icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ፎርትናይት ምዕራፍ 6 ክፍል 3 ላይ የሚገኙ ሄሮይክ መሳሪያዎች ዝርዝር እና በእጅዎ ማስገቢያ መንገዶች 

ሰላም የፎርትናይት አፍቃሪያን! ሱፐር ተብሎ ስለሚጠራው የፎርትናይት ምዕራፍ 6 ክፍል 3 ሲነሳ፣ ሄሮይክ መሳሪያዎች በቅድሚያ የሚነሱ ጉዳዮች ናቸው። እነዚህ ኮሚክ መጽሐፍትን እና ሳይንሳዊ ልብ ወለዶችን መሠረት በማድረግ የተሰሩ ልዩ መሳሪያዎች  የውጊያ ተሞክሮዎችን ሙሉ በሙሉ ሊቀይሩ የሚችሉ ኃይለኛ አቅምን የሚያጎናጽፉ ናቸው። 

አሁን ላይ ተካተው ከሚገኙት መሳሪያዎች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-  

  • ሚስት ጋውንትሌትስ (Myst Gauntlets)፦ የዳርክ ኢነርጂ ሞገድን የሚያመነጭ መሳሪያ። 

  • ኪልስዊች ሪቮልቨርስ (Killswitch’s Revolvers)፦ ከጥቃት ማምለጥ  እና የማነጣጠር ብቃትን የሚጨምረውን Ariel Modeን ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል መሳሪያ። 

  • ትራኪንግ ቫይዘር (Tracking Visor)፦ በአቅራቢያ የሚገኙ የጠላት ዱካዎችን ተከታትለው ማደን የሚያስችል መሳሪያ።  

  • ቤዝ ፐልስ (Bass Pulse)፦ ወደ አየር ሊያስወነጭፍዎ የሚችል ባለተከታታይ ሶኒክ ፍንዳታ መሳሪያ። 

በዚህ ሲዝን መጨረሻ ላይ ለመካተት እቅድ የተያዘላቸው ሄሮይክ መሳሪያዎች፡- 

  • ሰርፈር ኪዩብ (Surfer Cube)፡- ከኪዩብ ኢነርጂ የተሰራ ባለከፍተኛ ፍጥነት ሆቨርቦርድ። 

  • ስተርም ቢስት ፖም-ፖምስ (Storm Beast Pom-Poms)፡- ወደ አስፈሪ አውሬነት መቀየር የሚያስችል። 

  • ሚስቲክ ፎርም (Mystic Form)፡- ለአጭር ጊዜ ወደ ማይበገሩ የቁራ መንጋዎች መቀየር የሚያስችል። 

  • አሴንድድ ሚስት (Ascended Myst)፡- የሚስት ጋውንትሌትስ እና ሚስቲክ ፎርምን ያጣመረ ከፍተኛ ጥቃትን ማድረስ የሚችል መሳሪያ። 

ከእነዚህ እጅግ በጣም ኃይለኛ ከሆኑ መሳሪያዎች በተጨማሪ እንደ፦ 

  • ሮቢንስ ግራፕል ላውንቸር (Robin’s Grapple Launcher) 

  • ስፓየር ራይፍል (Spire Rifle) 

  • ሃይፐርበርስት ፒስትል (Hyperburst Pistol) 

  • ዴድአይ ዲ.ኤም.አር (Deadeye DMR)  

እነዚህን እና የመሳሰሉ ከፍተኛ መሳሪያዎችም ያሉ ሲሆን፣ እነዚህ መሳሪያዎች ብዙውን ጊዜ ልዩ ድብቅ ቦታዎች ላይ ወይም ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ላቦራቶሪዎች ውስጥ ይገኛሉ። 

እነዚህን ሄሮይክ መሳሪያዎች ለማግኘት ደሴቱንን አብጠርጥረው ማሰስ ይጠበቅብዎታል። ሊገኙባቸው ከሚችሉ ቦታዎች ውስጥ፦ 

የሂሮ ድብቅ ማከማቻዎች (Hero Caches)፦ ዋና መገኛቸው ሲሆን፣ እንደ ሱፐርኖቫ አካዳሚ (Supernova Academy) ወይም የተለያዩ የጠላት ምሽጎች አቅራቢያ የሚገኙ ቁልፍ ቦታዎች ላይ ተበታትነው ይገኛሉ። እነዚህ ልዩ ሣጥኖች ከC እስከ S ደረጃ የተሰጣቸው ሲሆን፣ ደረጃው ከፍ ባለቁጥርም ብርቅዬ መሳሪያዎችን የማግኘት ዕድልዎ ይጨምራል። አንዳንዶቹ ለመከፈት ከፍ ያለ የሂሮ ደረጃን (Hero Rank) የሚጠይቁ ቢሆንም፣ ተልዕኮዎችን በመወጣት ወይም በቀላሉ ግጥሚያዎችን በማድረግ የሂሮ ደረጃዎን ማሳደግ ይችላሉ። 

ከሂሮ ድብቅ ማከማቻዎች ውጭ፣ አንዳንድ መሳሪያዎች መሬት ላይ ወይም መደበኛ ሣጥኖች ውስጥ በዘፈቀደ ሊገኙ የሚችሉ ቢሆንም፣ ይሄ የሚሆንባቸው ጊዜያት ግን እጅግ ውስን ናቸው። ሌላው ያሸነፏቸውን ተጫዋቾችን መዝረፍ ወይም ከNPCዎች ሊገዟቸው ይችላሉ። የመጨረሻው መንገድ፣ የቴክኖሎጂ ላቦራቶሪዎች (Tech Labs) ሲሆኑ፣ ከፍተኛ አቅም ያላቸውን መሳሪያዎችን በተለያዩ ግብዓቶች ሊሸጡልዎ ይችላሉ።  

መልካም ጨዋታ! 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !