icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

አዲሱ የፎርትናይት ምዕራፍ 6 ክፍል 4 የሚለቀቅበት ቀን እና አዳዲስ ጉዳዮች! 

ሰላም! እንደምን አላችሁ? ፎርትናይት ምዕራፍ 6 ክፍል 4 ሊጀመር በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ነው የቀሩት! እንደተለመደው ተጫዋቾች በጉጉት እየተጠባበቁ ይገኛሉ። እንዲሁም የታሪክ ጭብጡ ከሌላ ዓለማት የመጡ ፍጥረታት ላይ እና፣ ብዙ አስደናቂ የሆኑ ነገሮች ዙሪያ የሚያውጠነጥን በመሆኑ፣ በጣም አሪፍ እና ድንቅ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። 

እ.ኤ.አ. ሐሙስ ኦገስት 7፣ 2025 ምዕራፍ 3 ካለቀ በኋላ ሊጀመር ቀጠሮ ተይዞለታል። ክፍል 3 በፈረንሳይ አቆጣጠር 5፡59 AM ማለዳ ላይ የሚቋጭ ሲሆን፣ እንደተለመደው ዝመናው ከተደረገ በኋላ ሰርቨሮዎቹ የሚከፈቱ ይሆናል። 

የዚህ አዲስ ክፍል ጭብጥ ከሌላ ፕላኔት በመጡ ፍጥረታት የሚደረግ ወረራ ላይ ያውጠነጥናል። ብዙ ታማኝ ምንጮች እንዳረጋገጡት ከሆነ ደሴቲቱ ሙሉ በሙሉ የምትቀየር ሲሆን፣ አዲስ በኬሚካል የተበከሉ አካባቢዎች፣ የባዕድ ፍጥረታት ምሽጎች፣ አልፎ ተርፎም ወድቀው የተከሰከሱ የጠፈር መንኮራኩሮች እንደሚኖሩም ጠቁመዋል። በአጠቃላይ ይዘቱ በቴክኖሎጂ የበለጸገ እና ምስጢራዊ ኩነቶች ላይ ያተኮረ እና ሳይንሳዊ ልብወለድን (sci-fi) መሠረት በማድረግ የተሰራ ነው። 

Battle Pass እንደተለመደው ከዚህ ጭብጥ ጋር የሚሄድ ሲሆን፣ ከሌላ ዓለም የመጡ ፍጥረታቱን መሠረት ያደረጉ ማጌጫዎች (skins)፣ ከባድ የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች እና “close encounters of the third kind” ጋር ተቀራራቢነት ያላቸው እንቅስቃሴዎች (emotes) ይኖራሉ። እንደ ቴሌፖርት፣ መንሳፈፍ ወይም የኢነርጂ ጥቃቶችን የመሳሰሉ አዳዲስ አስገራሚ ክህሎቶችን የምናገኝበት ዕድል ይኖራል። እንዲሁም ፕላዝማ የጦር መሳሪያዎች፣ ከፍተኛ አቅም ያላቸው መግብሮች (advanced gadgets) . . . በአጭሩ መደበኛ ስልቶችን ሙሉ በሙሉ በሚቀይሩ አማራጮች የተሞላ ነው። 

ሌላው አዲስ ጉዳይ፣ ከOne Piece ጋር ኅብረት ማድረጉ ነው። አዎ! ሉፊ እና ቡድኑ፣ ከራሳቸው አልባሳት፣ ማስጌጫዎች እና ልዩ ተልዕኮዎች ጋር ፎርትናይትን ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል። እውን ነው! ማንም ያልጠበቀው ትልቅ ዜና ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደዚህ ዓይነት ትብብሮች የፎርትናይት መለያ ሆነዋል፤ ይሄኛው ደግሞ እጅግ ተወዳጅ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም። 

ካርታውም ከሌላ ፕላኔት ከመጡት ባዕድ ፍጥረታት ጋር በሚጣጣም መልኩ የሚቀየር ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ የተቀየሩ ቦታዎች፣ ተለዋዋጭ ዝግጅቶች እና ምናልባትም አስደናቂ የሆነ የመክፈቻ ዝግጅትም ይኖራል ተብሎም ይጠበቃል። ምንጫቸው የማይታወቅ ጭምጭምታዎች እንዳሉት ከሆነ፤ ቀጥታ ስርጭት ላይ የሚደረጉ ወረራዎች፣ ሲኒማቲክ ምስሎች፣ ልዩ ተልዕኮዎች እና ምናልባትም የባዕድ ፍጥረታቱ የመጀመሪያ ግንኙነት’ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !