
ኔትፍሊክስ ላይ ያዩትን አስደናቂውን ስኩዊድ ጌም ፎርትናይት ውስጥ መጫወት ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ የምስራች! ኔትፍሊክስ ላይ ከሚገኘው ተከታታይ ፊልም ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው፣ በርካታ የፈጠራ ካርታዎች (Creative maps) ፎርትናይት ላይ ተዘጋጅተዋል። ደስ የሚለው ነገር ደሞ በቀላሉ "ቀይ መብራት፣ አረንጓዴ መብራት" (Red Light, Green Light)፣ የመሰናክል ውድድሮችን፣ የማምለጥ ጨዋታዎችን እና ራሱን ስኩዊድ ጌም በፎርትናይት ስታይል በቀላሉ ማግኘት እና ከሌሎች 16 ተጫዋቾች ጋር መጫወት ይችላሉ።
የስኩዊድ ጌም ደሴትን ለመቀላቀል፣ ፎርትናይትን ይክፈቱ፣ ወደ ክሬቲቭ ሞድ በመሄድ "Enter Island Code" የሚለውን ክሊክ በማድረግ መጫወት የሚፈልጉትን የካርታ ኮድ ያስገቡ። በ2025 ተወዳጅነትን ካተረፉ ኮዶች መካከል፦
Squid Grounds (Reload Mode):- ምንም ኮድ ሳያስፈልግዎ፣ በቀጥታ Epic Games’ Reload mode ላይ ማግኘት ይችላሉ።
Octo Game 3፦ 6780-5121-6543
OCTO GAME SQUAD NITE፦ 9870-6349-9196
Squid Run (escape game)፦ 0357-8039-3531
Squid Game 3 by ughbug፦ 3526-0995-1394
እያንዳንዱ ካርታ የራሱ የሆነ ይዘት እና ድባብ ያለው ሲሆን፣ አንዳንዶቹ በህልውና ላይ ሲያተኩሩ፣ ሌሎቹ ደግሞ ፈጣን ምላሽ ወይም የቡድን ስራ ላይ ያተኩራሉ።
አሪፍ ተሞክሮ ማግኘት እንዲችሉ ከጓደኞቻችሁ ጋር (በበዛችሁ ቁጥር ይበልጥ የተሻለ ይሆናል) በመሆን ይጫወቱ። ያስታውሱ! ለእያንዳንዱ የደሴት ህግጋት ትኩረት ይስጡ፣ እንዲሁም "ቀይ መብራት፣ አረንጓዴ መብራት" (Red Light, Green Light) የሚለውን ጨዋታ በደንብ ይለማመዱ፣ ምክንያቱም አንዷ ትንሽ ስህተት ከጨዋታው ልታስባርርዎ ትችላለች። በተጨማሪም እያንዳንዱ የካርታ ፈጣሪ የተለያዩ ይዘቶችን እና አጨዋወቶችን ካርታቸው ላይ ስለሚያካተቱ የተለያዩ ካርታዎችን ከመሞከር ወደኋላ አይበሉ።