
ከሴፕቴምበር 6 እስከ 7፣ ሊዮን ከተማ ውስጥ በሚገኘው የLDLC ስቴዲዬም የሚካሄደው የ2025ቱ የፎርትናይት ዓለም-አቀፍ ሻምፒዮና፣ በአይነቱ አዲስ የሆነ የሶስትዮሽ ቡድን አወቃቀር እና ለሁለት ቀናት የሚቆይ እልህ አስጨራሽ በፉክክር የተሞላ ውድድር ለተመልካቾች የሚያቀርብ ይሆናል።
ይህ የዓለም ሻምፒዮና በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሶስት አባላትን የሚያቅፍ የቡድን አሰላለፍን የሚከተል ሲሆን፣ ሠላሳ ሦስት ቡድኖች በFNCS የተዘጋጀውን፣ የዲቪዥናል ካፕ፣ ፕሌይ-ኢንስ፣ የቡድን ደረጃዎች፣ የመጨረሻ ዕድል ማጣሪያዎች እና የክልል ፍጻሜዎችን ያካተተ ረጅም እና አድካሚ ፈተናዎችን ካለፉ በኋላ ውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ብቁ መሆን ችለዋል። በአጠቃላይ 11 ከአውሮፓ፣ 7 ከመካከላዊ ሰሜን አሜሪካ፣ 3 ከሰሜን ምዕራብ አሜሪካ፣ 3 ከእስያ፣ 3 ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ 3 ከብራዚል እና 3 ከኦሽኒያ የተውጣጡ ቡድኖች ውድድሩ ላይ ይሳተፋሉ።
በቀን ስድስት፣ በአጠቃላይ 12 ግጥሚያዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ ሁሉም ቡድኖች እያንዳንዱ ዙር ላይ ይወዳደራሉ። የመጨረሻው ደረጃ አሰጣጥ የሚወሰነውም የምርጦች ምድብን (ምርጥ 1፣ ምርጥ 5፣ ምርጥ 10...) እና የወዳቂዎችን ምድብን በሚሸልም የነጥብ አሰጣጥ ሲስተም የተዘጋጀ በመሆኑ፣ ቡድኖች የቆይታ ጊዜያቸውን እና ጥረታቸውን ማመጣጠን እንዲችሉ ይረዳቸዋል። 12ቱ ግጥሚያዎች ከተደረጉ በኋላ፣ በርካታ ነጥቦችን የሰብሰበው ቡድን የዓለም ሻምፒዮና በመሆን ከአጠቃላዩ የ$2,000,000 ሽልማት ትልቁን ድርሻ የሚሸለም ይሆናል።
ሌላው ጉዳይ፣ ይህ ዙር ታዋቂውን “Axe of Champions“ን የሚተካ “Blade of Champions” የተባለ የፎርትናይት ኢ-ስፖርት የተሃድሶ ዘመንን የሚያመለክት አዲስ ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋውቃል።
ሁሉም ግጥሚያዎች በፎርትናይት የTwitch እና YouTube ቻናሎች ላይ ከዝርዝር ስታቲስቲክስ ዘገባዎች እና የዴስክ ትንታኔዎች ጋር ውድድሩን በአካል በመገኘት መመልከት ላልቻሉ በቀጥታ ይተላለፋሉ። እንዲሁም ዝግጅቱ ከመጀመሩ በፊት ቀድመው የEpic Games አካውንታቸውን ከቀጥታ ስርጭት ፕላትፎርሙ ጋር ለሚያገናኙ ተመልካቾች ልዩ ልዩ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል።
የፎርትናይት የአሸናፊዎች ዙፋንን ለመቀዳጀት የሚፋለሙ 33 ቡድኖችን፣ 12 በፉክክር የተሞሉ ግጥሚያዎችን፣ በድጋፍ እና ከፍተኛ ውርርድ የተሞሉ ሁለት አስደናቂ ቀናትን የሚያቀርበው ይህ ግዙፍ የዓለም ዋንጫ ዝግጅት፣ የተጫዋቾችን ስልት፣ የተቀናጀ አሰራር እና የአዕምሮ ፅናት የሚፈትን የዓመቱ ድንቅ የኢ-ስፖርት ክስተት እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም።