icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

የሪማች የደረጃ አሰጣጥ እና ደረጃን ማሳደጊያ መንገዶች 

የሪማች፣ ስሎክላፕ (Sloclap) የእግር ኳስ ውድድር ሲሙሌተር የሙከራ ስሪቱን (beta) ከለቀቀ አንስቶ ብዙ ተጫዋቾችን መሳብ ችሏል። ሆኖም ግን የግል ክህሎት እና የተቀናጀ የቡድን አጨዋወት እኩል መስፈርት በሆነበት በዚህ ጌም የደረጃ አሰጣጥ ስርዓቱ እንዴት ነው የሚሰራው? ለሚለው ጥያቄ በዚህ አጋዥ መመሪያ መልሱን በዝርዝር አዘጋጅተንልዎታል። 

ሪማች ሌሎች አንጋፋ የውድድር ጌሞች እንደሚያደርጉት ፍትሐዊ እና ሚዛናዊ ግጥሚያዎችን ለማረጋገጥ የተዘጋጀ መዋቅርን ይከተላል። እያንዳንዱ ተጫዋች አንድ ገፀ-ባህሪን ብቻ የሚቆጣጠር በመሆኑ፣ ድል በግል ችሎታ ላይ ብቻ ሳይሆን በተቀናጀ የቡድን አጨዋወት ላይም የተመሰረተ ነው። ሲስተሙ ልክ እንደ ሮኬት ሊግ ወይም ኦቨርዋች የELO-style ደረጃ አሰጣጥን ይከተላል፣ ይህም ማለት ግጥሚያዎች ላይ በሚያስቆጥሯቸው ውጤቶች፣ አንዳንዴም በአፈፃፀምዎ ላይ በመመስረት ነጥቦችን ያገኛሉ ወይም ያጣሉ ማለት ነው። ይህም ሁልጊዜ ችሎታቸው ከእርስዎ ጋር ከሚመጣጠን ተጫዋቾች ጋር ግጥሚያዎችን እንዲያደርጉ እና ከጊዜ በኋላ ጥረትዎን የሚመጥን ሽልማት እንዲያገኙ ያስችሉዎታል። 

ስሎክላፕ (Sloclap) እስካሁን በይፋ የደረጃ አሰጣጥ ዝርዝር ባያወጣም፣ የሙከራ ጨዋታው (beta) እና ከተጫዋቾች የመጡ አስተያየቶች ጥሩ የደረጃ አሰጣጥ ሲስተም እንዳለው ይጠቁማሉ፡- 

  • ነሐስ (Bronze)፦ ሁሉም አዲስ ተጫዋቾች የሚጀምሩበት፣ የጀማሪዎች ደረጃ። 

  • ብር (Silver)፦ ዋና የሚባሉ የአጨዋወት ዘዴዎቹን የተረዱ መካከለኛ ደረጃ ተጫዋቾች። 

  • ወርቅ (Gold)፦ ጥሩ ልምድ ያካበቱ እና የተቀናጀ የቡድን ጨዋታን የተረዱ ጎበዝ ተጫዋቾች። 

  • ፕላቲኒየም (Platinum)፦ አሪፍ የአጨዋወት ዘዴን የሚከተሉ እና ንቃተ-ህሊናን የተቻሩ ተጫዋቾች። 

  • ዳይመንድ (Diamond)፦ ስልትን፣ ጊዜ አጠባበቅን እና አስደናቂ የአፈፅፀም ብቃትን ያጣመሩ፣ ባለከፍተኛ ደረጃ ተጫዋቾች። 

  • ኢሊት / ማስተር (Elite / Master)፦ ወደ ፕሮፌሽናል የተጠጉ፣ ፕሮፌሽናሎች እና ጌሙ ውስጥ አሉ የተባሉ እጅግ ምርጥ ተጫዋቾች። 

ይህ የደረጃ አሰጣጥ ሲስተም ሁሉም ተጫዋቾች እንደየጥረታቸው በራሳቸው ጊዜ ደረጃቸውን እንዲያሳድጉ እና ተጨባጭ ግቦችን እንዲያስቀምጡ የሚያስችል ነው። ወርቅ ደረጃ ላይ የደረሰ ተጫዋች ጨዋታውን በደንብ መረዳቱን፣ ፕላቲኒየም እና ከዚያ በላይ ደረጃ ላይ የሚገኝ ተጫዋች ደግሞ እጅግ ጥሩ የአጨዋወት ክህሎት ያለው እና በስልቶች የሚመራ ምርጥ ተጫዋች መሆኑን ያሳያሉ። 

የሚጫወቱት ለክብር፣ ለሽልማት ወይም ለዝና ይሁን፣ የሪማች የደረጃ ሞድ (ranked mode) ብቃትዎን ማሻሻል የሚችሉበት ግልጽ እና ጥረትዎን የሚክስ አካሄድን ይከተላል። 

 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !