
ሪማችን ለመጫወት ምርጡ መንገድ ኪቦርድ ወይስ ኮንትሮለር ነው የሚለው ጉዳይ በተጫዋቾች ዘንድ እጅግ አከራካሪ ርዕስ ነው። እንደተጫዋቹ የአጨዋወት ዘይቤ እና ዓላማ ሁለቱም የየራሳቸው ጥቅም እና ጉዳት አላቸው።
ኪቦርድ እና ማውዝን መጠቀም በተለይ ለረጅም ርቀት ወይም ማዕዘን ምቶች እጅግ በጣም እስተማማኝ ነው። ፒክስሉ ድረስ ማነጣጠር የሚያስችል በመሆኑ፣ ከፍተኛ ደረጃ አፈፃፀም ላይ መድረስ ለሚጥሩ ተጫዋቾች እጅግ ጠቃሚ ነው። የቁልፍ ምላሾቹ በጣም ፈጣን በመሆናቸው፣ ፈጣን ኮምቦዎችን እና ድርጊቶችን መፈጸም ያስችልዎታል። እንዲሁም የኪቦርድዎን ቁልፎች ከአጨዋወት ዘይቤዮ ጋር እንዲስማሙ በማድረግ ሙሉ በሙሉ ማስተካከል ይችላሉ።
ሆኖም መጠቀም የሚችሉት classic 8-direction (WASD) በመሆኑ እንቅስቃሴዎች የተገደቡ ናቸው፤ ይህም ኳስ መቆጣጠርን እና የአቅጣጫ ለውጦችን አዳጋች ያደርጋቸዋል። እንዲሁም ረጅም ጊዜ ለሚጫወቱ ተጫዋቾች አድካሚ፣ ለአዲስ ተጫዋቾች ደግሞ የመማር ሂደቱን አዳጋች ሊያደርገው ይችላል።
ኮንሶል ተጠቃሚ ከሆኑ ወይም ይበልጥ ምቹ አማራጭ ከፈለጉ ኮንትሮለር ጥሩ አማራጭ ነው። ለአጠቃቀም ቀላል እና ለአያያዝ ምቹ የሆነ አሰራሩ ሳይታወቅዎ ለረጅም ጊዜ እንዲጫወቱ ያስችልዎታል። አናሎግ ቁልፎቹም ኳስ መቆጣጠርን፣ ማታለልን እና አቅጣጫ ቅየራን ይበልጥ ቀላል ያደርጉታል። የመንቀሳቀስ እና ኳስ የማቀበል የአፈፃፀም ሂደቱም ዝንፍ አይልም፤ በተለይ ደግሞ ለቡድናዊ ጨዋታዎች ጠቃሚ ናቸው።
የኮንትሮለር ጉዳት፣ ያለ ማውዝ ኳስን፣ በተለይ ረጅም ርቀት ወይም ጠባብ ማዕዘኖች ላይ ለማነጣጠር እጅግ አዳጋች ነው። አንዳንድ ኮምቦዎችንም ለመጠቀም የተለያዩ ቁልፎችን መቀያየርን ስለሚጠይቅ፣ ጨዋታዎን ትንሽ ያንቀራፍፍብዎታል። በተጨማሪም ገመድ አልባ ኮንትሮለርን የሚጠቀሙ ከሆነ አንዳንድ የትዕዛዝ መዘግየቶች ሊያጋጥምዎ ይችላል።
ያልተዛነፉ አፈፃፀሞችን ከፈለጉ እና መቆጣጠሪያ ቁልፎችዎን ማስተካከል ምቾት የማይነሳዎ ከሆነ ኪቦርድ/ማውዝ ይጠቀሙ።
የተቀላጠፈ እንቅስቃሴ፣ ለአጠቃቀም ቀላል እና ምቾትዎን ሳይነሱ ለረጅም ጊዜ መጫወት የሚሹ ከሆነ ደግሞ ኮንትሮለር እንዲጠቀሙ እንመክራለን።
በስተመጨረሻ የእርስዎን ፍላጎት የሚያውቁት እርሶ እራስዎ ነዎት፤ ሪማች ሁለቱንም አምራጮች የሚቀበል በመሆኑ፣ ሁለቱንም አማራጮች ራስዎ በመሞከር የቱ ከእርስዎ አጨዋወት ጋር እንደሚስማማ ለመሞከር ወደ ኋላ አይበሉ።