
EA FC 26 በአስደናቂ የስልት ማስተካከያዎቹና በተሻሻለ የAI የመከላከል የUltimate Team ጨዋታን መለወጥ ችሏል። ሁሌ ማሸነፍ እንዲችሉ ትክክለኛ አሰላለፍ መምረጥና ስልትዎትን ሊያስተካክሉ ይገባል። ሁሉም የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ላይ ቅድሚያ መስጠት ያለብዎትን ቁልፍ ማስተካከያዎች እና አሰላለፎች እንደሚከተለው አስቀምጠናል።
4-2-3-1 Wide አሁንም አስተማማኝ የሆነ አሰላለፍ ነው። በጣም የተመጣጠነ ሲሆን የመከላከል ብቃትን፣ አጥቂ አማካይንና ፈጣን ሽግግሮችን ያጣምራል። ሁለቱ አማካይ ተከላካዮች ከተቃራኒ ቡድን የሚመጡ ጥቃቶችን መከላከል እንዲሁም የጨዋታ ፍጥነት መቆጣጠር ላይ ይሰራሉ፣ የጎን አማካዮች ደግሞ ጠንካራ የማጥቃት ድጋፍን ይሰጣሉ። ጨዋታውን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር የሚያስችልዎ ምርጥ አሰላለፍ ነው።
4-2-1-3 ከፍተኛ የማጥቃት ስልት ላይ ያተኩራል። የማዕከላዊ አጥቂ አማካዩ ከአጥቂው ጎን ለጎን ልክ እንደ ሁለተኛ አጥቂ ሆኖ ይጫወታል፣ ሦስቱ አጥቂዎች ደግሞ ፈጣን ዕድሎችን ለመፍጠር በመጣመር ይሰራሉ። መልሶ ማጥቃት ላይ ክፍተቶችን አግኝተው ሲጠቀሙበት እጅግ ውጤታማ የሚያደርግዎ አሰላለፍ ነው።
ታዋቂው 4-4-2 በዚህ ሲዝንም ተመልሶ መጥቷል። ይህ አሰላለፍ፣ በጥቃት እና በመከላከል መካከል ያለው ሚዛናዊነት፣ አስተማማኝ የማዕከላዊ አማካይ ጥምረቱ እና ውጤታማ የክንፍ ተጫዋቾች አጠቃቀሙ ቀለል ያለ፣ ውጤታማ እና ተደራሽ አማራጭ ያደርጉታል።
ከስልቶች አንጻር "ሚዛናዊ" እና "የመልሶ ማጥቃት" የአጨዋወት ስልቶች በጣም ውጤታማ ናቸው። ሚዛናዊ የሚባለው ስልት 4-2-3-1ን በመጠቀም ኳስን በመቆጣጠር ፈጣን መልሶ ማጥቃቶችን ለማድረግ ምርጥ ነው፣ መልሶ ማጥቃት ደግሞ በ4-2-1-3 ወይም 4-4-2 ቡድንዎ በፍጥነት እንዲንቀሳቀስ እና ተቀራኒ ቡድን ጫና በሚፈጥርበት ወቅት ለመቆጣጠር ያስችልዎታል።
በመከላከያ ረገድ፣ በ50 እና 70 መካከል የሚገኝ መስመር ከ"ሚዛናዊ" ጫና ስልት ጋት መጠቀም ረጅም ኳሶችን ለመገደብ ያስችልዎታል፣ መመለስ ከፈለጉ ደግሞ ይበልጥ ጠንከር ያለ ጫና ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሲቃረብ መጠቀም ይችላሉ።
የተጫዋቾች ሚና፡
ግብ ጠባቂ፡- ቦታን ለመሸፈን እንዲረዳ Sweeper ወይም Balanced ይምረጡ።
ተከላካዮች፡- አደጋዎችን ለመቀነስ በሚያጠቁበት ጊዜ ወደኋላ ይመለሱ።
አማካይ ተከላካዮች፡- የተቃራኒ ቡድንን ጥቃት ለመስበር ኳስ የሚቀሙና ቦታ የሚሸፍኑ ሚናዎችን ይምረጡ።
አማካይ አጥቂዎች፡- ግቦችን ለማስቆጠር የሚያግዙ Shadow Striker ወይም Inside Forward ይምረጡ።
አጥቂዎች፡- ውጤታማ ለሆነ አጨራረስ Advanced Forward ወይም Poacher ይጠቀሙ።
የበላይነትን የመቆጣጠር ምስጢሩ መላመድ ነው። በFC 26 አዳዲስ ሚናዎችና የመከላከያ ዘዴዎች በመጠቀም የጨዋታ እቅዶችዎን ውጤትን፣ ተጋጣሚዎን እና ወቅታዊ ሁኔታዎችን መሠረት በማድረግ ያስተካክሉ። የተለያዩ ዘዴዎችን እና ስልቶችን መጠቀም ከጊዜ በኋላ የበላይነትን ያስገኝልዎታል።