
ፎርትናይት ምዕራፍ 6 ክፍል 3 ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ የስታር ዋርስ ድባብን ሊላበስ ተዘጋጅቷል፣ ይህን አስመልክቶም አድናቂዎች በደስታ ተጥለቅልቀዋል። እ.ኤ.አ. ከሜይ 2025 ጀምሮ ከእያንዳንዱን ታዋቂ ገጸ-ባህሪያት ማለትም ከሬይ፣ ከዳርዝ ሲዲየስ፣ ከዳርዝ ቬደር፣ ከማሴ ዊንዱ እና ከዳርዝ ሞል ጋር የተያያዙ አብሪ ሻሞላዎችን አደን ደሴቲቱ ወደ ጋላክቲክ የጦርነት አውድማነት የምትቀየር ይሆናል። እነዚህ አብሪ ሻሞላዎች መልክ ብቻ አይምሰሏችሁ፣ ከምታስቡት በላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ የሚችሉ ኃይለኛ መሳሪያዎች ናቸው።
እያንዳንዱ የራሳቸው ልዩ የሆነ ኃይል ያላቸው ሲሆን፦
ሬይ፡- አስፈንጥሮ የሚጥል ኃይለኛ ግፊት (Force Push)
ዳርዝ ሲዲየስ፦ በአስደንጋጭ እና በከፍተኛ በኃይል የተሞላ ተወርዋሪ መብረቅ (Force Lightning)
ዳርዝ ቬደር፡- አምዘግዝጎ ሻሞላውን መወርወር (Saber Throw)
ማሴ ዊንዱ፡- እንደ መንጠቆ፣ ጨምድዶ መያዝ (Force Grapple)
ዳርዝ ሞል፡- ልክ እንደ ብስጩ ጀዳይ ጠላትን ማጋጨት እና መወርወር (Force Slam)
በአጭሩ፣ እንቅስቃሴዎን እና የውጊያ ስልትዎን ሙሉ በሙሉ በመለወጥ፣ እውነተኛ የስታር ዋርስ ስሜትን ያጎናጽፋሉ።
የስታር ዋርስ አብሪ ሻሞላዎችን ሁለት መንገዶችን በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ፡-
በቅድሚያ፣ ካርታው ላይ የሚገኙ ምልክቶችን ይፈልጉ (ሰማያዊ = ሬይ፣ ቀይ = ሲት፣ ወይን-ጠጅ = ዊንዱ)።
በመቀጠል፣ ሆሎግራሙ ጋር ይነጋገሩ እና ስልጠናውን ይውሰዱ።
በመጨረሻም፣ አብሪ ሻሞላውን እና ኃይሉን መቀበል ይችላሉ።
ማስታወሻ፦ ይህን ዘዴ በመጠቀም፣ በአንድ ግጥሚያ አንድ ሻሞላ ብቻ ነው ማግኘት የሚችሉት።
ሻሞላ ያለው ተጫዋች ይፈልጉ እና ያስወግዱት
ከዛ፣ መሳሪያውን ይውሰዱ
ማስታወሻ፦ ይህ ዘዴ ፈጣን ቢሆንም፣ አደገኛ እና የውጊያ ችሎታ የሚጠይቅ ነው።
ሬይ እና ሲዲየስ ከሁለተኛው አውሎ ነፋስ በኋላ የሚመጡ ሲሆን፣ ሰማያዊ ወይም ቀይ ምልክቶቹን በመከተል ያገኟቸዋል።
ቬደር Shogun Solitude ውስጥ የመሸገ በመሆኑ፣ እሱን ማግኘት ትንሽ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ውጊያ ላይ ድል ከነሱት በኋላ፣ ልዩ ሻሞላውን እና ኃኣይሉን ማግኘት ይችላሉ።
ማሴ ዊንዱ እና ዳርዝ ሞል እ.ኤ.አ ሜይ 8 ላይ የራሳቸውን ተልዕኮ ይዘው ይመጣሉ።
ሁለተኛው አውሎ ነፋስ እንደተከሰተ ወዲያውኑ ምልክቶቹን ይፈልጉ። ሌሎች ተጫዋቾችም እንደርሶ አደን ላይ ሊሆኑ ስለሚችሉ ቀድመው ለመገኘት ይሞክሩ።
እንደ እድል ሆኖ ውጊያ መኃል ሻሞላ የያዘ ሰው ካዩ፣ ምንም ጊዜ ሳያጠፉ ያስወግዱት እና መሳሪያውን ይውሰዱ።
ከአብሪ ሻሞላዎቹ በተጨማሪ ፎርትናይት የሚከተሉትንም አካቷል፡-
ያልተገደበ ቀልሃ ያላቸው ብላስተሮች
X-Wings እና TIE Fighters
የፖ-ዳሜሮን እና የኤምፐረር ፓልፓቲን አዳዲስ አልባሳት
የስታር ዋርስ ይዘት ያላቸው አካባቢዎች
ፎርትናይት ስታር ዋርስን በተመለከተ ምንም የቀረው ነገር የለም። ምን ይጠብቃሉ!? አሁኑኑ ሻሞላዎን ይያዙ እና ይህን አስደናቂ ውጊያ ይቀላቀሉ!
መልካም ጨዋታ!