
በ2025 የፎርትናይት የውጊያ ማለፊያዎን (Battle Pass) በፍጥነት ማሳደግ ከፈለጉ፣ የግድ XP የሚያገኙባችውን መንገዶች ማሳደግ አለብዎ። ይህንንም ለማድረግ፦ ተጫዋቾች ነጥቦችን መሰብሰብ እንዲችሉ በማሰብ የፈጠራ ሞድ (Creative mode) ላይ የተዘጋጁ ካርታዎች ላይ መሳተፍ፤ XP Infinity ላይ በራስ-ሰር XPዎችን መሰብሰብ፤ የሚያሸልሙ 50 መዳረሻዎች ያሉት Creative XP Parkourን መጫወት፤ ወይም ፈጣን ድሎችን ማግኘት የሚችሉበት Box Fight Battle Arena ላይ በመሰልጠን እጅግ በርካታ XPዎችን መሰብሰብ ይችላሉ። የተለያዩ ካርታዎችን በመቀያየር መጫወት እየተዝናኑ፣ ሳይሰለቹ ደረጃዎን በፍጥነት ማሳደግ ያስችልዎታል።
በዚህ አያበቃም፤ ዕለታዊ እና ሳምንታዊ ተልዕኮዎችን ከመደበኛ ጨዋታዎ ጋር በማዋሃድ በቀላሉ የተለየ ጥረት ማድረግ ሳይጠበቅብዎ በርካታ ሽልማቶችን መሰብሰብ እና ደረጃዎን በፍጥነት ማሳደግ ይችላሉ።
ሌላው፣ ሁለት ወይም በቡድን በመሆን መጫወት XPዎን መጨመር የሚችሉበት ሌላ ቀላል ዘዴ ነው። ለቡድን XP ጉርሻዎች ምስጋና ይግባና፣ እስከ +120% የሚደርሱ ተጨማሪ XPዎን ማግኘት የሚችሉባቸው አንዳንድ አጋጣሚዎችም አሉ። ከጉርሻዎቹ ባሻገር፣ ከጓደኞች ጋር መጫወት ጌሙን ይበልጥ አስደሳች እና ተልዕኮዎችን የማጠናቀቅ እድልዎን ይጨምርልዎታል።
እንዲሁም በEpic Games የሚዘጋጁ እንደ ድርብ XP weekends ያሉ ልዩ ዝግጅቶች ሊያመልጡዎ አይገባም። የጨዋታ ጊዜዎን እነዚህ ዝግጅቶች በሚደካሄዱበት ወቅት በማድረግ፣ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ብዙ ደረጃዎችዎን ማሳደግ ይችላሉ።
ሌላው ቁልፍ ነገር፣ በየጊዜው ሞዶችን እና ካርታዎችን መቀያየር ነው። ተመሳሳይ ተግባሮች ወይም ካርታዎች ላይ ለረጅም ጊዜ መቆየት በጊዜ ሂደት የXP ገቢዎን ይቀንሰዋል። Battle Royaleን፣ ተልዕኮዎችን ወይም የCreative XP ካርታዎችን እየቀያየሩ መጫወት ቀጣይነት ያለው እና ያለተገደበ እድገት እንዲያገኙ ያስችልዎታል።
እነዚህን ሁሉ ዘዴዎች አጣምሮ በመጠቀም፣ በቀን እስከ 150,000 XPዎችን በቀላሉ ማግኘት እና ደረጃዎን በሚያስደንቅ ፍጥነት ማሳደግ ይችላሉ። ያስታውሱ! አንድ ነገር ላይ ችክ ሳይሉ የተለያዩ ነገሮችን ይሞክሩ፣ የጉርሻ መጠኖችዎን ያሳድጉ፣ እያንዳንዱን ግጥሚያ የውጊያ ማለፊያችሁን (Battle Pass) ማሳደግ ወደሚችሉበት አጋጣሚ ይቀይሩ።
መልካም ጨዋታ!