icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

GTA 6ን ኮምፒውተርዎ ላይ ለመጫወት የሚያስፈልጉ የሲስተም መስፈርቶች 

Rockstar እስካሁን GTA 6ን ለመጫወት የሚያስፈልጉ የኮምፒውተር ሲስተም መስፈርቶችን በይፋ የገለጸ ባይሆንም፣ አዝማሚያዎችን እና የባለሙያዎችን ትንታኔዎችን መሠረት በማድረግ፣ GTA 6ን በተቀላጠፈ ሁኔታ እና ያለምንም ችግር ለመጫወት የሚያስችሉ የኮምፒውተር ሲስተም መስፈርቶችን እንደሚከተለው አዘጋጅተና። 

መደበኛ የኮምፒውተር ሲስተም መስፈርቶች፦ 

  • ኦፕሬቲንግ ሲስተም፦ በቅርቡ የዘመነ ዊንዶውስ 10 

  • ፕሮሰሰር፦ ኢንቴል ኮር i5-8500 / AMD Ryzen 5 3600 

  • ራም፦ 16 ጂቢ 

  • ግራፊክስ ካርድ፦ NVIDIA GeForce RTX 3060 (8GB) / AMD Radeon RX 6700 XT 

  • ስቶሬጅ፦ ከ150–160 ጂቢ ፈጣን SSD 

እነዚህን መስፈርቶች በመጠቀም፣ በመካከለኛ የግራፊክስ ቅንብሮች፣ በ1080p ጥራት፣ ከ30 እስከ 60 FPS ባለ ፍሬም መጫወት ያስችልዎታል። ሆኖም ግን ጌሙ በሚለቀቅበት ጊዜ የሚኖረው አወቃቀር ይወስነዋል። 

ለተሻለ ተሞክሮ የሚመከሩ የኮምፒውተር ሲስተም መስፈርቶች፦ 

  • ኦፕሬቲንግ ሲስተም፦ በቅርቡ የዘመነ ዊንዶውስ 10 / 11 

  • ፕሮሰሰር፦ ኢንቴል ኮር i5-13400F / AMD Ryzen 5 5600X CPU 

  • ራም፦ 32 ጂቢ 

  • ግራፊክስ ካርድ፦ NVIDIA GeForce RTX 4060 (8GB) / RTX 4080 Super / AMD Radeon RX 7600 / RX 7950XT 

  • ስቶሬጅ፦ NVMe SSD (150–160 ጂቢ) 

እነዚህን መስፈርቶች በመጠቀም፣ በ1080p ወይም 1440p ጥራት፣ በ60+ FPS ከፍተኛ የግራፊክስ ቅንብሮች ያለምንም መቆራረጥ መጫወት ያስችልዎታል። 

የተሻለ ተሞክሮ ማግኘት የሚያስችሉ ተጨማሪ ነጥቦች፦ 

  • ፈጣን SSD መጠቀም ጌሙን ለመክፈት የሚወስደውን ቆይታ በእጅጉ ይቀንሳል። በተለይ እንደ GTA 6 ላሉ ትልቅ ጌሞች ወሳኝነት አለው።  

  • 16 ጂቢ ራም በቂ ቢሆንም፣ 32 ጂቢ ራም መጠቀም ኮምፒውተርዎ ላይ ጌሙን እየተጫወቱ ሌሎች መተግበሪያዎችን ከጀርባ ማስኬድ ያስችልዎታል። 

  • ምንም እንኳን 1080p ጥራት በቂ ቢሆንም፣ ባለ 1440p IPS/OLED ሞኒተሮችን መጠቀም ምስሎችን ይበልጥ ማራኪ እና አይነ-ግቡ ማድረግ ያስችልዎታል፣ ። 

  •  የተሻለ የድምፅ ጥራት ለማግኘት፣ የድምፅ ካርድዎ ከDirectX 12 ጋር ተመጣጣኝ መሆኑን ያረጋግጡ። 

ኮምፒውተርዎ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈቶች የማያሟላ ከሆን፣ የሚከተሉትን ማሻሻያዎች ማድረግ ይችላሉ፦ 

  • የራም አቅምን መጨመር (ከ16 → 32 ጂቢ) 

  • ከፍተኛ ፍጥነት ያለው SSD መጫን 

  • ወደተሻለ ግራፊክስ ካርድ ማሻሻል 

እነዚህ ማሻሻያዎች ኮምፒውተር ላይ GTA 6ን ብቻ ሳይሆን ሌሎች በቅርቡ ለሚለቀቁ ትልቅ ጌሞችን ያለምንም ችግር እንዲጫወቱ ያስችልዎታል። 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !