
ኒንቴንዶ (Nintendo) በቅርቡ ማሪዮ ካርት ወርልድን በተመለከተ መግለጫ የሰጠ ሲሆን፣ ሬይንቦው ሮድን (Rainbow Road) በራስ-ሰር ከመከፈት ይልቅ በጥረት የሚገኝ ሽልማት እንዲሆን በማሰብ ጅማሮው ላይ እንደሚቆለፍ አሳውቋል። ተጫዋቾች ይህን ታሪካዊ መንገድ ለማስከፈት እያንዳንዱን ትራክ ቢያንስ አንድ ጊዜ ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል። ምንም አቋራጭ መንገዶች የሉም፣ ችሎታና ቁርጠኝነት ብቻ!
ይህ ውሳኔ፣ ተጫዋቾች በጌሙ ታሪክ ውስጥ እጅግ ታዋቂ የሆነውን መንገድ ለማስከፈት ሙሉ ብቃታቸውን በመጠቀም እንዲጥሩ የሚያደርግ ፈተና ነው። እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፣ ሬይንቦው ሮድ ከትራክም በላይ ነው፣ በልዩ መታጠፊያዎች፣ አስደናቂ ምስሎች፣ ከግጭት መከላከያ አጥሮች ነፃ የሆነ እና ብቃትን በሚፈትሹ መሰናክሎች የተሞላ ጉዞ ነው።
ኒንቴንዶ እስካሁን በይፋ የገለጸው ነገር ባይኖርም፣ ነገር ግን፣ ስዊች 2 አስደናቂ ምናልባትም በውድድሮች መኃል የሚቀያየር፣ በብርሃን የተንቆጠቆጠ ወይም ደረጃ በጨመሩ ቁጥር የሚከፈቱ ድብቅ ክፍሎች ያሉት ሙሉ በሙሉ እንደ አዲስ የተሠራ ሬይንቦው ሮድ እንደሚያቀርብ ተጫዋቾች ባለ ሙሉ ተስፋ ናቸው።
ማሪዮ ካርት ወርልድ ከሬይንቦው ሮድ በተጨማሪ አዳዲስ ይዘቶችን ያካተተ ሲሆን፡-
Exploration Mode፡- የፈለጉትን አካባቢ በነፃነት ማሰስ እና መጓዝ ያስችልዎታል።
Survival Mode፡- ሁሉንም ከጨዋታ ውጪ ማድረግ ለሚሹ የሚሆን እና ምርጦቹ ተወዳዳሪዎች ብቻ የሚተርፉበት የባትል-ሮያል ዓይነት ሞድ።
አዳዲስ መካኒኮች፡- በኃይል የተሞሉ ዝላዮች፣ ሃዲዶች ላይ መንሸራተት እና ከአካባቢዎ ጋር መስተጋብር የሚፈጥሩበት።
24 ተጫዋቾችን የሚያሳትፍ የኦንላይን ውድድር፡- ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ትርምስን እና ፉክክርን የሚፈጥር ግዙፍ ውድድር።
በአጭሩ ማሪዮ ካርት ዎርልድ አዲስ ምዕራፍ ብቻ አይደለም፣ ራሱን የቻለ እና በአዳዲስ መካኒክሶችን የተሞላ የፍሬንቻይዙ አስደናቂ እትም ነው!
ለመወዳደር ዝግጁ ነዎት?