
M417 A2፣ የባትልፊልድ 6 ቤታ (ሙከራ) ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወዳጅነትን ማትረፍ የቻለ ሁለገብ እና ኃይለኛ መሳሪያ ሲሆን፣ አባሪ ማሻሻያዎችን ሲጨመሩበት ደግሞ ይበልጥ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ የሚያስችል ነው። ይህን ጠመንጃ በአግባቡ መጠቀም፣ እንደልብ መንቀሳቀስ፣ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ እንድችሉ እና በማንኛውም ሁኔታ ሊጠቀሟቸው የሚችሉ መሣሪያዎች ያካተተውን የ"Assault" ሚናን መጠቀም ይኖርብዎታል። እንደ M320A1 ያሉ ፈንጂ ማስወንጨፊያዎች ጋር አብረው በመጠቀም ሕንፃዎችን ማፈራረስ ወይም ተሽከርካሪዎችን ድምጥማጣቸውን ማጥፋት፤ እንዲሁም የጭስ ወይም ፍላሽ ቦምቦችን በመጠቀም ጠላቶችን ከተደበቁበት አግተልትለው ማስወጣት ወይም ከአጣብቂኝ አደጋ ለመማምለጥ ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ።
ወደ አባሪ ማሻሻያዎች ስንመጣ ደግሞ፣ የነጥብ አጠቃቀም ሲስተሙ በዘፈቀደ ሳይሆን ነገሮችን አስበው በጥንቃቄ እንዲወስኑ ያስገድድዎታል። ከሚመከሩ አማራጮች መካከል፣ M417 A2 ከመካከለኛ እስከ ረጅም ርቀት ለሚደረጉ ውጊያዎች፣ በተኩስ ወቅት አለመንገጫገጩ እና የማይዛነፈ የማነጣጠር አቅሙ ተመራጭ ነው። አጭር ድምጽ ማፈኛ (30 ነጥብ) የመሳሪያዎን እርግጫ እና ድምጽ በመቀነስ ጠላት ዓይን ውስጥ እንዳይገቡ ያስችልዎታል። ባለ368 ሚ.ሜ አፈሙዝ (10 ነጥብ) ደግሞ የጥይትዎ ረጅም ርቀት የመጓዝ አቅም ይጨምራል፤ 6H64 ቨርቲካል ግሪፕ (25 ነጥብ) በበኩሉ፣ በተኩስ ወቅት መሳሪያዎ እንዳይንገጫገጭ እና ዒላማ እንዳይሰት ያረጋጋልዎታል። ተከታታይ ተኩሶችን ለማድረግ፣ ባለ25 ዙሩን የጥይት ካርታ (15 ነጥብ)፤ የጥይትዎን የጉዳት መጠን ለመጨመር ደግሞ FMJ ጥይቶችን (5 ነጥብ)፣ እና ለመካከለኛ ርቀት ውጊያዎች CCO 2x ኦፕቲክን (10 ነጥብ) በመጨመር ይጠቀሙ።
እነዚህን አባሪዎች ከM417 A2 መሳሪያዎ ጋር አብረው በመጠቀም፣ በተለይ ቤታው ላይ በሚገኙ ነፃ አካባቢዎች ላይ የሚካሄዱ አብዛኞቹ ውጊያዎች ላይ አይበገሬ ሊያደርግዎ የሚችል እጅግ አስተማማኝ መሳሪያ ማድረግ ይችላሉ። እንዲሁም በአንድ የአጨዋወት ስልት እንዲገደቡ ከሚያደርጉ ሌሎች ጠመንጃዎች በተለየ፣ ማንኛውም ሁኔታዎች ላይ ሁለገብ አገልግሎት ይሰጥዎታል።
በአጠቃላይ፣ የልብ አድርስ፣ የማይዛነፍ እና ሁለገብ መሣሪያ እየፈለጉ ከሆነ M417 A2 ምርጫዎ ሊሆን ይገባል። የAssault ሚናን እና ተገቢዎቹን አባሪ ማሻሻያዎች እና የእጅ ቦምቦች በመጠቀም የጦር ሜዳውን መቆጣጠርና ድልን መቀዳጀት ይችላሉ።