ባትልፊልድ 6 ኮምፒውተር ላይ ለመጫወት ሁለት ዓይነት ቅድመ-ሁኔታዎች አሉ። አንደኛው መሠረታዊ መስፈርቶችን በማሟላት ጌሙን መጫወት የሚችሉበት መደበኛ ወይም አስፈላጊ ቅድመ-ሁኔታ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ጥራት ያለው ግራፊክስ እና እንከን የለሽ አፈጻጸም ማግኘት የሚያስችል ቅድመ-ሁኔታ ነው።
መደበኛው ወይም አስፈላጊው መስፈርት (Minimum configuration) – በ1080p ጥራት በሰከንድ 30 ፍሬሞች ማስተናገድ የሚችል ሲሆን፡-
ኦፐሬቲንግ ሲስተም (OS)፦ ዊንዶውስ 10 64-ቢት ከDirectX 12 ጋር
ፕሮሰሰር (CPU)፦ ኢንቴል ኮር i5-8400 ወይም AMD Ryzen 5 2600
ራም (RAM)፦ 16 ጊጋባይት ዱዋል ቻናል (2133 MHz ቢጠቀሙ ይመከራል)
ግራፊክስ ካርድ (GPU)፦ Nvidia RTX 2060፣ AMD RX 5600 X፣, ወይም Intel Arc A380 (6 ጊጋባይት VRAM)
ማከማቻ (Storage)፦ መደበኛ ሃርድ ድራይቭ (HDD) ላይ 55–75 ጊጋባይት
ደህንነት (Security)፦ TPM 2.0፣ UEFI Secure Boot፣ HVCI እና VBS የሚቀበል
ኢንተርኔት (Internet)፦ ያስፈልጋል
ይህም ከ2019–2020 የተሰሩ መካከለኛ ኮምፒውተሮች የሚያሟሉት መስፈርት በመሆኑ ኦንላይን ጌሙን መጫወት ያስችልዎታል፣ ሆኖም ግን የግራፊክስ ጥራቱ ያን ያህል አይደለም።
ሁለተኛው እና ቢጠቀሙት የሚመከረው ቅድመ-ሁኔታ (Recommended configuration) – በ1440p ጥራት በሰከንድ 60 ፍሬሞች (ወይም በተሻለ ሁኔታ 1080p በሰከንድ ከ80 ፍሬሞች በላይ) በሆነ ጥራት ለመጫወት የሚከተሉት ያስፈልጋሉ፡-
ኦፐሬቲንግ ሲስተም (OS)፦ ዊንዶውስ 11 64-ቢት
ፕሮሰሰር (CPU)፦ ኢንቴል ኮር i7-10700 ወይም AMD Ryzen 7 3700X
ራም (RAM)፦ 16 ጊጋባይት ዱዋል ቻናል (3200 MHz ቢጠቀሙ ይመከራል)
ግራፊክስ ካርድ (GPU)፦ Nvidia RTX 3060 Ti፣ AMD RX 6700 XT፣ ወይም Intel Arc B580 (8 ጊጋባይት VRAM)
ማከማቻ (Storage)፦ በፍጥነት ሎድ እንዲያረግ፣ ኤስኤስዲ (SSD) 75 ጊጋባይት
ደህንነት (Security)፦ TPM 2.0፣ UEFI Secure Boot, HVCI እና VBS የሚቀበል
ኢንተርኔት (Internet)፦ ያስፈልጋል
ኮምፒውተርዎ ቢያንስ RTX 2060 ወይም ተመጣጣኝ፣ 16 ጊጋባይት ራም፣ እና ከi5-8400/Ryzen 5 2600 ጋር ተቀራራቢነት ያለው ፕሮሰሰር ካለው፣ አነስተኛውን setting በመጠቀም ጌሙን መጫወት ይችላሉ። ነገር ግን የተሟላ እና ጥራት ያለው ምስል ለማግኘት እና ያለምንም እንከን መጫወት እንዲችሉ ሁለተኛውን አማራጭ ቢጠቀሙ ይመከራል።
መልካም ጨዋታ ተመኘን!