
ሮብሎክስ ላይ Round Sixን ይጫወታሉ? እንግዲያውስ የምስራች አለን! እስከ እ.ኤ.አ ጁላይ፣ 2025 ድረስ ሊጠቀሟቸው የሚችሉ ኮዶችን አዘጋጅተንልዎታል! እነዚህ ኮዶች የጌሙ መገበያያ ገንዘብ የሆነውን "ዎንስ" ያስገኙልዎታል። ረጅም ሰዓታትን ሳይለፉ ደረጃዎን ማሳደግ ከፈለጉ፣ ዛሬውኑ ይሞክሯቸው።
እስካሁን ባለን መረጃ እንደሚሰሩ ያረጋገጥናቸው 3 ኮዶች፡-
3kLikes – 40,000 ዎንስ ያስገኝልዎታል።
ILOVEROUNDSIX – 10,000 ዎንስ አካውንትዎ ላይ ይጨምርልዎታል።
UPDATE1 – ተጨማሪ 10,000 ዎንስ በነጻ ያገኛሉ።
ይፍጠኑ ግን፣ ኮዶቹ እንደ አብዛኞቹ የሮብሎክስ ጌሞች፣ በተለይ ከአዲስ ዝመና ወይም ልዩ ዝግጅት በኃላ ያለምንም ማስጠንቀቂያ የአገልግሎት ጊዜያቸው ሊያልቅ ይችላል። እንዲሁም ድንገት ኮዱ ካልሰራ፣ ወይ ቀድመው ተጠቅመውታል ወይም ተሰርዞ ሊሆን ይችላል።
ኮዶቹን እንዴት መጠቀም እንዳለብዎ ካላወቁ፣ እነዚህን ሂደቶች ይከተሉ፦
1. Round Sixን ይክፈቱ።
2. በስክሪኑ በግራ በኩል የሚገኘውን “Codes” የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ።
3. ኮዱን ይፃፉ ወይም copy፣ paste በማድረግ ያስገቡ።
4. Confirm የሚለውን ቁልፍ በመጫን ይጨርሱ።
ያስታውሱ፡- ይህን ከማድረግዎ በፊት ግን ሮብሎክስ ላይ የሚገኘውን “ROUND SIX FANS” የተባለ ግሩፕ መቀላቀል እንዳለብዎ አይርሱ። ካልተቀላቀሉ ኮዶቹ አይሰሩም።
የሰበሰቧችውን ዎንሶች ማስጌጫዎችን ለመግዛት፣ አዲስ ይዘቶችን ለማስከፈት ወይም ሂደትዎን ለማፋጠን መጠቀም ይችላሉ። በተለይ ደግሞ ለጌሙ አዲስ ከሆኑ ወይም በአጭር ጊዜ ደረጃዎን ማሳደግ ከፈለጉ እጅግ ይጠቅሙዎታል።
ማስታወሻ፡- አብዛኛውን ጊዜ ትልቅ update ሲኖር ወይም የበዓላት ሰሞን የጌሙ አዘጋጆች አዳዲስ ኮዶችን ስለሚለቀቁ መከታተልዎን አይርሱ። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ለሚያጋጥሙ ብልሽቶች (bugs) ወይም ያልተጠበቁ የጥገና መቋረጦች፣ ለተጫዋቾች በካሳ መልክ ሊለቀቁ ይችላሉ።
መልካም ዕድል!