እ.ኤ.አ ኦገስት 7፣ 2025 ላይ የተጀመረው የፎርትናይት ምዕራፍ 6 ክፍል 4 እስካሁን ከቀረቡት ሁሉ እጅግ አስደናቂው ነው ማለት ይቻላል! "Shock 'N Awesome" የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ክፍል፣ የደሴቲቱን መልክዓ ምድር፣ የጨዋታ ተሞክሮውን እና አጠቃላይ Battle Royaleን ሙሉ በሙሉ የሚቀይሩ እጅግ ግዙፍ በሆኑ ነፍሳቶች የሚደረግ ወረራን ያቀርባል።
እንዲሁም፣ The Hive፣ Swarmy Stash፣ O.X.R. HQ፣ Ranger's Ruin እና Demon’s Debris የተባሉ አምስት ዋና ዋና ቦታዎችም ተካተዋል። በምላሹም፣ በርካታ ታዋቂ ቦታዎች ተቀንሰዋል። አሁን ላይ የካርታው አንዳንድ ክፍሎች በትላልቅ ጎጆዎች እና በድብቅ ላቦራቶሪዎች ተወረዋል፣ እያንዳንዳቸውም ለማሸነፍ አዳጋች በሆኑ መሰናክሎች የተሞሉ ናቸው።
ሶስት የነፍሳት ዓይነቶች ግጥሚያዎችን የሚያናውጡ ሲሆን፣ የመጀመሪያዎቹ Swarmers የተባሉት እጅግ ፈጣን እና ደካማ ቢሆኑም፣ እጅግ በጣም ብዙ እና አንድ ተጫዋችን በሰከንዶች ውስጥ የመውረር አቅም አላቸው። Bombers በመባል የሚጠሩት ደግሞ ጎጆዎች አካባቢ በመደበቅ ዝንጉ ተጫዋቾች ላይ ጥቃት የሚጥሉ ናቸው። ሶስተኛዎቹ Queens ሲሆኑ፣ እያንዳንዱ ዋና የሚባሉ ጎጆዎች የሚጠበቁት በእነዚህ አስፈሪ ነፍሳቶች ነው። እነዚህን ያሸነፉ ተጫዋቾች፣ ልዩ የጦር መሳሪያዎችን ወይም ከፍተኛ ዝላይ፣ ተጨማሪ ፍጥነት ወይም ወድቀው ጉዳት እንዳይደርስባቸው አዳዲስ ችሎታዎችን የሚሰጡ ሜዳሊያዎችን ይሸለማሉ።
የተወሰሱ አስደናቂ የጦር መሳሪያዎችም የሚገኙ ሲሆን፣ Bug Blaster ፈንጂ፣ እንደሚነጥር ኳስ መንቀሳቀስ የሚያስችል Roly Poly፣ Leadspitter 3000 አነስተኛ ሽጉጥ፣ Sweeper Shotgun፣ O.X.R. ጠመንጃ፣ እና Swarmstrike ተወንጫፊ ሮኬት የሚገኙ ሲሆን፣ የPower Rangers’ Blade Blasterም፣ የሲዝኑ መገባደጃ ላይ የሚካተት ይሆናል። እንዲሁም አዲሱ O.X.R. የደረጃ ሰንጠረዥም፣ በተጫዋቾች የጨዋታ አፈጻጸም ላይ በመመስረት ተጫዋቾች ቀስ በቀስ Exotic እና Mythic የጦር መሣሪያዎችን እንዲከፍቱ ያስችላቸዋል።
Battle Passም አንጋፋ ትብብሮችን በውስጡ አካቷል። የPower Rangers ቶሚ ኦሊቨርን እና ምስጢራዊው የMegazord ማስጌጫን ጨምሮ፣ ከHalo Spartans እና ለዚህ አስደናቂ ጦርነት ከተፈጠሩ አዳዲስ ገጸ-ባሕሪዎች ጎን ጦርነቱን ይቀላቀላሉ። ይህም የድሮ ትውስታዎችን እና ሳይንሳዊ ልብ-ወለድን በማዋሃድ ሲዝኑን ይበልጥ አስደሳች ቃና እንዲኖረወድርጎታል።
ይህ ሲዝን፣ ሊቆጣጠሯቸው የሚችሉ ጥገኛ ተውሳኮችን ወይም ጊዜያዊ የነፍሳት ለውጦችን፣ አፈጻጸምን መሠረት ያደረጉ የብቃት ጉርሻዎችን እና ከትልቅ የጠላት መሪዎች ጋር ውጊያዎችን፣ ያካተተ አስደናቂ ተሞክሮን ለተጫዋቾች የሚያቀርብ ልዩ ሲዝን ነው። የቀጥታ ስርጭት አዘጋጆች እና ይዘት ፈጣሪዎች፣ ለዚህ በትርምስ እና በጀብዶች የተሞላ ሲዝን አዳዲስ ስልቶችን በማዘጋጀታቸውን ከአሁኑ ጀመረዋል።