ከብዙ ዓመታት ጥበቃ እና ከተጫዋቾች ተደጋጋሚ ጉትጎታ በኋላ፣ ፕሮክሲሚቲ ቻት ፎርትናይት ላይ የሚካተትበት ቀን በስተመጨረሻ ደርሷል። ይሄ አዲስ አማራጭ የግንኙነት ልውውጦችን እጅግ ቀላል እና አዝናኝ በማድረግ የBattle Royale ድባብን ሙሉ በሙሉ ሊቀይር እንደሚችል ትልቅ ተስፋ ተጥሎበታል።
ይህ አማራጭ በአቅራቢያዎ የሚገኙ ተጫዋቾችን ብቻ መሰማማት የሚያስችልዎ ሲሆን፣ የቡድን አጋሮችዎ፣ ጠላቶችዎ ወይም እርስዎ የሚገኙበት ሕንፃ ውስጥ የሚገኙ የማያውቋቸው ሰዎች ቢሆኑም፣ ድምፃቸውን የሚሰሙት በቅርብ ርቀት ላይ ሲገኙ ብቻ ነው። ይህ ዜና ከተሰማ ጀምሮ ከተጨዋቾች የደስታ እስከ በቃ! መተራመሳችን ነው የሚሉ ምላሾች ተሰምተዋል። ፕሮክሲሚቲ ቻት የተቀናጀ የቡድን ስራን፣ ማዘናጋትን ወይም ድንገተኛ ጥምረትን መፍጠር የሚያስችል ቢሆንም፣ እንደ መሳዳደብ፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲመጡ በፍርሃት መጮኽን፣ መካካድን ወይም ጠላትን ወደ ወጥመድ ለማስገባት በዘፈን መሳብን እና ለመሳሰሉ የማይረቡ ሁኔታዎችም በር ይከፍታል። የCreative mode እና UEFN ተጫዋቾችም የድምፅ ቻት ራሱን የቻለ መሣሪያ የሚሆንባቸውን ሁኔታዎችን አስቀድመው በማሰብ ላይ ይገኛሉ።
Epic Games ሊከሰቱ ስለሚችሉ ስጋቶች ቀድሞውኑ ግንዛቤ በመያዙ፣ የቅድመ ጥንቃቄ ሂደቶችን አስቀምጧል። የወላጅ መቆጣጠሪያዎች አሁንም ተግባራዊ የሚሆኑ ሲሆን፣ በወላጆች ማይክሮፎናቸው የታገደ ማንኛውም ተጫዋቾች ይህን አማራጭ እንዳይጠቀሙ እገዳ ይጣልባቸዋል። በተጨማሪም፣ ትንኮሳን መቆጣጠር የሚያስችል የአቤቱታ ማቅረቢያ አማራጭም ተካቷል።
ይህን አማርጭ ቀድሞ የመጠቀም እድል በተሰጠ ጥቂት ቀናት ውስጥ፣ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ተጫዋቾች ሰዎችን ሲያስደነግጡ፣ እርስ በርስ ሲያሾፉ እና ሆድ የሚያቆስሉ ሳቆችን በሚያሳዩ ቪዲዮዎች ተጥለቅልቋል። ፎርትናይት ላይ መሳጭ፣ አዝናኝ እና ወሰን የሌለውን ፈጠራን ያጣመረ አዲስ ዘመን እየመጣ ይመስላል፣ ከዚህ በኋላ እያንዳንዱ ጨዋታ እጅግ በሚያስቁ እና አዝናኝ ሁኔታዎች የሚታጀብ መሆኑ አይቀሬ ነው… ይህ ደግሞ ማንም ሊያመልጠው አይገባም።