icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ዋን ፒስ፡ ምዕራፍ 1154 መቼ ነው የሚለቀቀው እና በነፃስ የት ማንበብ ይቻላል? 

በዚህ ሳምንት ሲጠበቅ የነበረው የዋን ፒስ ክፍል 1154 የማይለቀቅ መሆኑ ተሰምቷል፣ የOne Piece አድናቂዎች በትዕግስት መጠበቅ ሳይኖርባቸው አይቀርም። አዎን፣ እንደ ኤልባፍ ያለ ውስብስብ እና አጓጊ ታሪክ መኃል እንኳን ማንጋው ድንገት እረፍት ሊወስድ ይችላል። ስለዚህ፣ የዚህ ድንገተኛ የእረፍት ዜና ምክንያት ምንድን ነው? ከሁሉም በላይ ደግሞ ታሪኩ ላይ ቀጥሎ የሚከሰተውን ጉዳይ መቼ ማንበብ እንችላለን? ለሚሉት ጥያቄዎች ቀጥለን መልሶች አዘጋጅተንላችኋል። 

ይህ ተከታታይ መጽሐፍ እ.ኤ.አ በ1997 ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ኦዳ በሚያስደንቅ እና ወጥ በሆነ መልኩ ታሪኩን ለአንባቢዎች ሲያቀርብ ቆይቷል። ነገር ግን ይህን የመሰለ አንጋፋ ማንጋ እንኳን ያልታሰቡ እክሎች ሊያጋጥሙት ይችላሉ። በዚህ ሳምንት ዊክሊ ሾነን ጃምፕ አዲስ የOne Piece ክፍል አያቀርብም፥ ይህም የሆነው በጊዜ ማጠር ወይም ስህተት አጋጥሞ አይደለም፣ ይህ የሆነበት ምክንያት እረፍት በማስፈለጉ ነው። በየሳምንቱ ከሚወጡ ምዕራፎች፣ ተከታታይ የቀጥታ ስርጭቶች፣ ቃለ-መጠይቆች፣ ዝግጅቶች እና ለሦስት አስርት ዓመታት የሚጠጋ የማያቋርጥ ሥራ፣ ኦዳ እረፍት ለመውሰድ መወሰኑ አጥጋቢ ምክንያት ነው፣ ይበልጥ ደግሞ አጥጋቢ የሚያደርገው እድሜው ከ50 በላይ መሆኑ ነው። 

አንዳንድ አድናቂዎችን ያስገረመው ይህ እረፍት ከሶስት ሳምንታት ዑደቱ ይልቅ ከሁለት ምዕራፎች በኋላ መከሰቱ ነው። ነገር ግን እረፍት መወሰዱ የጤና ችግርን ከመጋፈጥ የሚሻል እና አሳማኝ ውሳኔ ነው። ስለ ሎኪ ታሪክ፣ ስለ ንጉሣዊ ቤተሰብ እሰጣገባ እና ስለ ዓለም መንግስታት ያዘጋጃቸው በሙሉ በጥልቅ ዝርዝሮች የተሞሉ ናቸው። ታሪኩ ጥራቱን የጠበቀ የሆነበት ምክንያትም ኦዳ ነገሮችን በትክክል ለመስራት ሰፊ ጊዜ ወስዶ ማዘጋጀት በመቻሉ ነው። 

ግን አያስቡ! እረፍቱ ይህን ያህል ረጅም አይደለም። ክፍል 1154 እ.ኤ.አ ጁላይ 13፣ 2025 ላይ በይፋ ይለቀቃል። በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ አድናቂዎች ጋር በተመሳሳይ ጊዜ Manga Plus ወይም Viz Media ላይ በነፃ ማንበብ ይችላሉ። ትዕግስቱ ለሌላችሁ ደግሞ አፈትልከው የሚወጡ መረጃዎች እንደተለመደው እ.ኤ.አ ሐሙስ ጁላይ 10፣ 2025 ላይ ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። 

እርግጥ ነው፣ ሊያበሳጭ ይችላል፣ ያለፈው ክፍል እጅግ ልብ በሚያንጠለጥል መልኩ ነበር ያለቀው። ስለ ንጉስ ሃራልድ፣ የዓለም መንግስታት ድብቅ ሴራዎች፣ እና ስለ ሎኪ ያለፈ ታሪክ ቀጣዩን ክፍል እጅግ ልብ አንጠልጣይ አድርገውታል። ብዙዎች ቀጣዩን ክፍል ለመቀጠል ተስፋ አድርገው ነበር፣ ሆኖም አንድ ሳምንት ማለት ነገ ነች፣ በትዕግስት ይጠብቁ። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !