Rockstar ለጥራት እና ለተጫዋቾች ተሞክሮ ያለውን ትልቅ ቦታን ግን ማሳያ ነው። GTA VI ጌም ብቻ አይደለም፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነትን ያገኘ ክስተት ነው። ጊዜው ደርሶ በስተመጨረሻ ሲለቀቅም፣ ጥበቃው በከንቱ እንዳልነበር ማረጋገጫ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም። 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !