icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ክሌር ኦብስኩር፡ ኤክስፔዲሽን 33፣ ክሮማቲክ ላንሰርን የት ማግኘት እና እንዴት ማሸነፍ ይቻላል? 

ክሌር ኦብስኩር፡ ኤክስፔዲሽን 33 ላይ ክሮማቲክ ላንሰር ገና ጌሙን ሲጀምሩ ከሚያገኟቸው የጠላት አለቆች አንዱ ነው። ጨዋታው ገና ሲጀመር የሚመጣ ቢሆንም እጅግ ፈታኝ ጠላት ነው። ይህም ለእርስዎ ቅልጥፍናን ለመለማመድ እና የውጊያ ስልቶችን ለመማር ጥሩ አጋጣሚ ነው። 

ክሮማቲክ ላንሰርን የት ነው የሚገኘው? 

ክሮማቲክ ላንሰርን ለማግኘት "Great Clearing" ላይ ካለው save point ቦታ ትንሽ ራቃ ብሎ ወደሚገኘው "Flowered Valleys" ቀጥታ ይሂዱ። ወደ "Indigo Tree" የሚወስደው ገደል ላይ ለመውጣት አይሞክሩ፣ ይልቁን ከ "Great Clearing" በስተቀኝ የሚገኘው ቦታ ላይ በርካታ የ"Nevronዎች ቅሪተ-አካል ያለበት ትንሽ እና ገለልተኛ ቦታ ያገኛሉ። ክሮማቲክ ላንሰርን የሚያገኙት እዚህ ቦታ ላይ ሲሆን፤ በቀላሉ አረንጓዴ ቅርፊቱን አይተው ሊለዩት ይችላሉ። ነገር ግን ጥቃት ካልሰነዘሩበት በስተቀር በራሱ አያጠቃወትም፤ ይህም በደንብ መዘጋጀት እንዲችሉ እድል ይሰጥዎታል። 

ከውጊያው በፊት ምን ማድረግ አለብዎ? 

በብቁ አቋም ለመጀመር ለመዋጋት፣ ከውጊያው በፊት ቢያንስ level 3 ቢደርሱ ይመከራል። በተጨማሪም በረዶን የመቋቋም አቅሙ አነስተኛ በመሆኑ የበረዶ መሳሪያዎችን ወይም ድግምቶችን ሊጠቀሙ ይገባል። እንዲሁም የጨረቃ በረዶ ድግምቶችን መጠቀም አስደናቂ ውጤቶችን ያስገኝልዎታል። ይህ ውጊያ ጌሙ ውስጥ ወሳኝ የሆኑትን ጥቃትን የማምለጥ እና የመከላከል (dodging and parrying) ችሎታዎን ለማዳበር የሚያስችልዎ ትልቅ አጋጥሚ ነው። 

ክሮማቲክ ላንሰርን እንዴት ማሸነፍ ይቻላል? 

ክሮማቲክ ላንሰር "Expert mode" ላይ፣ 6,670 የህይወት ነጥቦች (health points) አሉት። የጥቃት አሰናዘር ስልቱ በጣም ቀላል በመሆኑ ያለምንም መጨናነቅ የሚለመድ ነው። ፍልሚያውን እንደተጀመረ ጭንቅላቱ ላይ የሚገኘውን ክብ የኃይል ኳስ (energy orb) ለመምታት ይሞክሩ፤ ጥሩ አድርገው ከመቱት የህይወቱን አንድ አራተኛ (25%) ባንዴ መቀነስ ይችላሉ። ከዚያ በመቀጠል ድክመቱን ለመጠቀም እና ውጊያውን ለማፋጠን አካላዊ ጥቃቶችን እና የበረዶ ድግምቶችን እያፈራረቁ ያጥቁት። 

የሚጠቀማቸው ዋና ዋና የጥቃት ስልቶቹ ጥቂት ቢሆኑም ጉዳት የማድረስ አቅማቸው ግን ከፍ ያለ ነው። ብዙውን ጊዜ ሁለት ፈጣን ምቶችን በተከታታይ ይሰነዝራል፤ ስለዚህ መልሰው ከማጥቃትዎ በፊት ይከላከሉ ወይም ለማምለጥ ይሞክሩ። በተጨማሪም ከማጥቃቱ በፊት ኃይል የሚያጠራቅምበት በጣም ኃይለኛ ግን ቀስተኛ የጥቃት ስልትንም ይጠቀማል። ይህንን ጥቃት መመከት ከቻሉ መልሶ የማጥቃት እና ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ የሚያስችል ጥሩ እድል ያገኛሉ። ክሮማቲክ ላንሰር ሊገመቱ የሚችሉ ቀላል ስልቶች ስላሉት ውጤታማ የመመከቻ ስልቶችዎን ለመጠቀም አመቺ ነው። 

 

ሽልማቱ ምንድን ነው? 

ክሮማቲክ ላንሰርን ሲያሸንፉ የሚከተሉትን ይሸለማሉ፦ 

  • 180 XP 

  • 2 ክሮማ ካታሊስቶች 

  • 5 ሉሚኮለር 

  • መሠረታዊ የጥቃት አቅምዎን በ50% የሚያሳድግ፣ የደረጃ-2 “Enhanced Attack” ፒክቶግራም  

እነዚህ ሽልማቶች መጀመሪያ ላይ በጣም ጠቃሚ ቢሆኑም፣ ነገር ግን ወደ ጨዋታው ይበልጥ እየዘለቁ ሲሄዱ ያላቸው ፋይዳ እየቀነሰ ይሄዳል። 

መልካም የጨዋታ ጊዜ! 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !