
አሁን ላይ ፎርትናይት በሁሉም የመተግበሪያ መደብሮች ላይ ባይገኝም፣ የሚጠቀሙት ስልክ አንድሮይድ ይሁን አይፎን፣ ስልክዎ ላይ ጭነው መጫወት የሚችሉበትን ዘዴ ዛሬ እናሳይዎታለን። ቀጥሎ እንዴት አንድሮይድ እና አይፎን ስልኮች ላይ ፎርትናይትን በቀላሉ የሚጭኑበትን መንገድ ሂደት በሂደት የሚያሳይ መመሪያ እነሆ፡-
ፎርትናይት አሁን ላይ Google Play መደብር ላይ የማይገኝ ቢሆንም፣ እነዚህን ሂደቶች በመከተል በቀላሉ ስልክዎ ላይ መጫን ይችላሉ፡-
1. ብሮዘርዎን ይክፈቱና የEpic Games ድረ-ገጽን ይክፈቱ
2. የEpic Games መተግበሪያን (APK ፋይል) ያውርዱ
3. ስልክዎ ከማይታወቁ ምንጮች (Unknown Source) ስለሚመጡ መተግበሪያዎች ማስጠንቀቂያ ከሰጠዎ፡-
- ወደ Settings → Security ይሂዱ
- በመቀጠል "Install from unknown sources" የሚለውን አማራጭ ያብሩ
4. የEpic Games መተግበሪያን ይክፈቱ እና ፎርትናይትን በመፈለግ Install የሚለውን ይጫኑ
5. ወደ Epic Games አካውንትዎ ይግቡ ወይም አዲስ ይክፈቱ
6. የሳምሰንግ ተጠቃሚ ከሆኑ፣ ፎርትናይትን በቀጥታ ከGalaxy Store መጫን ይችላሉ።
የአይፎን ተጠቃሚ ከሆኑ፣ ነገሮች ትንሽ ሊወሳሰቡ ይችላል። በአፕል እና በኢፒክ ጌምስ መካከል ተፈጥሮ ከነበረው አለመግባባት በኋላ ፎርትናይት ከApp Store እንዲሰረዝ ተደርጓል። አውሮፓ ውስጥ የሚገኙ ከሆነና iOS 17.6 ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሲሪቶችን የሚጠቀሙ ከሆነ ግን የEpic Games አዲሱ የiOS መደብርን በመጠቀም ፎርትናይትን መጫን ይችላሉ፡-
1. Safari Browserን ይክፈቱና ወደ Epic Games ድረ-ገጽ ይሂዱ
2. "Install on iOS" የሚለውን ይጫኑና ሂደቶቹን እስከመጨረሻው ይከተሉ
3. የመጫን ሂደቱን እንዲያረጋግጥጡ ከተጠየቁ Settings ውስጥ ያጽድቁ
4. የEpic Games Storeን ጭነው ከጨረሱ በኋላ ከመደብሩ ፎርትናይትን ያውርዱ
ማስታወሻ፡ በፀደቁ የመተግበሪያ መደብር ፖሊሲዎች የተነሳ፣ አሁን ላይ ይህ የመጫኛ ዘዴየሚሰራው አውሮፓ ውስጥ ብቻ ነው።
ክላውድ ጌሚንግ (Cloud Gaming) (ለማንኛውም የስልክ ዓይነት)
የሚገኙት ከአውሮፓ ውጪ ከሆነ ወይም ምንም አማራጭ ከሌለዎ፣ የክላውድ ጌሚንግ ዘዴን በመጠቀም ምንም ነገር መጫን ሳይጠበቅብዎ በGeForce NOW አማካኝነት ቀጥታ ብሮውዘርዎ ላይ ፎርትናይትን መጫወት ይችላሉ፡-
1. Safari ን ይክፈቱና ወደ GeForce NOW ድረ-ገጽ ይሂዱ
2. ነጻ የNVIDIA አካውንት ይክፍፈቱና ከEpic Games አካውንትዎ ጋር ያገናኙት
3. በመጨረሻም፣ ቀጥታ ፎርትናይትን ብሮውዘርዎ ላይ ያስጀምሩት
መቆጣጠሪያዎቹ (touch controls) በደንብ ከመስራታቸው የተነሳ በመተግበሪያው እየተጫወቱ ያሉ ነው የሚመስልዎት።
- እንደ Epic Games ድረ-ገጽ ወይም Galaxy Store kalu ታማኝ ምንጮች ብቻ ያውርዱ
- ፈጣን Wi-Fi፣ በቂ ማከማቻና ጥሩ RAM ያለው ስልክ ይጠቀሙ
- ዝማኔዎች ወይም የብልሽት ጥገናዎች ቶሎ እንዲደርስዎ የEpic Games ዜናዎችን ይከታተሉ
ስለዚህ አዎ፣ በ2025ም ፎርትናይትን ሞባይል ስልኮች ላይ መኮምኮም ይችላሉ! ትንሽ ትዕግስት እና ትክክለኛውን ዘዴ መከተል ብቻ ነው የሚጠበቅብዎ።