icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

የፎርትናይት ምዕራፍ 6 ክፍል 3 የትዊች ስጦታዎች ምንድን ናቸው? እንዴትስ ተሸላሚ መሆን ይቻላል? 

ሰላም የፎርትናይት ቤተሰቦች፣ ዛሬ አስደሳች ዜና ይዘን መጥተናል! የፎርትናይት ምዕራፍ 6 ክፍል 3 የሆነውን "ሱፐር" አስመልክቶ፣ ኢፒክ ጌምስ አዲስ የትዊች ስጦታዎችን ይዞላችሁ መጥቷል። ይህ አስደናቂ ዕድል፣ ትዊች ላይ የፎርትናይት ቀጥታ ስርጭቶችን በመመልከት ብቻ ሁለት ልዩ የሆኑ ማስጌጫዎችን በነጻ ማግኘት ያስችልዎታል! ይህን አስመልክቶም የዚህ አስደናቂ ዕድል ተቋዳሽ መሆን እንዴት እንደሚችሉ ቀጥለን በዝርዝር ስላስቀመጥን፣ ማንበብዎን ይቀጥሉ! 

የመጀመሪያው ሽልማት፣ Neon Backtracker በመባል የሚጠራ አብረቅራቂ የጀርባ ቦርሳ (back bling) ሲሆን፣ ይህ ቦርሳ በሐምራዊ እና ብርቱካንማ ቀለሞች ያጌጠ፣ retro-futuristic ይዘት ያለው እና አይነ-ግቡ ቦርሳ ነው። ቀጣዩ ሽልማት ደግሞ Neon Noctiblade የሚባል የሚያበራ ዶማ ሲሆን፣ ይህ ልዩ ንድፍ የተላበሰ መሳሪያ የገፀ-ባሕሪዎን ትጥቅ ማሟላት የሚያስችልዎ ምርጥ አማራጭ ነው። እነዚህ ሁለት መሳሪያዎች ትዊች ላይ ለሚደረገው የስጦታ ፕሮግራም ብቻ የተዘጋጁ በመሆናቸው፣ የመሳሪያ መደብሩ ወይም Battle Pass ውስጥ ሊያገኟቸው አይችሉም። የስጦታ ፕሮግራሙ እስከ ጁን 15፣ 2025 ድረስ ብቻ የሚቆይ በመሆኑ ፈጥነው ተሸላሚ ይሁኑ! 

እነዚህን ሽልማቶች ለመሸለም በቅድሚያ የኢፒክ ጌምስ አካውንትዎን ከትዊች አካውንትዎ ጋር ማገናኘት ይጠበቅብዎታል። ይህም በጣም ቀላል ነው! ቀጥታ ወደ Epic Games ድህረ ገጽ ይግቡ፣ ወደ settings ይሂዱ፣ ከዚያ "Connected Accounts" የሚለውን ይጫኑ፣ እና የTwitch አካውንትዎን ያገናኙ። በመቀጠል ወደ Twitch ይሂዱና፣ የፎርትናይት ምድብን በመክፈት "Drops Enabled" የሚል ምልክት የተደረገባቸውን ቀጥታ ስርጭቶች መርጠው ይመልከቱ። 

Neon Backtrackerን ለማስክፈት 30 ደቂቃ ቀጥታ-ስርጭቱን መመልከት የሚጠበቅብዎ ሲሆን፤ Neon Noctibladeን ለማግኘት ደግሞ በአጠቃላይ 1 ሰዓት እስኪሞላ ድረስ መመልከትዎን ይቀጥሉ። አስደሳቹ ነገር፣ ግዴታ አንድ የቀጥታ-ስርጭት ላይ መቆየት አይጠበቅብዎትም፣ ሌሎች ቀጥታ-ስርጭቶችን ቀይረው መመልከት የሚችሉ ሲሆን፤ ከዚያም ስጦታ የሚያስገኙ የፎርትናይት ቀጥታ-ስርጭቶች ላይ ያሳለፉት ጊዜ ይደመር እና ሽልማትዎን ማግኘት ይችላሉ። 

አስፈላጊውን የእይታ ጊዜ ካስቆጠሩ በኋላ ወደ Twitch Drops Inventory ገጽ በመሄድ፣ እያንዳንዱ ሽልማት ላይ "Claim" የሚለውን ይጫኑ እና ፎርትናይትን ይክፈቱ። ሽልማቶችዎን ወዲያው Lockerዎ ውስጥ ያገኟቸዋል፤ ሆኖም ግን አልፎ አልፎ በተለያዩ ምክንያቶች እስከ 14 ቀናት ሊወስድ ስለሚችል በትዕግስት ይጠብቁ! 

እነዚህ ሽልማቶች በሁሉም የጌም መድረኮች ማለትም ፒሲ፣ ኮንሶል ወይም ሞባይል ላይ ይሰራሉ። ከሁሉም በላይ አስደናቂው ነገር ደግሞ ሙሉ በሙሉ ነፃ መሆናቸው ነው! ምንም ግዢ ማድረግ አይጠበቅብዎትም፣ ብቸኛ የሚያስፈልግዎ የEpic Games አካውንት፣ የ Twitch አካውንት እና ለአጭር ጊዜያት ቀጥታ ስርጭቶችን መመልከት ብቻ ነው።  

ይፍጠኑ! መልካም እድል! 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !