icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

የፎርትናይት አዲሱ የቼዝ ሞድ የሆነውን፣ የፖሊስ ሲሙሌተር ራሽን እንዴት መጫወት ይቻላል? 

ፎርትናይት ላይ አዲስ ነገር መሞከር ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ፣ በቅርቡ Creative Island ላይ የተካተተውን እና የወንጀል ፊልም ላይ እየተወኑ ያሉ እስከሚመስልዎት ድረስ ባትል ሮያልን የፖሊስ እና ሌባ ሽኩቻ ድባብ ያለበሰውን Police Simulator Rush ዛሬውኑ ይሞክሩ። በዚህ ጌም መሆን የሚፈልጉትን ሚና መምረጥ የሚችሉ ሲሆን፣ ካሻዎት ጎዳናዎች ላይ የመኪናውን ሳይረኖች እያንቦገቦገ የሚንቀሳቀስ ፖሊስ፣ አይ! ካሉ ደግሞ በኒዮን መብራቶች የተንቆጠቆጠ መኪናው ውስጥ ሙዚቃውን ጣሪያው እስኪቀደድ ድረስ ከፍቶ የሚሾፍር ሌባም መሆን ይችላሉ። ይሄ ሁሉ የሚሆነው የተጨናነቁ አውራ ጎዳናዎች፣ ጠባብ መተላለፊያዎች፣ ያሉባት ትልቅ ከተማ ውስጥ ነው። ከፍተኛ ዝላዮችን ማድረግ፣ ሳንቲሞችን መሰብሰብ፣ የሚችሉ ሲሆን፣ ሰባቱ ተፎካካሪዎችዎን ማሸነፍ እንዲችሉ በተገቢው ሰዓት የፍጥነት ማስወንጨፊያዎን መጠቀም ይጠበቅብዎታል። 

በቀላልሉ መቀላቀል የሚችሉ ሲሆን፣ በቅድሚያ ኮምፒውተርዎ ላይ ፎርትናይትን ይክፈቱ እና Creative mode ውስጥ “Enter Island Code” የሚለውን በመምረጥ፣ 7147-2213-2365 ብለው ይጻፉ እና ያረጋግጡ። አለቀ! 

እዚህ ጌም ውስጥ 8 ተጫዋቾችን የሚያሳትፍ ፈጣን ውድድር፣ የመረጡትን ሚና የሚመጥኑ ቄንጠኛ መኪኖች፣ በመሰናክሎች እና መወጣጫዎች የተሞሉ ተለዋዋጭ ቦታዎች፣ ነጥብዎን ለመጨመር መሰብሰብ የሚችሏቸው ሳንቲሞች፣ እና ምርጥ ከሚባሉ ተጫዋቾች ጋር መወዳደር የሚችሉበት ዓለም አቀፍ የመሪዎች ሠሌዳ ይጠብቁዎታል። አሸናፊዎች የሚጠቀሙት አንድ ምስጢር አለ፣ እሱም ፍጥነት መጨመሪያ መሳሪያቸውን በአግባቡ እና ትክክለኛው ሰዓት ላይ መጠቀም መቻላቸው ነው። እርስዎም በጥበብ ከተጠቀሙበት፣ ከተሸናፊነት ወደ ኩሩ አሸናፊነት ሊያበቃዎ ይችላል። 

ጥቂት የማሸነፊያ ዘዴዎች፡- ከተወዳዳሪዎች ለመራቅ አቋራጮችን እና ጉልበት መጨመሪያ ዞኖችን ይፈልጉ፣ ፍጥነትዎን አስቸጋሪ ቦታዎች ላይ ወይም ማጠናቀቂያ መስመሩ ላይ በብልሃት ይጠቀሙ፣ እንዲሁም የአጨዋወት ስልትዎን ከሚናዎ ጋር በማመጣጠን ይጫወቱ። ፖሊስ ከሆኑ ሌቦችን በቀላሉ መያዝ እንዲችሉ በቡድን ተቀናጅቶ መስራት አስፈላጊ ነው፤ ሌባ ከሆኑ ደግሞ ፖሊሶችን ማምለጥ እንዲችሉ፣ ከመጀመሪያው ጀምሮ በፍጥነት መንዳት እና መተላለፊያ አቋራጮችን ወይም በትራፊክ የተጨናነቁ መንገዶችን መጠቀምን አይርሱ። 

  
መልካም ጨዋታ! 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !