
ጋሪስ ሞድ (GMod) ተወዳጅ ከሆኑ የኮምፒውተር ጌሞች መካከል አንዱ በመሆን በ2025ም ዝናውን ማስጠበቅ የቻለ እና ተጫዋቾች እንደምርጫቸው ሊያስተካክሉት የሚችሉት Sandbox ጌም ነው።
ይህንን ጌም መጫወት የሚችሉበት ቀላል መንገድ፣ የSteam ፕላትፎርምን መጠቀም ሲሆን፣ በቅድሚያ የSteam አካውንት ይክፈቱ እና ከSteam መደብር ጋሪስ ሞድን በ9.99 ዩሮ ይግዙ፤ በመቀጠል ላይብረሪዎን በመክፈት ጌሙን ያውርዱ እና ኮምፒውተርዎ ላይ ይጫኑት። ሂደቱ ቀላል እና በራሱ የሚካሄድ በመሆኑ ምንም የሚያደናግር ሂደት አያግጥምዎትም።
በሚጫወቱበት ወቅት የምስል መቆራረጥ እክሎችን ለማስወገድ፣ የካውንተር-ስትራይክ፡ ሶርስ ፋይልን እንዲጭኑ ይመከራል። ይህ የሚመከርበት ምክንያትም፣ ይህ ጌም የጋሪስ ሞድ ላይ፣ በተለይ እንደ "Murder" ወይም "Trouble in Terrorist Town" ላሉ ሞዶች የሚሆኑ በርካታ ቴክስቸሮችን እና ሞዴሎችን የሚያቀርብ በመሆኑ ነው። ጭነው እንደጨረሱ ጋሪስ ሞድን በSteam በኩል ይክፈቱት፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲከፍቱት አንዳንድ ዝመናዎችን ሊጭን ይችላል። እንደ ኮምፒውተርዎ አቅም ግራፊክስ እና የድምፅ ቅንብሮችን ቀድመው ቢያስተካከሉ ይመረጣል።
ጌሙ ብዙ ተጫዋቾች አንድ ላይ መጫወት የሚችሉባቸው የተለያዩ ሞዶች ያሉት ሲሆን፣ ሜኑው ላይ "Multiplayer" የሚለውን በመጫን ማግኘት እና ሰርቨሮችን በስም ወይም በሞዳቸው (Murder፣ TTT፣ Sandbox ወዘተ) በመፈለግ መቀላቀል ይችላሉ። አንድ ሰርቨርን ሲቀላቀሉ ጋሪስ ሞድ አስፈላጊ ነገሮችን በሙሉ በራሱ ስለሚያወርድ፣ እርስዎ ምንም ማድረግ አይጠበቅብዎትም። Sandbox ሞድም ለብቻዎ መጫወት ስለሚያስችልዎ ጌሙን ቀድመው መሞከር ወይም በነፃነት መገንባት ያስችልዎታል።
ሞዶች ወይም "addons" የጋሪስ ሞድ የጀርብ አጥንት ናቸው! አድ-አኖችን ለመጫን ወደ Steam Workshop በመሄድ የሚፈልጉትን መርጠው subscribe ማድረግ ይችላሉ፤ አስፈላጊ ከሆነ ደግሞ ጌሙን ድጋሚ ሲያስጀምሩት በራሳቸው መስራት ይጀምራሉ። ከጓደኞቾችዎ ጋር መጫወት ከፈለጉ ደግሞ፣ የራስዎን ሰርቨር መከራየት ወይም በቀጥታ ኮምፒውተርዎ ላይ በመፍጠር መጫወት ይችላሉ። ሁለተኛው አማራጭ ይሻለኛል ካሉ ግን ሞዶቹን፣ ካርታዎቹን እና አድ-ኦኖቹን በራስዎ ማስተካከል ይጠበቅብዎታል።
በመጨረሻም፣ ጥሩ እና አስደሳች ጊዜ ማሳለፍ እንዲችሉ ጌምዎን እና አድ-ኦኖቹን በየጊዜው ያዘምኑ፣ የተለያዩ የጌም ኮሚኒቲዎች ውስጥ ይሳተፉ፣ እንዲሁም የሰሯቸውን ፕሮጀክቶች back up በማድረግ እንዲያስቀምጡ እንመክራለን።
መልካም ጨዋታ ተመኘንላችሁ!