icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ባትልፊልድ 6 ላይ ከP18 ጋር አብረው ሊጠቀሟቸው የሚችሉ ምርጥ ሚናዎች እና ማሻሻያዎች 

የባትልፊልድ 6 የሙከራ ስሪት ውስጥ ከሚገኙ የጦር መሳሪያዎች መካከል፣ P18 በመባል የሚታወቀው መሳሪያ ከሁሉም የላቀ አቅም እና ጉልበትን የተላበሰ ነው። እንዲሁም ሁሉም ሚናዎች ውስጥ በመደበኛነት መገኘቱ፣ በተኩስ ወቅት አለመንገጫገጩ፣ የማይዛነፈ የማነጣጠር አቅሙ እና ለአጭር ርቀት ውጊያዎች ላይ ሁነኛ መሆኑ የብዙሃን ቁጥር አንድ አማራጭ መሆን አስችሎታል። ሆኖም ግን ይህንን መሳሪያ በአግባቡ መጠቀም እና ይበልጥ ውጤታማ መሆን ከፈለጉ፣ አባሪ ማሻሻያዎችን በማከል ሊጠቀሙት ይገባል። 

ማሻሻያ ሲስተሙ 100 ነጥቦችን የሚይዝ ሲሆን፣ እያንዳንዱም አባሪ ማሻሻያ የራሱ የሆነ ዋጋ አለው። ለP18 የሚሆኑ ምርጥ አባሪ ማሻሻያዎች የሚከተሉት ናቸው፡- መደበኛ ድምጽ ማፈኛ (20 ነጥብ)፣ ፊን 99 ሚ.ሜ አፈሙዝ (20 ነጥብ)፣ ባለ 17 ዙር የጥይት ካርታ (5 ነጥብ)፣ ሙሉ ብረት ለበስ ጥይቶች (5 ነጥብ) እና ባለ1x እይታ ሚኒ ፍሌክስ (10 ነጥብ) ናቸው። እነዚህን አባሪ ማሻሻያዎች ከP18 መሳሪያዎ ጋር አብረው ሲጠቀሙ፣ የአጭር እና የመካከለኛ ርቀት ውጊያዎች ላይ ፍጹም የማይንገጫገጭ፣ ወጥ እና ሁለገብ ውጤትን ያገኛሉ። 

ሚናዎችንም በተመለከተ፣ የአጨዋወት ስልትዎን ከP18 ጋር በማመጣጠን እንደሚከተለው ያስተካክሉ፦ 

  • ጥቃት (Assault)፦ ከሩጫ ወደ ተኩስ አቋም በፍጥነት መሸጋገር፣ እና የጢስ ቦምብን በመጠቀም ጠላቶች ባልጠበቁት ሰዓት ጥቃት ማድረስ ይችላሉ። 

  • ኢንጂነር (Engineer)፦ P18ን ከተሽከርካሪ ማውደሚያ መሳሪያዎ ጋር በማጣመር፣ ህንፃዎች ውስጥ የሚገኙ ጠላቶች አመድ ማድረግ ይችላሉ። 

  • ድጋፍ (Support)፦ ትኩረትዎን ህይወት ከማትረፍ እና ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ላይ ሳያነሱ ጥቃቶችን መጣል ይችላሉ። 

  • ስለላ (Recon፦: በተለይም ከቢከኖች (beacons) ወይም ከC4 ጋር በማጣመር ስውር ጥቃቶችን መጣል የሚያስችል ፍጹም ተመራጭ ነው። 

የትኛውንም ሚና ቢመርጡ፣ የጠላት እይታን ለመሸፈን፣ የእይታ መስመሮቻቸውን ለመከለል እና የአጭር ርቀት ውጊያዎች ላይ ውጤታማ መሆን እንዲችሉ፣ ሁሌም ቢሆንም የጢስ ቦምብ በእጅዎ ሊኖር ይገባል።። 

አሁን ላይ፣ የሙከራ ስሪቱ ሁለገብ ሚናዎችን ይደግፋል። P18 እንደ መጠባበቂያ መሳሪያነት ማገልገል የሚችል ቢሆንም፣ ለአጭር ርቀት ውጊያዎችም እንደ ዋና መሳሪያነትም ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። ይበልጥ ውጤታማ መሆን እንዲችሉ፣ የተለያዩ ቦታዎችን እና ሞዶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በርካታ አማራጮችን ቢሞክሩ፣ እንዲሁም የሴንሲቲቪቲ መቼትዎን እና አባሪ ማሻሻያዎችዎን የአጨዋወት ስልትዎን እንዲመጥን አድርገው ቢያስተካክሉ ይመከራል። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !