icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ሮክስታር ጌምስ ራሱን የቻለ የጂቲኤ 6 ቻናል ያለው የዲስኮርድ ሰርቨር ከፈተ! 

ሮክስታር ጌምስ (Rockstar Games) እ.ኤ.አ. ፊብሪዋሪ 12 2025 ጂቲኤ 6 (GTA 6) ከመውጣቱ ከወራት በፊት አዲስ የዲስኮርድ ሰርቨር በመክፈት አድናቂዎቹን አስደንቋል። ከ215,000 በላይ የሚሆኑ ተጫዋቾች ሃሳቦቻችውን ለማጋራት፣ መረጃዎችን ለመቀያየር እና ስለ ጂቲኤ 6 ያላቸውን ጉጉት ለማሳየት በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ሰርቨሩን ተቀላቅለዋል። 

ሰርቨሩ ራሳቸውን የቻሉ የጂቲኤ ኦንላይን (GTA Online)፣ የሬድ ዴድ ኦንላይን (Red Dead Online)፣ ቀደምት የሮክስታር ስራዎች እና በቅርቡ ለሚለቀቁ ጌሞች የተዘጋጀ ቻናሎች ያሉት ሲሆን፣ የዓይኖች ሁሉ ማረፊያ የሆነው ቻናል ግን የጂቲኤ 6 ነው። በሰዓት ውስጥ ተጫዋቾች ስላቀዷቸው ዘረፋዎች፣ የጨዋታ መካኒክሶች እና ትንበያዎችን ያዘሉ በሺዎች የሚቆጠሩ መልዕክቶች ያለገደብ ይጎርፋሉ። 

ይህ ሁሉ ዱብዳ የሆነበት ሮክስታርም ትርምሱን እና ማለቂያ የሌላቸው መልዕክቶችን ለመቀነስ በማሰብ ጥብቅ ህጎችን አውጥቷል። ለጊዜው የእንግሊዝኛ ቋንቋ አማራጭ ብቻ መኖሩ አንዳንድ ተጫዋቾችን ቅር ቢያሰኝም፣ አጠቃላይ የማህበረሰቡ ድባብ እና አቀባበል አሁንም ፍጹም አዎንታዊ ነው። 

ከስቱዲዮው መደበኛ መረጃዎች በማይሰጡበት በዚህ ሰዓት፣ ይህ ሰርቨር በፍጥነት የማህበረሰቡ ማዕከላዊ መሰብሰቢያ እና መረጃ መለዋወጫ ማዕከል መሆን ችሏል። ሰርቨሩን ለመክፈት ሮክስታር የወሰነው ውሳኔም፣ ከደጋፊዎቹ ጋር በቀጥታ መገናኘት እና ስለጂቲኤ 6 የሚናፈሱ አሉባልታዎችን እንዲቆጣጠር ያስችለዋል። 

ቀደም ሲል በድብቅነቱ የሚታወቀው ሮክስታር አሁን ማህበረሰቡ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል ያሰበ ይመስላል። ይህ የዲስኮርድ ሰርቨር መገናኛ መሳሪያ ብቻ አይደለም፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የሮክስታር አድናቂዎች ሊጎበኙት የሚገባ ሁለገብ ማዕከል ነው። 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !