
EA Sports FC 26 እ.ኤ.አ. ሴፕቴምበር 26፣ 2025 ላይ የሚለቀቅ ሲሆን አስቀድመው ጌሙን ለሚያዝዙ ተጫዋቾችም ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅሞችን የሚያቀርብ ይሆናል። ቀድሞ ከመጫወት እድል እና ከUltimate Team ጉርሻዎች እስከ Career እና Clubs ሞዶች ላይ ስለሚገኙ ጥቅሞች፣ እንዲሁም በFC 25 ላይ ስለሚገኙ ልዩ ሽልማቶች፣ ከመግዛትዎ በፊት ቀድሞ ማወቅ ተገቢ ነው።
ሁሉም ፕላትፎርሞች ላይ Standard (€79.99) እና Ultimate (€109.99) የተሰኙ ሁለት አይነት እትሞች ይኖራሉ። Ultimate Edition ጌሙ ከመለቀቁ 7 ቀናት በፊት (ከሴፕቴምበር 19 ጀምሮ) መጫወት ከማስቻሉም በላይ (በተለይ ለUltimate Team) እጅግ በርካታ አስደሳች ጥቅሞችን ይሰጣል። ሆኖም ግን፣ አብዛኛዎቹ ቦነሶች ከNintendo Switch ወይም Switch 2 ቨርዥኖች ጋር የማይጣጣሙ መሆናቸውን ልብ ሊሉ ይገባል።
እንደእትሞቹ አይነት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ማግኘት ይችላሉ፡-
ቀድሞ የመጫወት እድል (ሴፕቴምበር 19)
FC 25 ላይ የማይሸጡ 93+ Icon Player (ከSwitch በስተቀር)
FC 26 ላይ የCareer Mode 3 ታሪካዊ Icons
ከSeason 1 ባለ 5 ኮከብ አሰልጣኝ እና ስካውት
ተጨማሪ የLive Manager ተግዳሮቶች
1 Archetype Consumable (Standard)
260,000 የክለብ ነጥቦች + ሁለት እጥፍ XP ለ10 ጨዋታዎች (Standard)
ክለቦች ውስጥ፣ ለProዎ ተጨማሪ የስብዕና ነጥቦች
በ2 ወራት የሚዳረሱ 6,000 FC ነጥቦች (Ultimate)
ጅማሮ ላይ የሚገኝ፣ 1 የማይሸጥ FUT Icon (Ultimate)
ለሚከፈቱ ይዘቶች Premium Season 1 Pass (Ultimate)
በUltimate Team ውስጥ ልዩ እድገት (Ultimate)
FC 25 ጉርሻዎች፡- የተጫዋች ማሻሻያ + ከ5 Icons ውስጥ 1 የመምረጥ እድል (Ultimate only)
እነዚህን ሁሉ ጥቅሞች ለማግኘት ከኦገስት 26 በፊት ጌሙን ማዘዝ ይኖርብዎታል። ሁሉም ይዘቶች ከEA አካውንትዎ ጋር የተገናኙ በመሆናቸው የኢንተርኔት ግንኙነትን ይፈልጋሉ።
በአጭሩ፣ Ultimate Team ውስጥ ይበልጥ ተጠቃሚ መሆን ወይም የCareer mode እድገትዎን ማሳደግ ከፈለጉ፣ Ultimate Edition፣ በተለይ በቋሚነት ለሚጫወቱ ወይም የፉክክር መንፈስ ለአላቸው ተጫዋቾች ብዙ አስደናቂ ጥቅሞችን ያስገኛል።