በፈረንሳዩ ስቱዲዮ ስሎክላፕ የተዘጋጀው "ሪማች" የተሰኘው የእግር ኳስ ጌም፣ ተወዳጅነትን ባገኘው የባለብዙ ተጫዋቾች ሞዱ ብቻ ሳይሆን ተመጣጣኝ በሆነ መሸጫ ዋጋውም የብዙዎችን ትኩረት እየሳበ ይገኛል። እ.ኤ.አ. ጁን 19፣ 2025 ፒሲ፣ ፒኤስ 5 እና ኤክስ-ቦክሶች ላይ ሊለቀቅ ቀጠሮ የተያዘለት ሲሆን፣ የተለያዩ የተጫዋቾችን ፍላጎት የሚመጥኑ ሦስት ስታንዳርድ፣ ፕሮ እና ኢላይት እትሞችን አዘጋጅቷል።
እያንዳንዱ እትሞች ምን ምን እንደሚያካትቱ እነሆ፡-
ይህ በጣም ርካሹ አማራጭ ሲሆን፣ በውስጡ ሙሉ ጌሙን እና የቅድመ-ትዕዛዝ ሽልማት የሆነውን የአዶፕተር ኮፍያን ያካትታል። ስለ ማስጌጫዎች ወይም ቀድመ-ተደራሽነት ግድ ለሌላቸው እና በቀላሉ ወደ ሪማች በመግባት አዝናኝ እና በጀት ቆጣቢ ተሞክሮን ማጣጣም ለሚፈልጉ ተጫዋቾች የሚሆን ጥሩ አማራጭ ነው።
የተሻሻሉ አማራጮች ያሉት ጥሩ የሚባል እትም ሲሆን፣ ከሙሉ ጌሙ ባሻገር የCaptain Pass ማሻሻያ ትኬትን፣ የብላዞን ተጫዋች የጀርባ ምስል እና ማዕረግን፣ የብላዞን ይዘት ያላቸው ልብሶች እና መለዋወጫዎችን እና እ.ኤ.አ. ጁን 16 ላይ ጌሙ በይፋ ከመለቀቁ ከ72 ሰዓታት በፊት ቀድመው ጌሙን በእጅዎ ማስገባት የሚችሉበትን እድል በውስጡ ይይዛል። ይህ እትም የጨዋታ ተሞክሮዎን እንደፍላጎትዎ ማስተካከል እና በይፋ ከመለቀቁ በፊት ቀድመው እንዲጫወቱ ያስችልዎታል።
ለሪማች ቀንደኛ አፍቃሪያን የተዘጋጀ የተሟላ እትም ሲሆን፣ ፕሮ እትም ላይ የሚገኙ ጥቅማጥቅሞችን ሁሉ ያካተታል። በተጨማሪም ሁለት የCaptain Pass ትኬቶችን፣ የግሊቸር ጫማዎችን፣ የብላዞን AR ጎልን፣ የብላዞን ኮፍያን እና ልዩ ልዩ ማስጌጫዎችንም በውስጡ ያካተታል። ይህ ብቻ አይደለም፣ ጌሙ በይፋ ከመለቀቁ ከ72 ሰዓታት በፊት ቀድመው ጌሙን መኮምኮም ያስችልዎታል። ይህ እትም ልዩ ይዘቶችን ለሚፈልጉ እና ፕሪሚየም ማስተካካያዎችን በመጠቀም ለየት ማለትን ለሚፈልጉ ተጫዋቾች የሚመጥን ምርጥ አማራጭ ነው።
የተጠቀሱት ዋጋዎች ተመጣጣኝ መሆናቸው ግልጽ እና የማያከራክር ጉዳይ ነው። በእያንዳንዱ እትሞች መካከል ያለውም የዋጋ ልዩነት €10 ብቻ በመሆኑ ተጫዋቾች ፍላጎታቸውን መሠረት በማድረግ በቀላሉ የሚፈልጉትን እትም መምረጥ በቀላሉ ያስችላቸዋል። ከፍ ያሉት እትሞች ላይ ከሚገኙት የቅድመ-መዳረሻ አማራጮች በስተቀር በፕሮ እና በኢላይት እትሞች መካከል ያሉት ልዩነቶች ተጨማሪ የማስጌጫ አማራጮች መኖራቸው ብቻ በመሆኑ የትኛውንም እትም ቢጠቀሙ ጨዋታው ላይ የተለየ ጥቅማጥቅም ወይም ተጽዕኖ አይኖረውም።