icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ሪማች ላይ አይበገሬ ተከላካይ መሆን የሚያስችሉ መሠረታዊ ስልቶች 

ሪማች ላይ ከተቃራኒ ቡድኖች የሚመጡ ጥቃቶችን ያለምንም እንከን ለመከላከል ብርቱ የመከላከል ብቃትን ይጠይቃል። ”ምርጡ የመከላከያ ስልት ምርጥ የማጥቃት ብቃት ነው” የሚለው አባባል እውነት ቢሆንም፣ ግጥሚያዎችን ማሸነፍ እንዲችሉ የመከላከል መሠረታዊ ክህሎቶችዎን ማዳበር እጅግ አስፈላጊ ነው። 

ጀማሪዎች ከሚያረጓቸው በጣም የተለመዱ ስህተቶች አንዱ አላስፈላጊ ሸርተቴዎችን ከመጠን በላይ መጠቀም ሲሆን፣ ሸርተቴ ሲያደርጉት አስደሳች ቢሆንም፣ ይህን ስልት እንደመጨረሻ አማራጭ ብቻ ጥቅም ላይ ሊውል የሚገባው ነው። የተሳሳተ ሰዓት ላይ ከተንሸራተቱ ወድቀው ይቀሩ እና አጥቂው ወደ ግብ የሚወስደውን ክፍት መንገድ በነፃነት ይጠቀመዋል። ስለዚህ ኳሱን እንደሚያገኙት እርግጠኛ ሲሆኑ ብቻ ይጠቀሙበት። 

የመከላከል አቋም ቁልፍ አካሄድ ሲሆን፣ ይህንንም ለመጠቀም (ኪቦርድዎ ላይ Left Ctrl እና የእጅ መቆጣጠሪያዎ ላይ LT/L2) ሲጠቀሙ ተጫዋችዎ ይበልጥ አስተማማኝ አቋም ላይ እንዲሆኑ እና፣ ኳስን መልሰው ለመቀማት እና ክፍት ቦታዎችን በቀላል ለመሸፈን ያስችላቸዋል። እንዲሁም በአንድ ለአንድ ጨዋታዎች ላይ አይበገሬ ያደርግዎታል። ስኬታማነትዎን ይበልጥ ለመጨመር ይህንን ስልት ከመደበኛ ሸርታቴዎች ጋር በማዋሃድ ይጠቀሙት። 

ብዙ ግቦች የሚከሰቱት በመልሶ ማጥቃት ወቅት በመሆኑ፣ ቡድንዎ በሚያጠቃበት ወቅት በንቃት ይጠባበቁ። ይህም የሚሆነው ብዙውን ጊዜ ተከላካዮች ቦታቸውን ለቀው ያለ ሽፋን ወደ ፊት ስለሚመጡ ነው። የማጥቃት ሂደቱ ላይ በቀጥታ ተሳታፊ ካልሆኑ፣ ረጅም ኳሶችን ለመቀማት እና የተቃራኒ ቡድን አጥቂዎችን ለመከታተል እንዲችሉ መኃል ሜዳ ላይ ይቆዩ። ይህ ዲሲፕሊን በፈጣን የመልሶ ማጥቃት ጊዜዎች ወቅት ሊከላከሏቸው የሚችሏቸውን ግቦች ለመከላከል ይረዳዎታል። 

የመዓዘን ምቶችን እና አየር ላይ የሚመጡ ኳሶች የሚሄቡበትን አቅጣጫ ለመቀየስ ወይም አደገኛ ሙከራዎችን ለማገድ ትክክለኛውን ጌዜ ጠብቀው ይዝለሉ። ይህ ስልት የተቃራኒ ቡድኑ ግብ ጠባቂ ጨዋታውን ድጋሚ በአግባቡ መጀመር እንዳይችል አስቸጋሪ ያደርግበታል። 

የመከላከል ክህሎት የግል ብቃት ላይ የተመሰረተ ብቻ አይደለም፣ የተቀናጀ የቡድን አደረጃጀትም ወሳኝነት አለው። አጥቂዎቹን አንድ በአንድ ምልክት ያድርጉ፣ እና ኳስ የያዘውን ተጫዋች እንዲከተል አንድ ተከላካይ ብቻ ይላኩ። ይህም መንገድ እንዲዘጉ እና ከትርምስ ያድንዎታል። 

በመጨረሻም ጉልበትዎን በአግባቡ ይጠቀሙ። ያለዓላማ በየቦታው አይሩጡ። ቅድሚያ ጨዋታውን ያንብቡ፣ ጥቃቶች ይከላከሉ፣ ተቃራኒ ቡድኖችን አስጊ ከሆኑ ቦታዎች ያስለቅቁ፣ በቃ! በዓላማ ሲንቀሳቀሱ የተቻኮሉ ውሳኔዎችን ከማድረግ ያድናሉ። 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !