icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ሪማች ላይ አይበገሬ ግብ ጠባቂ መሆን የሚያስችሉዎ ቁልፍ ጉዳዮች! 

ሪማች ላይ ግብ ጠባቂ መሆን ስልትን፣ ቀድሞ የማሰብ ብቃትን እና ብርታትን የሚጠይቅ ወሳኝ ሚና ነው። ከተቃራኒ ቡድን የሚደረጉ እያንዳንዱ ሙከራዎችን ማስቆም መቻል ቀላል ጉዳይ አይደለም፤ ነገር ግን ተገቢውን ቅድመ-ዝግጅት በማድረግ እና የጨዋታውን ስልቶች በጥልቀት በመረዳት ለቡድንዎ የማይደፈር ዘብ መሆን ይችላሉ። 

የራሳቸው ጥንካሬ እና ድክመት ያላቸው የተለያዪ ዓይነት የግብ ጠባቂዎች አሉ። አስተማማኝ የሚባለው የግብ ጠባቂ ዓይነት በዋናነት ከቅጣት ምት ክልል መስመሩ የማይወጣ፣ ደህንነት ላይ የሚያተኩር፣ እንዲሁም ፈጣን ምላሾችን በመከላከል እና አየር ላይ የሚመጡ ኳሶችን በመከላከል የተካነ ነው። ሆኖም የዚህ ግብ ጠባቂ ደካማ ጎን፣ በፈጣን ጨዋታዎች ወይም ድንገተኛ ኳሶች የሚደናገጥ መሆኑ ነው። ስልታዊው ግብ ጠባቂ የምንለው ደግሞ ሁሌ ከጨዋታው ጋር ይግባባል፣ እንቅስቃሴዎችን አስቀድሞ ይገምታል፣ እንዲሁም ኳሱን በጥሩ ሁኔታ ለቡድን አጋሮቹ ያከፋፍላል። የጨዋታውን ሁኔታ መረዳት መቻሉ ጠቃሚ ቢሆንም፤ ከመጠን በላይ በማሰብ ጊዜውን ሊያባክን ይችላል። ስሜታዊ የምንለው ግብ ጠባቂ በበኩሉ ብዙ ጊዜ ጥቃቶችን ለመቀልበስ እና መልሶ ለማጥቃት የግብ ክልልን የሚለቅ ዓይነት ነው ። ለጨዋታው መነቃቃትን ቢሰጥም፤ ከግብ ክልሉ በጣም ርቆ ከወጣ ቡድኑን ለአደጋ ያጋልጣል። በተቻለ መጠን ብዙ ኳሶችን ማዳን ከፈለጉ የአጨዋወት ስልትዎን ከሁኔታው ጋር በማጣጣም እነዚህን የተለያዩ የግብ ጠባቂ አፈፃፀሞች ማዋሃድ ያስፈልጋል። 

ቦታ አያያዝ እና ጥሩ ቦታ መያዝ ከተቃራኒ ቡድን የሚደረግ ሙከራን ለማክሸፍ ዕድል ይሰጣል። የኳሱ አቅጣጫ ወዴት ሊሆን እንደሚችል ለመገመት ይሞክሩ። ሁልጊዜ ዝግጁ እንዲሆኑ ያልተጠበቁ ኳሶችን የማዳን ክህሎትዎን ማዳበር ይኖርብዎታል። ዝቅተኛ ኳሶችን የመቅለብ ክህሎት፣ በመሬት ለሚደረጉ ወይም ሰያፍ ሙከራዎችን ለመከላከል ወሳኝ ነው። አየር ላይ ለሚደረጉ ሙከራዎች ወደ ማዕዘኖች መምቻ ክል መሄድ ይችላሉ፣ ነገር ግን ኳሱን ሊደርሱበት እንደሚችሉ ቀድመው እርግጠኛ ይሁኑ። 

ፍጹም ቅጣት ምቶች ሁሌም ቢሆን ፈታኝ ናቸው። እነዚህን ምቶች የማክሸፍ እድልዎን ከፍ ለማድረግ፣ ፍፁም ቅጣቱን የሚመታው ተጫዋች እንዳይሸውድዎ የመጨረሻው ሰከንድ ላይ ይዝለሉ። ወደፊት በመሄድ፣ በመቃኘት ወይም መዝለል ካሰቡበት ተቃራኒ አቅጣጫ በመንቀሳቀስ ምቱ ሲመታ ወዳሰቡበት አቅጣጫ በመዝለል ለማታለል ይሞክሩ። እንዲሁም ተጫዋቹ ኳሱን ወደ አንድ ጎን እንዲመታ በመጋበዝ ቦታዎን በዘዴ በመቀየር ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ መዝለል ይችላሉ። ለጠንካራ ወይም ሰያፍ ምቶች፣ ተረጋግተው የኳሱ አቅጣጫ ላይ ብቻ ያተኩሩ። አይቸኩሉ! ሰያፍ ምቶች ለማንበብ አስቸጋሪ በመሆናቸው፤ ጽኑ አቋም በመያዝ፣ ልብዎ ወደፈቀደው አቅጣጫ ለመዝለል ዝግጁ ይሁኑ። 

ግብ ጠባቂ መሆን ማለት ንቁ፣ ዝግጁ፣ የጥቃት ስልቶችን አስቀድሞ መገመት መቻል እና ስሜትህን መቆጣጠር መቻል ማለት ነው። የተሳሳቱ ቦታ አያያዞችን እና ከአደገኛ የአንድ ለአንድ ሁኔታዎችን ለማስወገድ ከቡድንዎ ተከላካዎች ጋር መነጋገር ይጠቅማል። ከሁሉም በላይ ስህተት ከተፈጠረ በኋላ ትኩረትን ሙሉ በሙሉ መሰብሰብ መቻል የምርጥ ግብ ጠባቂ መገለጫ ነው። 

አንድ አባባል አለ፦ "ጥሩ ግብ ጠባቂ አስደናቂ ኳሶችን ያድናል። ታላቅ ግብ ጠባቂ ግን ትክክለኛ ቦታ አያያዝን ስለሚከተል፣ ከዚህ ሁሉ ነፃ ነው።" 

ሰናይ ተመኘን! 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !