icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ማሪዮ ካርት ወርልድ፣ ስዊች 2 ላይ አሸናፊ ሊያደርጉዎት የሚችሉ 5 ምስጢሮች! 

ማሪዮ ካርት ወርልድ ኔንቲዶ ስዊች 2 ላይ ሊመጣ ነው! እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ጌሙ አስደናቂ ነገሮችን ይዞ የመጣ ሲሆን፡- ዋና መሠረታዊ ይዘቶቹ እንዳሉ ሆነው፣ አዲስ እንደልብዎ ሊያሰሱት የሚችሉት ሰፊ ዓለም፣ እንደ Knockout እና Off-Road ያሉ አዳዲስ የጨዋታ ሞዶችን በውስጡ አካቷል። ሁሌ መሸነፍ ከሰለቸዎ ወይም አንደኛ የመውጣት ፍላጎቱ ኑሮዎት ምን ማድረግ እንዳለብዎ ግራ ከተጋቡ፣ አያስቡ! እንዴት አሸናፊነትን መቀዳጀት እንደሚችሉ በዝርዝር እንነግርዎታለን። 

1. በቱርቦ ይጀምሩ 

ሁሉም ተወዳዳሪ ወደፊት ሲሸመጥጥ ብቻዎን ወደ ኋላ መቅረት ካልፈለጉ ውድድሩ እንደተጀመረ ወዲያው ቱርቦዎን መጠቀም  ይኖርብዎታል። ልክ ሁለተኛው ማስጀመሪያ ደወል እንደተደወለ ወዲያውኑ ነዳጁን ይጫኑ። ቸኩለው ከጀመሩ መኪናዎ ይቆማል፤ ከዘገዩ ደግሞ ወደኋላ የመቅረት እጣ-ፈንታ ይገጥምዎታል። ጊዜው ትንሽ ሊመስል ይችላል ሆኖም ግን የሚፈጥረው ለውጥ እጅግ ከፍተኛ ነው። 

2. ድሪፍት ማድረግ ይለማመዱ 

ለመታጠፍ ሲሞክሩ ZR የሚለውን ቁልፍ ተጭነው በመያዝ ድሪፍት ማድረግ የሚችሉ ሲሆን፣ ቁልፉን ለአፍታ ይዘው ሲለቁት ፍጥነትዎ በሚያስገርም ሁኔታ ይበልጥ ይጨምራል። በተለይ ጠባብ መታጠፊያ ማዕዘኖች ላይ ሚኒ፣ ሱፐር እና አልትራ የሚባሉትን ቡስቶች እንዴት መጠቀም እንዳለብዎ በደምብ ከተረዱ፤ እርስዎ ላይ የሚደርስ ማንም የለም። 

3. አቋራጮች መንገዶችን ያስሱ 

እያንዳንዱ ትራኮች ፍጥነት መጨመሪያ ቦታዎች፣ ወደ ተጨማሪ ቦታዎች የሚወስዱ መንገዶች እና የመሳሰሉ ድብቅ ምስጢሮች አሏቸው፤ ማሪዮ ካርት ወርልድ ደግሞ ሰፊ ክፍት ዓለም እንደመሆኑ መጠን የተለያዩ ቦታዎችን ማሰስ ወሳኝነት አለው። ስለዚህ ቦታዎችን ያስሱ፣ ይሞክሩ፣ ይመዝግቡ። ትክክለኛውን አቋራጭ በትክክለኛው ጊዜ መጠቀም ትልቅ ለውጥ ሊያስገኝ ይችላል። 

4. መሳሪዎችዎን በአግባቡ ይጠቀሙ 

መሳሪዎችዎን ባገኙት አጋጣሚ መጣል ዋጋ ያስከፍልዎታ! ለምሳሌ፡ ጥቃት ለመጣል Green Shell ወይም Banana ከሚጠቀም ይልቅ Red Shell ቢጠቀሙ ይመከራል። እንዲሁም ከBlue Shell ጥቃቶች ወይም ወጥመዶች ለማምለጥ Mushroomዎን በቁጠባ ይጠቀሙ። በአጠቃላይ መሳሪያዎችዎን በከንቱ ሳያባክኑ፣ ለዓላማ እና ስልቱን በጠበቀ መልኩ ይጠቀሙባቸው። 

5. ምርጥ ገጸ-ባሕሪያትን እና ካርቶችን በማጣመር ይሞክሩ 

እያንዳንዱ ገጸ-ባሕሪያት፣ ካርቶች፣ ጎማዎች ወይም መንሸራተቻዎች፣ ፍጥነት፣ አነዳድ . . . ውድድርዎ ላይ ትልቅ ሚናን ይጫወታሉ። ስለዚህ ስታይልዎን የበለጠ መቀያየር የሚያስችሉዎ Dash Foods እና እልባሳት ስለሚገኙ ለእርስዎ ተስማሚ የሆኑትን እስኪያገኙ ድረስ የተለያዩ አማራጮችን እየቀያየሩ ይሞክሩ። 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !