
KPop Demon Hunters እ.ኤ.አ. ጁን 20፣ 2025 ኔትፍሊክስ ላይ ከተጀመረ ጀምሮ ዓለም አቀፍ ክስተት መሆኑን አስመስክሯል። ይህ የኮሪያውያን አኒሜሽን ፊልም፣ በሶኒ ፒክቸርስ አኒሜሽን እና በበርካታ ታዋቂ የK-pop ኮከቦች ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን፣ ሩሚ፣ ሚራ እና ዞይ የተባሉ ዝነኞችን ስለያዘ Huntr/x – ስለተባለ ምናባዊ ቡድን የሚዳሰስ ፊልም ነው። እነዚህ ዝነኞች ሁለት ዓይነት ሕይወት የሚመሩ ሲሆን፣ ቀን ላይ ኮከብ ሙዚቀኞች፣ በሌሊት ደግሞ አጋንንት አዳኞች ናቸው። ይህ በአስደናቂ ድርጊቶች፣ በሙዚቃዊ ትርኢቶች የተሞላ እና የwebtoonsን ግራፊክ ስታይል መነሻ በማድረግ የተሰራ ፊልም በአጭር ጊዜያት የዓለም አቀፍ ተመልካቾችን ልብ ከማረክ አልፎ፣ በ41 አገሮች የኔትፍሊክስ ከፍተኛ 10 ውስጥ መመደብ ችሏል።
KPop Demon Hunters ስክሪን ላይ ከነበረው ስኬት በተጨማሪ የሙዚቃውን ዓለምም ተቆጣጥሯል። እንዲሁም እንደ Blackpink እና Twice ያሉ ታላላቅ አርቲስቶችን ያሳተፈው ኦርጅናል የፊልም ማጀቢያ ሙዚቃቸው የቢልቦርድ ዝርዝር ላይ በመካተት የፕሮጀክቱን ዓለም አቀፋዊነት ማረጋገጥ ችሏል።
ይህን ታላቅ ስኬት ተከትሎም በርካታ የኮሪያ እና ዓለም አቀፍ ስቱዲዮዎች ፊልሙን ፕሮጀክቶቻቸው ላይ ለማካተት በመረባረብ ላይ ይገኛሉ። ሁለት መንገዶች የቀረቡ ሲሆን፣ አንደኛው Huntr/x ላይ ሙሉ በሙሉ ያተኮረ ቪዲዮ ጌም ማዘጋጀት ወይም ደግሞ፣ ልዩ ዝግጅቶችን ወይም ልዩ ይዘቶችን (ገፀ-ባሕሪያት፣ ሙዚቃዎች፣ መለዋወጫዎች፣ ወዘተ) በመጠቀም ከሌሎች አንጋፋ ጌሞች ጋር በመተባበር ለመስራት ታስቧል።
ምርጫ ውስጥ ከገቡት አንጋፋ ጌሞች መካከል ፎርትናይት በተደጋጋሚ ተጠቅሷል። እንደሚታወቀው Epic Games’ Battle Royale ታዋቂ ትብብሮችን፣ ምናባዊ ኮንሰርቶችን፣ ዝነኞችን በእንግድነት በመጋበዝ እና ታዋቂ ፍራንቻይዞችን መሠረት ያደረጉ አልባሳትን በማዘጋጀት ይታወቃል። ከአሪያና ግራንዴ፣ ኤሚኒዪም እና ሃትሱኔ ሚኩ በኃላ በቅርቡ ሩሚ፣ ሚራ እና ዞይ የፎርትናይት ደሴቶች ላይ ሊታዩ እንደሚችሉ ተጠቁሟል። SamLeakss በX አካውንቱ ላይ እንዳጋራው ከሆነ Epic Games እና የKPop Demon Hunters ባለቤቶች ስለጉዳዩ ቀድሞውኑ መወያየት መጀመራቸን ገልጿል።
የፎርትናይት ዘመናዊነት ከፊልሙ ጋር ፍጹም እንደሚጣጣም ጥርጥር የለውም። አልባሳት፣ አስደናቂ ኮንሰርቶች፣ ፌስቲቫል ሞድ ውስጥ ያሉ ስሜት መግለጫ እንቅስቃሴዎች (emotes)፣ የታሪክ ጭብጥን መሠረት ያደረጉ ተልዕኮዎች . . . ምን አለፋችሁ እጅግ ብዙ ብዙ . . . ይህን አስመልክቶም ብዙኋን ጉጉታቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ። ማህበራዊ ሚዲያዎችም በአድናቂዎች ስዕል (fan art)፣ ፅንሰ-ሀሳቦች (concepts) እና መላምቶች በመጥለቅለቅ ላይ ይገኛሉ።