icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

የRockstar እና GTA 6 ልዩ የማስታወቂያ ስትራቴጂ፣ ዝምታ! 

እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 2023 ላይ የGTA 6 የመጀመሪያው ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ በጌሙን ዙሪያ የሚሰሙ ጭምጭምታዎች ፈጽሞ አልቀዘቀዙም። በሌላ በኩል ደግሞ Rockstar Games ሙሉ በሙሉ ዝምታን መርጧል። ምንም ዓይነት አዲስ ማስታወቂያዎች፣ የጌም ቪዲዮዎች፣ ስለታሪኩ ወይም ገጸ-ባህሪያቱ ምንም ዓይነት መረጃዎች አልወጡም። ነገር ግን ይህ ዝምታ በቸልተኝነት የመጣ ወይም የግንኙነት ችግር አይደለም፣ ሙሉ በሙሉ ሆን ተብሎ የተደረገ እና ጉጉትን ለመቀስቀስ ታስቦ የተደረገ ስልታዊ አካሄድ ነው። 

ሮክስታር ዝምታን ለምን መረጠ? 

የTake-Two Interactive ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ስትራውስ ዜልኒክ ይህ አካሄድ ሆን ተብሎ የሚደረግ መሆኑን በተደጋጋሚ ያሳወቁ ሲሆን፣ የዝምታው ግብ መዘግየቶችን ወይም ችግሮችን ለመደበቅ ሳይሆን ልዩ አጓጊ ክስተትን መፍጠርን ያለመ መሆኑን አረጋግጠዋል። አክለውም GTA 6 በመዝናኛ ኢንዱስትሪው ታሪክ ውስጥ በጣም ከሚጠበቁ ጌሞች አንዱ በመሆኑ፣ ሮክስታር ተጫዋቾችን በማስታወቂያ ከማጨናነቅ እና ሁሉንም ነገር አስቀድሞ ከማሳየት ይልቅ ድንገት በትክክለኛው ጊዜ ዱብዳ መሆንን እንደሚመርጥ ገልፀዋል። 

ይህ ስልት እያንዳንዱ በRockstar የሚደረጉ ማስታወቂያዎች እና መግለጫዎች ልክ እንደ ትልቅ ክስተት እንዲቆጠሩ የሚያስችል ነው። ሮክስታር በርካታ የማስታወቂያ ዘመቻዎችን በየጊዜው ከማካሄድ ይልቅ ጌሙ ሊለቀቅ አካባቢ ከፍተኛ ደስታን እና ጉጉትን የሚያጭሩ አጭር፣ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ዘመቻዎችን ማካሄድን ይመርጣል። 

ሆኖም ግን ይህ ስትራቴጂ ትልቅ ጥንቃቄን የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ሮክስታር ጉጉትን ከመፍጠር ባለፈ ከዚህ በፊት ዝግጅታቸውን ያልጨረሱ ወይም በችኮላ የተለቀቁ ባለትልቅ በጀት እና አንጋፋ ጌሞች ያጋጠሟቸውን ስህተቶችን ማስወገድ ይፈልጋል። ይህም ሁሉም ነገር ተጠናቆ እስኪያልቅ ድረስ ሊጠብቁት የማይችሉትን ቃል መግባት ወይም ድንገት ሊለወጡ የሚችሉ ባህሪያትን በማሳወቅ በተጫዋቾች ዘንድ ሊፈጠሩ የሚችሉ ቅሬታዎችን ማስወገድ ያስችላቸዋል። 

እንደ ቅርብ ጊዜ ዘገባዎች ከሆነ GTA 6 እ.ኤ.አ በ2025 መገባደጃ ላይ ሊለቀቅ እንደሚችል ተዘግቧል። እስከዚያው ድረስ Rockstar ዋና የማስታወቂያ ዘመቻውን ሊጀምር ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። አንዳንድ ተንታኞች Take-Two የፋይናንስ ውጤቶችን በሚያሳውቅበት ጊዜ ማለትም እ.ኤ.አ ሜይ 2025 አጋማሽ ላይ አዳዲስ ማስታወቂያዎች ሊወጡ ይችላሉ ብለው ያምናሉ። ይህም በጥንቃቄ ከተገበሩት ስልታዊ ውጥረት ጋር የሚጣጣም ይመስላል፣ እያንዳንዱ ዝምታ ጉጉትን የሚያጭር፣ እያንዳንዱ ጭምጭምታም ለትልቅ ክስተት ምክንያት ይሆናል። 

 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !