
ፎርትናይት ምዕራፍ 6 ክፍል 3 Star Warsን፣ እና ሌሎች አስደሳች አዲስ ነገሮችን ይዞ መጥቷል! ይህም የማንዶሎሪያኑን ጄትፓክ ለማግኘት ሁሉም ሰው በሚባል ሁኔታ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ይህ ጄትፓክ አየር ላይ እየበረሩ ጠላቶችን ማጥቃት፣ ወደ ከፍተኛ ቦታዎች ማምለጥ የሚያስችል እና አጨዋወትዎን የሚቀይር ድንቅ መሳሪያ ነው። ይህን አስደናቂ መሳሪያ እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ማወቅ ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ማንበብዎን ይቀጥሉ!
ይሄ ጄትፓክ መዘነጫ ወይም መዝናኛ ብቻ አይደለም። ጦርነቶችን በበላይነት መቆጣጠር፣ በተለምዶ መድረስ የማይችሉባቸው ቦታዎች ላይ መድረስ፣ ከጠላት የሚተኮሱ ጥይቶችን መሸወድ፣ እንዲሁም ከሁሉም በላይ ደግሞ ከፍታ ቦታዎችን ያለምንም እክል መቆጣጠር ያስችልዎታል። ይሄ ጄትፓክ የStar Warsን በድጋሚ መመለስ ምክንያት በማድረግ ሲሆን የተመለሰው፣ የሁሉንም ተጫዋቾች ቀልብ መሳብ ችሏል።
ይሄንን ጄትፓክ ሁለት መንገዶችን በመጠቀም ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፣ በጣም አስተማማኙ መንገድ በቀጥታ ከማንዶሎሪያን NPCዎች በ300 የወርቅ አሞሌ መግዛት ነው። እነዚህ NPCዎች ካርታው ላይ የሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ተደብቀው የሚገኙ ሲሆን፡ ከOutlaws Oasis አጠገብ፣ በCanyon Crossing እና በMasked Meadows መካከል ባሉ ተራሮች ላይ፣ ከPumped Power በስተምስራቅ በኩል፣ እንዲሁም Magic Mosses ላይ የሚገኘው ወንዝ አጠገብ ይገኛሉ። ሆኖም ግን ማወቅ ያለብዎ ጉዳይ፤ አንዳንድ ጊዜ Magic Mosses ውስጥ ሻጮጩን ለማስከፈት ማኅበረሰቡ የተወሰኑ ተልዕኮዎችን እስኪያጠናቅቁ መጠበቅ ሊኖርብዎ ይችላል።
ሌላኛው መንገድ ደግሞ፣ ሣጥኖች ውስጥ እንደ loot ሊያገኙት ይችላሉ። በተለይም ብርቅዬ በሆኑት፣ ተበታትነው የሚገኙ (Ground loot)፣ ከአቅርቦት ግብዓቶች (supply drops)፣ ወይም ደግሞ ከገደሉት ተጫዋች ላይ ማግኘት ይችላሉ። ይሄ ትንሽ ዕድልን የሚጠይቅ ቢሆንም፣ በደምብ ተግተው ፍለጋ ካደረጉ ውጤታማ መሆን ይችላሉ።
ማስታወሻ፡ በተቻለ መጠን ብዙ ሣጥኖችን በመክፈት ይፈትሹ፣ ማንዶሎሪያኖች የሚራቡባቸው አካባቢዎች ላይ ትኩረት ያድርጉ፣ እንዲሁም በየሳምንቱ የሚለቀቁ የStar Wars ተልዕኮዎችን ይከታተሉ።
አንዴ ጄትፓኩን እጃችሁ ካስገባችሁት በኋላ፣ አጠቃቀሙ እጅግ ቀላል ነው። ፒሲ ላይ፣ Spaceን፤ PlayStation ላይ Xን፤ Xbox ላይ Aን፤ እና Switch ላይ ደግሞ B የሚለውን ቁልፍ በመጫን ለአስራ ሁለት ሰከንድ ያህል አየር ላይ መንሳፈፍ ይችላሉ፣ ከዚያ ጄትፓኩ መልሶ ኃይል ለመሙላት ስምንት ሰከንድ ያስፈልገዋል። ሌላው፣ እየተጠቀማችሁበት ከወደቃችሁ ምንም ዓይነት ጉዳት አይደርስባችሁም።
መልካም ጨዋታ!