icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

 

ፎርትናይት ምዕራፍ 6 ክፍል 4 ላይ የሚገኘው፣ ምስጢራዊውን የዲኖ-ሜጋዞርድ ስኪን እንዴት ማስከፈት ይቻላል?

እንኳን ደስ አላችሁ! በመጨረሻ የዲኖ-ሜጋዞርድ ስኪን ፎርትናይት ላይ ሊካተት ነው! በዚህ ሲዝን በጣም ከሚጠበቁ ነገሮች መካከል አንዱ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም! ከፓወር ሬንጀርስ ጋር የተደረገው ይሄ ልዩ ሽርክና እ.ኤ.አ. ሴምፔምበር 16፣ 2025 ላይ በምዕራፍ 6 ክፍል 4 የሚጅመር ይሆናል። 

የዲኖ-ሜጋዞርድ ስኪን የእቃ መሸጫ መደብሩ ውስጥ ሊያገኙት የማይችሉት፣ የዚህ ሲዝን "ምስጢራዊ ስኪን" ነው። ማግኘት የሚችሉት Premium Battle Pass ወይም የፎርትናይት ቡድን (Fortnite Crew) ምዝገባ ያላቸው ተጫዋቾች ብቻ ናቸው። እ.ኤ.አ.ከሴምፔምበር 16 ጀምሮ፣ ተጫዋቾች የፓወር ሬንጀርስ ጭብጥ ያላቸው ተልዕኮዎች፣ የልዩ እቃዎች እና የጦር መሣሪያ ተልዕኮዎች እና ግዙፍ የደሴት ላይ ጦርነቶች ላይ መሳተፍ የሚችሉባቸው ልዩ የዲኖ ተልዕኮዎች የሚጀመሩ ሲሆን፣  እንደ Lil' Zord Battle ሞድ ኢሞቶች፣ የPower Sword መጥረቢያ (pickaxe)፣ ልዩ loading screen እንዲሁም ስፕሬይ እና አይከኖችን የመሳሰሉ ልዩ ሽልማቶችንም መሸለም ይችላሉ። 

በተጨማሪም፣ ታታሪ ለሆኑ ተጫዋቾች፣ የዲኖ-ሜጋዞርድ ስኪን በጥቁር እና ወርቃማ ቀለም የተዘጋጀ ሲሆን፣ ይህንንም ተሸላሚ ለመሆን የBattle Pass ተጨማሪ የተልዕኮዎች ገጽ ላይ መድረስ ወይም ከሜጋዞርድ ጋር የተያያዙ ማንኛውም ተልዕኮዎች ማጠናቀቅ ከተጫዋቾች ይጠበቃል። 

እነዚህ ተልዕኮዎች እስከ እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 1፣ 2025 ድረስ የሚቆዩ በመሆናቸው፣ ተጫዋቾች ሁሉንም ግቦች ማሳካት እና ይህን ታዋቂ ስኪን እስከወዲያኛው ከመጥፋቱ በፊት እጃቸው ውስጥ ማስገባት የሚችሉበት የስድስት ሳምንታት ጊዜ አላቸው።  

ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ይህ ልዩ የዲኖ-ሜጋዞርድ ስኪን ሎከርዎ ውስጥ እንዲኖር ከፈለጉ፣  አሁኑኑ Battle Passዎን ያዘጋጁ እና የPower Rangers ተልዕኮዎች እንደተጀመሩ ጊዜ ሳያጠፉ ይቀላቀሉ። 

 መልካም እድል! 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !